No automatic alt text available.
Eshete Kassa Zewudie

July 22, 2015 ·

እኛ እና መኪኖቻችን ============= አማሮች በኢትዬጵያ ምድር ተዘዋውረን የመስራት እና ንብረት የማፍራት መብቶቻችንን ያለ ህግ አማራ ስለሆን ብቻ ከተገፈፍን ቆይተናል። አማራ እና የአማራ በሆነ ነገር ላይ ማንም እጁን መጫን እንዲችል ሆኖ ያልተፃፈ ህግ ተቀምጧል። የአማራ መሬት ቋንቋ፣ባህል፣ሃይማኖት ፣ ቅርስ፣ ሃብት ወዘተረፈ ያለ ከልካይ ይዘረፋል፣ይዘለፋል፣ ይወድማል። ሃይ የሚለው የለም። ለዛሬው ስለ አማራ መኪኖች ትንሽ ልበል… …
የአማራ ታርጋ ይዞ ከአማራ ክልል ውጭ መንቀሳቀስ በአሁኑ ሰአት ከፈተኛ እንግልት እና ኪሳራ እያስከተለ ይገኛል። ሹፌሮቻችን አባይን ተሻግረው ጎሃ ፂዬን ብቅ እንዳሉ የሚደርስባቸው እንግልት ይሄ ነው አይባልም። የኦሮሞ ትራፊኮች ያለ ምንም ምክንያት እያስቆሙ የገንዘብ ቅጣት ይቀጧቸዋል። ለምን? ብለው የሚጠይቁትን እዬደበደቡ እስርቤት ይወረውሯቸዋል። ያውም በአማራነታቸው እዬሰደቡ እና እያንቋሸሹ ።
ወደ ትግራይ ክልልም ሲሄዱ የአማራ ሹፌሮች ብዙ ጊዜ እንደተደበደቡ ፣እንደተሰደቡ ፣ ያለ አግባብ እንደተቀጡ ነው። በአማራ ስም የሚንቀሳቀሱ መኪኖች ትንፋሽ አግኝተው በሰላም መንቀሳቀስ የሚችሉት አማራ ምድር ላይ ጎማቸው ሲረግጥ ብቻ ነው። ከአዲስ አበባ ማዶ ወደ ደቡብ ወደ ምስራቅ በአማራ ታልጋ ተዘዋውሮ መስራት ህልም እየሆነ ነው።ትራፊኮች አማ ሚለውን ታልጋ ሲያዩ የአማራ ጥላቻቸው ይገነፍላል። ፊሽካቸውን የሚያደርጉት ያሳጣቸዋል።ይወራጫሉ ።ሆቴሎች እና የአገልግሎት መስጫ ቦታዎች ለአማራ ሹፌሮች የሚያሳዩት መስተንግዶ ጥላቻን በሚያንፀባርቅ እና በሚንጓጠጥ መልኩ ነው። አንዳንዴ አልጋ እያላቸው በቁጣ “የለም !” እስከማለት የሚደርሱ ሆቴሎች እንዳሉ በተደጋጋሚ ሰምቻለሁ።
በአንፃሩ አማራ ክልል የሚመጡ የሌላ ክልል ታልጋ የተነለጠፈባቸው መኪኖች በነፃነት ተዘዋውረው የመስራት መብት ተሰጧቸዋል።ህዝቡም ምንም አይመስለውም ።መስተንግዶውንም ፍትፍት ከሚያስንቅ ፈገግታ ጋር ያቅርብላቸዋል። የአማራ ባለ ሃብቶች እና ሹፌሮች አሁን አሁን አንድ ዘዴ ዘይደዋል አሉ። መኪናቸውን በኦሮሚያ ክልል አስመዝግበው የኦሮሚያ ታርጋ ማውጣት። የመኪና ታርጋ ብቻ አይደለም ወደ ቡሬ አካባቢ ያሉ አማራ ነጋዴዎች የኦሮሚያ ንግድ ፍቃድ ሁሉ እያወጡ ነው።በባለፈው አንድ ኦሮምያ ውስጥ የሚኖር አማራ ለልጁ የወደፊት ደህንነት ሲል የኦሮሞ ስም አውጥቶለት ነበር ። መኪኖቻችን እና እኛ አንድ ሆንን ማለት ነው።
