የእራሳችሁን ድክመት ለምን ወደ አርበኞች ግንቦት 7 ለከክ?
***
በቅርቡ የአውሮፓ ህብረት የአርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋን ጨምሮ እንዲሁም የሌሎች ድርጅት ተወካይ ግለሰቦች በተገኙበት በአውሮፓ ህብረት መቀመጫ በብራስልስ በወቅታዊው የኢትዮጵያ የፖለቲካ ትኩሳት እንዲሁም ስለመጻኤ የኢትዮጵያ ሁኔታ ምክክር ማድረጉ ይታወሳል።

ይሁን እንጂ ምክክሩን ተከትሎ የተለያዩ ስሞታዎች፣ሲልቁም ዘለፋዎች በአርበኞች ግንቦት 7 እና በድርጅቱ ሊቀ-መንበር ሲሰነዘሩ በማህበራዊ ሚዲያው እየተመለከትን ነው።
በዋነኝነት እነኝህ ዘለፋዎች ደግሞ የሚወረውሩት ጨዋውን ኢትዮጵያዊ የአማራውን ህዝብ እንወክላለን ከሚሉ ከጨዋነት ካፈነገጡ እና ከጽንፈኛ ግለሰቦች መሆኑን ልብ ይለዋል።

ሲጀመር ለእነኝህ ሰዎች የአማራው ህዝብ መቼ ነው “ተናገር በከንፈሬ፣እዘዝ በወንበሬ”ብሎ ውክልና የሰጣቸው?

ሲቀጥልም በአርበኞች ግንቦት 7 እና በድርጅቱ ሊቀ-መንበር ላይ የሚሰነዘረው ዘለፋ መሰርቱ ምንድነው? በተደረገው የምክክር መድረክ አርበኞች ግንቦት 7 ተጋባዥ እንጂ መቼ ጋባዥ ወይም አዘጋጅ ሆነ? አንተግባ አንተውጣ ብሎ የሚፈቅድበትም ሆነ የሚከለክልበት የመድረክ አጋፋሪነት ስልጣን የት አገኘ?

እነኝህ ዘላፊዎች በድርጅቱ ወስጥ ስንት የአማራ ተወላጆች፣ምርጥ ኢትዮጵያዊያን ጀግኖች መኖራቸውን እንደምን ዘነጉት? ታዲያ እነኝህ ጀግኖች የመጡበትን ማህበረሰብ “በጠላትነት” ከፈረጀ ድርጅት ጋር ምትክ የማይገኝላትን ይህወታቸውን ለመስጠት እንዴት ቆርጠው ተነሱ? እነ ገብርየን (ሻለቃ መሳፍት ጥጋቡ)፣እነ ብርሃኑ ጀግኔ፣እነ ደስታው ተገኘን…የመሳሰሉ ቆራጦች ለማን ብለው በጀግንነት ጥለው ወደቁት?

ይህን ነባራዊ ሃቅ ዘላፊዎቹ በምን አመክንዮ ነው፣ ብላሽ(ውድቅ) አድርገው የሚያሳዩኝ?

እንደምን እራሳቸውን ብቻ የአማራ አዳኝና ከገነቱ ቦታ አድራሽ መንገድ አድርገው አሰቡ? ከሆነስ ከገነቱ የሚያደርሰው መንገድ ወይም ሃሳብ የትኛው ነው? ወይም ስንት ነው? አማራን ለማዳን ስንት ድርጅት መሆን ያስፈልጋል?
መልሱን ለአንባቢዎች እና ለባለጉዳዮቹ ልተወው…

ይሁን እንጂ በዚህ ዘለፋና ስሞታ እነኝህ ግለሰቦች አርበኞች ግንቦት 7ን “አዋረድን” ብለው ግን የድርጅቱን ጥንካሬ እንዲሁም የድርጅቱን መሪ የፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋን ትልቅነት መስክረዋል።በአውሮፓ ህብረት ላይ መድረክ አዘጋጅቶ ድርጅቶችንም ይሁን ግለሰቦችን የመጋበዝ አቅም እንዳለው በተዘዋሪ መንገድም ቢሆን እየነገሩን ነው።

እኛም እንላለን አቦ ያድርግልን!! ያ…ኔ በአማራው ህዝብ ይሁን በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ያገባናል የሚሉትን ሁሉ ጠርተን እንመካከራለን።ይሁን እንጂ ዘሬም በራችን ክፍት ነው።አርበኞች ግንቦት 7 በአንድነት ትግል እና በአንድ አገር፣ኢትዮጵያ መቼም ቢሆን የማይናወጥ አቋም አለው።

ዛሬ ግን እኔ የምለው ለእናተ በመድረኩ አለመጋበዝ አርበኞች ግንቦት 7 ሳይሆን ተወቃሹና ተነቃሹ የእናተ ተስማምቶና ተግባብቶ ያለመስራት ብቻ ነው።ከራሳችሁ ጥቅምና ተድላ ይልቅ የህዝብ ቁስል እና መከራ አልታያችሁ ስላለ ብቻ ነው።

ታዲያ ጥሬው እውነት ይህ ሆኖ እያለ የራሳችሁን ድክመት ለምን ወደ አርበኞች ግንቦት 7 ለከክ??

በመጨረሻም ይህን እላለሁ፡-

አርበኞች ግንቦት 7 ወያኔን በሁለገብ ትግል አስወግዶ ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ለመፍጠር የሚሻገርበትን ድልድይ ለመበጠስ ከምታትሩ ምንአለ የራሳችሁን መንገድ ብትደለድሉ?

አበቃሁ

ያም አለ…ያም አለ. ..ኢትዮጵያ በልጆቿ መስዋእትነት ነጻ ትወጣለች!!

አንድነት ሃይል ነው!!

Image may contain: 5 people, people smiling, people standing and suit