ህወሃት የሸጣት አሰብ በዱባይ እጅ ልትገባ ነው

ሥራ ያጣ መነኩሴ ቆቡን ቀዶ ይሰፋል
ስለአሰብ ወደብ እንቅልፍ ያጣው ኢትዮጵያዊ 16195168_10208276694696086_2894485667597258221_nErmias Tokuma Alemayehu
ህወሃት የሸጣት አሰብ በዱባይ እጅ ልትገባ ነው
ኢትዮጵያውያን ሕወኃትን ከሥልጣን ካስወገድን በዃላ በቀላሉ በዲፕሎማሲ አልያም በሀይልም ቢሆን ከሻእቢያ መልሰን እንቀበላለን ብለን የነበርነውን ህጋዊ የአሰብ መሬታችንን የሻአቢያው መሪ ኢሣያስ አፈወርቂ ለዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ ለ30 አመት በሊዝ ለመሸጥ ተስማምቷል፤ ሻአቢያ በዚህ ስምምነት በርካታ ቢሊየን ዶላር ወደካዝናው የሚከት ሲሆን በአንፃሩ የቀድሞ የኢትዮጵያ መንግሥታት ገንብተውለት ምንም ማሻሻያ ያላደረገበትና ያረጀው የአስመራ አየርመንገድ በዱባዮች ወደዘመናዊነት እንደሚቀየር ተነግሮታል። የህወሃቱ አሻንጉሊት ሐይለማሪያም ደሳለኝ የሻአቢያ እና የህወሃት ድራማውን ሳያውቅ አሰብን የኢትዮጵያ ነች ብሎ ሣይሆን ሻአቢያ የሚያገኘው ጥቅም አሳስቦኛል በየአረብ ሀገራቱ ቤተመንግሥት ደጅ እየጠና ይገኛል።
የዱባዩ ሚሊታሪ ቤዝ በአሰብ ከተገነባ በዃላ ሕወሃትን አስወግደን የአሰብ ወደብን የኢትዮጵያ ለማድረግ ብንሞክር እንኳን ፈተናው እጅግ ከባድ በመሆኑ በተለያዩ የአለም ሀገራት የምንገኝ ኢትዮጵያውያን ለተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሀፊ ድምፃችንን ልናሰማ ይገባል። የአረቦች ወታደራዊ አቅም መጠናከር የሚያሳስባት አሜሪካ ከኢትዮጵያውን ጥያቄ ጎን እንደምትሰለፍ ምንም አይነት ጥርጥር የለኝም። አምባገነኖቹ ኢሳያስና መለስ ኢትዮጵያን ለማዳከም አሰብን ከኢትዮጵያ መነጠላቸው ይታወቃል እነርሱ የታሪክ ዲቃላዎች ናቸው እኛ የዚህ ዘመን ወጣቶች የአሰብ ወደብ ተላልፎ ለዱባይ ሲሰጥ ከመመልከት በላይ አሣፋሪ ነገር የለም። የፖለቲካ ፓርቲዎች ለአለም አቀፍ ተቋማት ጉዳዩን የሚገልጽ ደብዳቤ ሊፅፋ ይገባል፤ በአውሮፓ እና አሜሪካ ሰፋፊ ሰላማዊ ሰልፎች ሊካሄዱ ይገባል።
#ኤርሚያስ_ቶኩማ