ይቺ ምድር የእኛ እንዳትሆን ተደርጋለች ። አማራ የሆነ ሰውም ሆነ እቃ ማየት አትፈልግም።ስለሆነም አማሮች በነፃነት እዬሰሩ የሚኖሩባት የማይሞቱባት ፣የማይጠሉባት ፣ የማይፈናቀሉባት ፣ በፍቅር የሚኖሩባት …ሃገር ከመቸውም ግዜ በበለጠ አሁን ይፈልጋሉ። ቢችሉ ግንባራችን ላይ አማራ እያሉ ቢያትሙብን እና በየደረስንበት ቢያሳድዱን ደስታቸው ነው። ማን ያውቃል ወደፊት እንደዛ ሊያደርጉ ይችላሉ። ልክ እንደ አይሁዶች ክንዳችን ላይ አማራ የሚል ጹሑፍ ሊያስሩብን ይችላሉ… የህወሓት እቅድ ይህ ነው። አማራ በተደረሰበት በአማራነቱ እንዲጠቃ ማስደረግ ።
የአማራን ህዝብ አስተዳድራለሁ የሚለው የሕውሐት የጡት ልጅ ብአዴን በዛ ህዝብ ላይ ይህ ሁሉ እንዲሆን አፈጣጠሩ ነው እና እዬተቁለጨለጨ ከማየት ውጭ አንዳች የሚፈይድልን ነገር የለውም። አቅመ ቢስ ነው። የሚሰራው ስራ አለ ከተባለ ከሌሎች ክልሎች በበለጠ ግብርን ከመጠን በላይ በአማራ ነጋዴዎች ላይ በመጣል ነጋዴ ወገኖቻችን ደም እያስተፋ ግብር ሰብስቦ ለፌድራል መንግስት ያስገባል። ግብር አሰባሰቡ ልዩ ነው። ተጨብጭቦለታል። በሰበሰበው ገንዘብ ግን ለአማራ ህዝብ መሰረታዊ ልማት አይሰራበትም። ብዙ ግብር ሰበሰበ ለመባል ብቻ ደፋ ቀና ይላል። ህወሓትን ያስደስታል። ይሄው ነው የመጨረሻ ግቡ ።
ህዝባችን በሁሉም ዘርፍ ተጠቅቷል። በምድር ላይ ይህን አይነት በደል የደረሰበት ህዝብ በታሪክ ሰምቼም አምብቤም አላውቅም።የአማራ ሰቆቃ ልዩ ነው። በጣም የሚገርመው ግን የአማራ ልጆች ለትግል አለመነሳታቸው ብቻ ነዉ፡፡ አንድ ሰው የአንተ የሆኑ ንብረቶችን፣ መገለጫዎችን እና ስሞችን ከጠላ አንተን የምር ጠልቶሃል ማለት ነው። እንደ ነገርኩህ መኪኖቻችን ምስክሮች ናቸው ። ካላመንከኝ መኪናህን እያሽከረከርክ ወደ ኦሮምያ ፣ደቡብ ፣ ትግራይ ፣ሶማሌ ሂድ የጥላቻን ጥግ ታያታለህ ። እሱ ካቃተህ ግን ጎጃም በረንዳ እና ጎንደር በረንዳ ሂድ እና ባለ አማ ታርጋ መኪና ሹፌሮችን… እህሳ? በላቸው ብሶታቸውን ይዘረግፉልሃል።
ጎበዝ ስንጠላ እማ ይግባን ። ሲጠሉት የማያውቅ ጅል ነው። ገለውም ፣ አፈናቅለውም፣ ዘርፈውም ፣ አስረውም፣ አሰቃይተውም… …ጥላቻቸውን እያሳዩን ነው ። እንዴት አይገባንም? አማራ የሚል ታርጋ የተለጠፈባቸው መኪኖቻችን አፍ አውጥተው ቢነግሩን ይገባን ይሆን? …ለሁሉም ነገር ልክ አለው። ወገኖቼ ጨርሶ ሳይመሽ እንንቃ