16266327_10208255989578471_6350131278561156780_n

ለኢትዮጵያውያን ግልፅ መልዕክት አለኝ
=========================

#በኢትዮጵያ ላይ ያለው አፈና የመብት ረገጣ በሁሉም ላይ መኖሩ የማይካድ ቢሆንም ተለይቶ ትኩረት ያልተሰጠበት ዕውነታ ከፊታችን እያየነው
ነገር ግን በድፍረት ልነንናገረው የማንፈልገው ለምን ይሆን? 16142283_10208258585603370_5991508113665286090_n
**************************************
ከሁሉም ኢትዮጵያውያን ተለይቶ #ፀላዒ የተባለ ሕዝብ አለ! !16195694_10208258585883377_5307942707066532147_n
#ፀላዒ ብቻም ሳይሆን በዘሩ ምክንያት #የተገደለ_የተፈናቀለ አለ! !!
አንድ ነገር መረሳት የሌለበት ጉዳይ አለ እሱም
የሕወሀትን ወይም tplf ሥም ማንሳት ተገቢ ይመስለኛል ምክንያት ለኢትዮጵያና ለሁሉም የኢትዮጵያ ሕዝብ መከራና ስቃይ የችግሩ መነሻና መድረሻ እሱው ሕወሀት ነው ።
በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ ሕወሀት በማኒፌስቶው ላይ ገና ከጅምሩ በረሃ ሲወርድ በፅሁፍ ያስቀመጠው መመሪያ አለው ።
ይህ መመሪያ የትግራይን ሕዝብ ነፃ አወጣለሁ ብሎ ነበረ አሁንም ለሩብ ምዕተ ዓመት ኢትዮጵያን እየገዛ ያን የመጀመሪያ ሥሙን tplf/ ሕወሀት =የትግሬ ነፃ አውጭ #የሚለውን ሳይቀይር ነው ።
##ሕወሀት / tplf የሚለውን ሥም አልቀየረም የትግሬ ነፃ አውጭ ከሆነ ትግራይ ነፃ የወጣችው ደርግ ከመውደቁ በፊት ነበር ለምን በዛን ወቅት የትግራይ ነፃነት አልታወጀም አሁንስ ማን ከለከለው ?
#የትግራይን ምድር ቀርቶ የተቀረውን የሀገሪቱን ጠቅላላ ምድሯን እና የሀገሪቱን ሀብት ከመዝረፍም ባሻገር የተወሰነ ወይም የተገደበ ብቻ ሳይሆን ለቀጣይ ዘመናት ወደፊት ለመቶ ዓመታት ትውልድ ከፍሎ የማይጨርሰው ዕዳ በኢትዮጵያ ሥም ተበድሯል አሁንም ይበደራል ።
የሀገርን #ዜግነት ትርጉም አልባ አድርጎ #ለባዕዳን ጥቅም ይቆማል ከኢትዮጵያውያን ይልቅ ለሶማልያና ለደቡብ ሱዳን ስደተኞች ቅድሚያ ይሰጣል ።
ለዜጎች በሀገር ቤትና እና ከሀገር ውጭም በስደት ለሚፈፀምባቸው ግፍ መቆሙ ይቅርና የአብዛኞዎቹን ግፍ አቀናባሪ የሚሆነው እራሱ ሕወሀት እንደሆነም ይታወቃል ።
#ሕወሀት ዜጎችን ራሱ በሚያስተዳድራት ሀገር ኢትዮጵያ ብቻ አይደለም እያንገላታና በደል እየፈፀመ ያለው ኢትዮጵያውያን በስደት ዓለም እንኳ በሰላም መኖር እንዳይችሉ በራሱ ሰዎች #በስደተኛ ሥም የተሰማሩ ሰላም በመንሳትና በመከፋፈል ላይ መሆኑን የለት ተዕለት የምናየው በመሆኑ አሊ የማይባል ሀቅ ነው ።
