yager-bet-tzta

በዚህ ፎቶ ግራፍ የምታዩት ምስል ወደኋላ ብዙ አማታት መልሶ የልጅነት አብሮ አደጎቸን የገጠሯን መንደሬን እት አበባዬን አስታወሰኝ
እኔን ሁናችሁ ይህን የሀገር ቤት ትዝታ ለምትጋሩኝ ሁሉ ቻል አድርጉት ያ የወርቃማው ዘመን አሁን ላይማሰቡ ትዝታም ብቻ ሳይሆን ቁጭትም እንዳያጭርባች ሥጋቱ አለኝ
አሁን ላይ በሀገር በቀል ወራሪዎች አማራ ተብለው ከአያት ከቅድመ ዓያት ጀምረው ከኖሩበት ቀየ መፈናቀል ብቻ ሳይሆን ግድያም ሲፈፀምባቸው እያየን እየሰማን ምንም አለማድረጋችን አሳዛኝ ነው የእህት አበባ እጅ ዛሬ እንደድሮው ረሀቤን ተቆጭው ልላት አልችልም የነበራትን ሁሉ አጥታለችና