አሁንስ ቀናሁኝ !!!

አሻግሬ እያየሁኝ

በቤቴ እሾክ አሜኬላ በቅሎብኝ
የእናቴን ጡት ሲነክሱብኝ
አው በቤቴ እሾህ አሜኬላ በቅሎብኝ
እነሆ አልቆም አልቀመጥ
አልራመድ አሮጥ
የውስጥ የእግር እሳት ሁኖብኝ
እንዳልናገረው ጉዱ የራሴ ሁኖብኝ
እህት ወንድሞቸም ጠሉኝ
ቀን ሲከፋ የአባት ውሻ ይናከሳል ሲሉኝ

አየሁት ደረስ ተረት እውነት
ወሬ ውሽት የሚሉት

መለየት አቅቶን ከወዳጅ ጠላትን
ግራ ተጋብተው ግራ ያገቡን

እነሆ የኔ የምለው
ደሜን የሚመልሰው
ዓይኔን ላፈር አለው
ያነ የኔው !
አወ የኔው !
ወንድም ጋሽ እኮ ነው
አወ የኔው
ቅቅቅቅቅ
አህያዋን ሲፈራ መደላሉን
የዝናብ ሱሪ እንቅፋቱን
ይህ የፈሪ ልጅ ሲፈራ ጊዜ
ያባቱን ገዳይ አረገው ሚዜ

ቀናሁኝ በጀግኖች
የሚያጠግብ ቂጣ ከጣዱ እንዲሉ
ድር ቢያብር
አንበሳ ያስር !!!!

Play
-4:49
Additional Visual Settings

Enter Watch And ScrollClick to enlarge

Mute