የሐረርን ከተማ ያወደማው ግዙፋ የኢጣሊያ የአየር ጥቃት

# ኢዮብ ዘለቀ
“ከልጅነት ጀምሮ የሚበልጠውን ዘመናችንን ያሳለፍነው በዚሁ በሀረር ከተማ ስለሆነ በቦምብ መመታቱንና መቃጠሉን በተለየ ልባችንን አሳዝኖናል::”
ግርማዊ ቀደማዊ ኃይለስላሴ
ከ81 አመት በፊት በመጋቢት ወር 1928 ዓ.ም የኢጣሊያ የጦር አውሮፓላኖች ድንገት በሐረር ከተማ ላይ ከፍተኛ ድብደባ ፈጸሙ ፤በዚህ ጥቃታ በርካታ ንጹሀን ዜጎች አብዛኛዎቹ ህጻናት እና ሴቶች አለቁ፤ በርካቶችም ቆሰሉ ፤ከቤት ንብረታቸውም ተፈናቀሉ ።
ይህንን ጥቃት ተከትሎ በአውሮፓና በሌሎችም አለማት የሚገኙ ጋዜጦችም ዜናውን በፊት ገጾቻቸው ላይ አስፈሩት፤ ከነዚህ ጋዜጦች አንዱ በአውስትራሊያ ይታተም የነበረው The Canberra Times ነው ይህ ጋዜጣ በ March 31,1936 እትሙ የአየር ድብደባውን አስመልክቶ እንደሚከተለው ጽፎ ነበር …..
” Italian bombs destroy harar mass air raid, undefended town, 40 killed: 120 injured. harar the second largest city in Abyssinia, was practically destroyed today, when 37 Italian bombers engaged in a mass air raid on the city”
Jeff perarce prevail the inspiring story of ethiopias victory በተሰኘው መጽሀፋቸው /ወደ አማርኛ በኤፍሬም አበበ ተተርጉሟል / ስለ ሀረሩ የአየር ጥቃት ይህንን ጽፈዋል …..
“መጋቢት 29 ቀን የኢጣሊያ ቦምብ ጣዮች የሃረርን ሰማይ ወረሩት ፡፡
ከማለዳ 1፡15 ሰዓት አካባቢም የኢትዮጲያን ሁለተኛ ቅዱስ ከተማ አመድ ሊያደርጉ ወሰኑ ፡፡
ያለምንም ፩ መቃወሚያና ወታደራዊ ጣቢያ በግላጭ ያገኞትን ከተማ አወደማት ፡፡
በድብደባው 40 ገድለው ከ 120 በላይ አቆሰሉ ፡፡ ጥንታዊቷ ከተማቸው የወደማችባው በሺህ የሚቆጠሩ ሃረሪዎችም ቤት አልባ ሆኑ ፡፡
በድብደባው አሮገው ቤተመንግሰት የፈረንሳ ሆስፒታልና ቆንስላ ራዲዮ ጣቢያ እስ ቤት ወደሙ ፡፡
የጃንሆ አባት ራስ መኮንን የተቀበሩበት ካቴድራልና የአፍሪካ መስጅድም ጋይተዋል፡፡”
ሁለተኛው ምስል በ alfred eisen staedt ከጥቃቱ ጥቂት ቀናት ቀድም ብሎ የተነሳ ፤የሐረር ከተማ ከፊል ገጽታ የሚያሳይ ምስል ነው