አፄ ዮሐንስ (ጻድቁ)
የጎንደር ከተማን መናገሻ አርገው ኢትዮጵያን ከመሩ ነገሥታት መካከል ከ1660-1674 ዓ/ም የነገሡት ጻድቁ ዮሐንስ አንዱ ናቸው፡፡ እኚህ ንጉሥ በዘመናቸው መልካምና ለሰው ሁሉ አዛኝ ስለነበሩ ሕዝቡ ጻድቁ ዮሐንስ እያለ ይጠራቸው ነበር፡፡ ጻድቁ ዮሐንስ በንግሥና ጊዜያቸው የትዳር አጋራቸው የነበሩት እቴጌ ሰብለወንጌል እዛው በቤተመንግስት ውስጥ የንስሐ አባት ከነበሩት ቄስ ጋር የፍቅር ግንኙነት ጀመሩ፡፡ ታዲያ ከዕለታት በአንዱ ቀን ጻድቁ ዮሐንስ፣ እቴጌይቱና ንስሐ አባትዬው በአንድ ማዕድ ሆነው የዓሣ ወጥ እየተመገቡ ሳለ ጻድቁ ዮሐንስ ” አሁን ሁላችን እውነት ብንናገር ይህ ዓሣ ሕይወት ዘርቶ ይነሳል” አሉ እቴጌይቱም የጻድቁን ንግግር ተከትለው ከንስሐ አባታቸው ጋር በፍቅር መኖር እንደሚፈልጉ ተናገሩ፡፡ ጻድቁ ዮሐንስ ደግሞ “የዚህን ዓለም ትቼ እግዚአብሔርን ባገለግል ይሻላኛል” አሉ በዚህ ጊዜ በድስት ውስጥ የነበረው ዓሣ ሕይወት ዘርቶ ተንፈራፈረ ጻድቁ ዮሐንስም አሸከራቸውን ጠርተውት ዓሳውን ወደ ጣና ባሕር ወስደክ ጣለው አሉት፡፡ ይህንንም ተከትሎ ሕዝቡ እንዲህ ሲል ገጠመ፦
‘የደጉ ዮሐንስ ደግነት ቢነሳ፤
ዘሎ ባህር ገባ የተጠበሰ ዓሳ፡፡
ጻድቁ ዮሐንስ ዘውድ ይዞ ብቃት
ልብ አምላክን ሆነ ልክ ንደ’ ዳዊት፡፡’
ይህ በጻድቁ ዮሐንስ ዘመን ወደ ባሕር ተጥሎ የነበረ ዓሣ ተራብቶና በዝቶ እስከ አሁን ድረስ ዝርያው በጣና እንዳለ ይነገራል፡፡ መልኩም ነጭ ጅራቱም ቆራጣ የሆነ ነው ይባላል፡፡ ዓሳ አጥማጆች በመረባቸው የዚህን አይነቱን ዓሣ የያዙት እንደሆነ አይተው የጻድቁ ዮሐንስ ዓሣ በማለት ወደ ባሕሩ መልሰው ይጥሉታል እንጂ አይበልቱም፡፡ ምንአልባት አሁን ላይ ጣና አካባቢ ያላቹ ስለዚህ ስለ ጻድቁ ዓሣ የምታውቁት ነገር ካለ ብትካፍሉን ደስ ይለናል፡፡
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ታሪክ ከአጼ ልብነ ድንግል እስከ ቴዎድሮስ በተክለጻዲቅ መኩሪያ
– ንጉሥ አዕላፍ ሰገድ በሊቀኅሩያን ተግባሩ አዳነ፡፡
– ጎንደር የአፍሪካ መናገሻ በአሰግድ ተስፋዬ
በጻድቁ ዮሐንስ ዘመን ሰው ተበድሎ መከራ ቢደርስበት የሚነግርለት እንዳይጣ በሚል ንጉሡ በአደባባይ ላይ ደወል አሰቀሉ፤ ከዚያም የተበደለ ሁሉ ከአደባባዩ እየሄደ ደውሉን ሲደውል ደዋዩን እያስጠሩ በደሉን እየጠየቁ ይፈርዱለት ጀመር፡፡ ታዲያ አንድ ቀን እንደተለመደው ደወሉ ተደወለ ጻዲቁ ንጉሥ ዮሐንስም “ሂዱ ደዋዩን ይዛቹ ኑ” ሲሉ አዘዙ፤ የተላኩት ሰዎችም ሄደው ሲመጡ ባዳ እጃቸውን ተመለሱ በዚህ ጊዜ ንጉሡ ምነው ደዋዩስ የት አለ ሲሉ ጠየቁ ሰዎቹም “ንጉሥ ሆይ ደውሉን የደወለው ሰው አይድለም አንድ አህያ ደውሉ የተሰቀለበትን እንጨት ሲታከከው ነው ድምፅ የተሰማው” አሏቸው ንጉሡም መልሰው “ታዲያ እሱም ተበድሎ ይሆናል አምጡት እንጂ” አሉ አህያውም መጥቶ ንጉሡ ፊት ሲቀርብ ለካ የጨው ነጋዴ አህያ ኖሮ በቁስል ተመቶ ጀርባው ተገጥቦ አዩት ጻዲቁ ዮሐንስም “በሉ ከእኔ በቅሎ ጋር እሰሩት” ብለው ጥሬ እያበሉ ጨው እያስላሱ የአህያውን ገጣባ ቁስል አዳኑለት፡፡
#ምኒልክ ዳግማዊ ሰለሞን

Image may contain: sky, text, outdoor and nature