#እንዴት #ሆድ #አይባሰን?

የዳባት ከተማ በዘመነ ሕወሓት የ40 ዘመን ብቀላ
==========================[====
ከሀዲው #ክንፈ #ገብረ #መድሕን ዳባት ነው ያደገው 
ዳባትን እንደውኃ ቀጅ ከደደቢት መርቶ ወገራን መውር የጀመረው ከ1970 ዎቹ ጀምሮ ነው
አስታውሳለሁ ]

የማይልኮ ውጊያ የዳባትን ተደጋጋሚ ወረራ
የዳባት መሠረተ ልማት ውድመት
በ1973 እና 1974 ዳባት ብሔራዊ ባንክ ነበር
ለሁለቱም አውራጃ አገልግሎት የሚሰጥ ታላቅ የሸቀጥ ማከፋፈያም ነበር ኢዲዲሲ የሚባል
የዳባት ከተማ ( የወገራ አውራጃ) በ ተከታታይ የምትመራው በአካባቢ ተወላጅ ነበር
ከደጃዝማች አያሌው ብሩ እስከ ደጃዝማች ቢትወደድ አዳነ መኮነን ከአብዮቱ በነ አባይ ጎሹ እንዲህ እያለች የቆየች ነበረች
የተግራይ ወራሪው ሕወሓት ከወገራ አወራጃ ሰሜናዊ ምዕራብ የወልቃየት ጠገዴን መድር ምዕራባዊ ዳርቻ እስከ ሱዳን የተዘረጋው መጠነ ሰፊ ለምና ድንግል ምድር የአርማጭሆን ግዛት የሰቲት ሁመራን ሰሊጥ አብቃይ ምድር ለመውሰድ በግልፅና በስውር በወገራ ላይ ደባና አሻጥር ግድያ አፍኖ መሰወር ከ40 ዘመን በላይ ነው
አስታውሳለሁ ሕወሓት ለመጀመሪያ ወረራ በመጣ ጊዜ ደባት ከተማን ለመያዝ አላቻለም ነበር ጦርነቱ ማይልኮንና ዳራ አካባቢ ላይ ነበር
ዳባት ከተማን የያዙበት አጋጣሚም አስታውሳለሁ
ስለዳባት ከተማ ልማት ታላቅ ባዛር ተዘጋጅቶ ነበር
የዳባት ባዛር ገቢው ለዳባት ከተማ ሲሆን በርካታ ሰዎች የታደሙበት በርካታ ደግሥ የተዘጋጀበት ዕለት ነበር ባዛሩ የሚከፈተው ዕለተ ሰንበት እሁድ ነበር በዋዜማው ቅዳሜ ራሴ ዳባት ከተማ ነበርኩ ማታውን ከዳባት ከተማ ገደብጌ ተመልሸ አዳሬ ገደብጌ ነበር በዛች ሌሊት የዳባት ከተማ በትግራዩ ነፃ አውጭ ሕወሓት ተወራ አደረች ያ ሁሉ ደግስ እንዳለነበር ተደረገ የዳባት ከተማ አሳቢ የነበሩ መሪዎች ሁሉም በየቤታቸው ተከበው ተደበደቡ ከማስታውሳቸው ሰዎች
የወጋራ አውራጃ ዋና አስተዳዳሪ
አቶ አባይ ጎሹ እና የሃምሳ አለቃ ደርሶ ነበሩ
ሃምሳ አለቃ ደርሶ የዳባት ተወላጅ ሲሆን አቶ አባይ ጎሹ የወልቃይት እና የጠገዴ ተወላጅ ነበር
በነገራችን ላይ ወገራን ከሚያስተዳድሯት አብዛኞዎቹ የወለቃይት ጠገዴ ሰዎች ነበሩ
ከቡር ደጃዘማች ቢትወደድ አዳነ መኮነንም የወልቃይት ጠገዴ ተወላጅ ሲሆኑ በነ አዲሱ ለገሰ ነበር ለድርድር ብለው ሳይስቡት ከበው ተከዜ ላይ የተገደሉት

Play