ይህን ችግር ከፊት ለፊት አውጥቶ መናገር ዘረኛ ሊያስብል ይችላል ወይ ?
*ወይስ አክራሪ ፖለቲከኛ ያስብላል ?
*ሕወሀት መንግሥት ነኝ እያለ ሀላፊነት በጎደለ መልኩ ከሚተገብራቸው ተግዳሮት አንፃር አኳያ ሲታይ ሕወሀት መንግሥት ነው? ወደሚል ድምዳሜ ያደርሰናል ።
በዚህ ላይ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ማወቅ ያለበት አንድ ደረቅ ሀቅ አለ! !!!
#ሕዝባዊ ወያነ ሀርነት ትግራይ ሕወሀት/ tplf አማራ የትግሬ ጠላት ነው ብሏል።
* አሁንም ይላል ።
#ሕወሀት አማራ ጠላት ነው በማለት ብቻ አልተገታም ሥልጣን በወጣ ማግሥት ጀምሮ በአማረኛው ተናጋሪ ሕብረተ ሰብ ላይ ሕወሀት በራሱ አቀናባሪነት እና ባሰለጠናቸው የጎሳ ካድሬዎቹ አማካኝነት ከእስላማዊው ዓለም ዓቀፍ አሸባሪ iss በበለጠ እንዲያውም ቀድሞ የመጣ ከአይሲስም በላይ #በ21ኛውክ/ ዘ :
*ቀድሞ የመጣ ዘግናኝ ግድያ በአማራው ላይ ፈፅሟል አስፈፅሟልሸ።
ይህን በአማራው ሕዝብ ላይ የታወጀበትን አማራ የትግሬ ጠላት የተባለበትን እና በአማራው ላይ ከ40 ዘመን በላይ የተፈፀመበትን በደል የዘር ማፅዳት ተግባር ሁሉም ኢትዮጵያዊ እውቅና ሊሰጠው ይገባል ።
#አማራ ይህን የዘር ማፅዳት ግፍ ለመቋቋም በአማራነቱ ቢደራጅ ማንም የሚቃወም መሆን የለበትም ምክንያት አማራ ከዘሩ ይልቅ በኢትዮጵያዊነቱ ማንም የሚጠረጥረው አይሆንም ።
#የትግሬው ነፃ አውጭ ነኝ ባዩ ሕወሀት አማራን ማጥፋት አለብኝ ብሎ የተነሳው እውነት የአማራው ሕዝብ#ተከዜን ተሻግሮ በትግሬ ሕዝብ ላይ የፈፀመው አንድም የሠራው ኃጢአት የለም ።
#ኢትዮጵያን አጥፍቶ የወደፊቷን ታላቋን( አባይ ትግራይን) ታላቅ #ኢምፓየር በአፍሪቃ ቀንድ ለመመሥረት ሲባል ኢትዮጵያ ትፍረስ ለዚህ ስኬትም በቅድሚያ አማራው መወገድ አለበት ብሎ ያምናል።
* ለተግባራዊነቱ በትጋት በተግባር ላይ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል ።
#ግን በአሁኑ ሰዓት አማራን እናደራጅ አማራን ልንገነጥል ነው እያሉ በሌላ መልኩ አማራ በደሉን ግፉን ጩኸቱን እንዳያሰማ ከሌሎች ወገኑም ሆነ ከአጎራባች አገሮች ጋር አብሮ እንዳይሰራ መሰናክል እየፈጠሩ ያሉት እኒህ የአማራ ተወካይ ነን የሚሉት ለአማራው የአልሞት ባይ ትግል የሚያግዙት ሳይሆኑ በአማራው ሥም የተመደቡ የሕወሀት ሰዎች ዳግማዊ #ብአዴኖች ናቸው አንዳንድ ቢኖሩም ነገሩ ያልገባቸው በየዋህነት የተቀላቀሉ ናቸው ብየ አምናለሁ ።
ድል ለግፉዓን! !!!!!
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር
#እሸቱ

Image may contain: text