ዝምታ የመሽነፍ ምልክት ነው 
====================
በዚህ ዘመን አፈራሽ የውጊያ ሥልት እኛ ኢትዮጵያውያን መጠቀም አልቻልነም ::

ምክንያት ደግሞ ፍላጎት ማጣት በሚዲያ የሚደረጉ ነገሮች ለውጥ የሚያመጣ መሆኑን በቂ ግንዛቤ ማጣት ትችትን መፍራት አንዳንዴም የጋራ ቤት የዝብሪት ደጃፍ
ሳይዘጋ ይቀራል እንዲሉ ::

የሚዲያን ጥቅም ከኛ በላይ ሕወሓት በበለጠ ያውቃል ::

ለዚህ ነው የመብት ጠያቂ የስብዓዊ መብት ተከራካሪ ውድ ኢትዮጵያውያንን ሀገር ስትጠፋ እያየን ዝም አንልም ብለው የፃፈ የተናገረ ሁሉ ” አሸባሪ ” ታፔላ የሀሰት ክስ ተፈብርኮባቸው
እነ አንዱዓለም አራጌ
እስክንድር ነጋ እና ሌሎችም በሕይወት ቢኖሩም ደማቸው ተመጦ ሥጋቸውን ጨርሰው ነው የተፈቱት

ሕወሓት ሚዲያን ይፈራል ስለዚህ ነፃነት ፈላጊ ሀገሩን የሚናፍቅ ሁሉ በሚዲያው ዘርፍ መጠንከር ያለብን

ዲያስፖራው አንድ ተቋም ሊመስርት ችሏል ያም የኢሳት ሚዲያ ነው
ይሄን ሚዲያ ለመዝጋት ያለመታከት ጠላት እየስራ ነው

ኢሳትን ለማውረድ የሳተላይት ካንፓኒን በገንዘብ በማባበል ብቻ አይደለም እኛን መስለው የተቃዋሚ ተቃዋሚ አሉ በነዚህ በኩል የሚደረገው ፀረ ኢሳት ዘመቻ ቀላል አደለም
ከአሉባልታ እስከ ባይኮት መጥራት ተደርጏል በሌሎች አካባቢ ምን እንደሚደረግ ሙሉ ግንዛቤ ባይኖረኝም በምኖርበት ሀገር አንድነትን የሚጠሉ አላማቸው በውል የማይታወቅ በስመ አማራ እየታወክን ሰውን ግራ በማጋባት ስለ ሀገሩ መሳተፍ እንዳይችል በማድረግ ላይ ናቸው በአማራነቴ በማንነቴ ይሉሀል አማራ ናቸው ብለን ለመማመን ይከብዳል አብዛኛዎቹ ከሌላብሔር ውሁዳን ናቸው

ቢያንስ ከአንድ አያታቸው የሌላ ብሔር ቅይጥ ሁነው ስናይ አላማቸው ይበልጥ ግልፅ ይሆናል ::

ሚዲያው ላይ ትኩረት መሱጠት አለበት በሚዲያው ጫና መፍጠር ተችሏል ::
ራሳቸው የሕወሓት ሰዎች ሰለሕወሓትና ስለሀገር ሁኔታውን ለማወቅ የኢሳት ሚዲያ የማይጎበኝ የለም

መብት ጠያቂ ለስብዓዊ መብት ተከራካሪ
የመከራ መስቀል የግፍ ፅዋ የሚቀበሉት ለዚህ ነው

የበለጠ ማዋዕለ ንዋይ አፍሶ የሚዲያ ሠራዊት አሰማርቶ ያውም የውሸት ፕሮፓጋንዳ ሀሰትን ይዞ እኛን ጥግ ማስያዝ የተቻለው
በሚዲያ ላይ አንድነቱ ላይ ዋዛፈዛ የሚሰሩትን በአንድነት ኃይሉ ላይ ቀለም ቀቢዎችን በምንም ዓይነት አይቶ ማለፍ የለብንም
ብንችል በጋራ ገብተን በምንችለው ሁሉ እውነቱን ማሳየት ስደቡ እያልኩ አይደለም
የሀገር ጉዳይ አሳሳቧቸው ሁሉንም ትተው በትግል ላይ ያሉትን ሥራየ ብለው ጧትና ማታ የሚያጠለሹትን ዝም ማለት የለብንም

ዝምታ እንደ ማመን ይቆጠራልና

Image may contain: 1 person