Truneh Yirga

ወጣቱ አርበኛ ሞላአጃው ሙላው፥

15202628_351282398557767_6993298180837023750_nአርማጭሆ ላይ የተሰዋው ወጣት ሞላጃዉ ሙላው። ከረጅም ዘመን በኋላ ስለሱ የሰማሁትና ያየሁት ከቀናት በፊት ከመንግስት ጋር ውጊያ የሚያደርጉ አባላት ተብሎ በፌስቡክ በተለቀቀ ቪዲዮ ላይ ነው፡፡

ያ ቪዲዮ ለእኔ ለግድያ እንደቀረበ ማስታዎቂያ ነበር።

ጊዜዉ በጣም ሩቅ ነው…….፡፡
በሰሜን ጎንደር ዞን ማስሮደንብ በተባለች ቦታ ከ አንዲት ጠላ ሻጭ ጎጆ ዉስጥ አንድ ህጻን ተወለደ፡፡
እንደሌሎች ህጻናት አባቱ አቅፎ ሳይስመዉ በምስኪን እናቱ ድጋፍ ብቻ ሲያገኝ እየበላ ሲያጣ ጾም እያደረ የሂወትን ጉዞ ተያያዘዉ፡፡
ትንሽ አደግ ሲልም ከትምህርቱ ጎን ለጎን ፀጉር በማትካክል እናቱንና ራሱን መደጎም ጀመረ፡፡ ያ በትምህርቱ ብርቱ አመለ ሸጋና ተወዳጅ ልጅ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህረቱን አጠናቆ ምስኪን እናቱንና የትውልድ ቀየውን ለቆ ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ወደ ሳንጃ አቀና፡፡
ያ ነገን የተሻለ ለማድረግ በትምህርቱ የበረታዉ……የዛሬ ኑሮዉን ቀዳዳ ለመድፈን ደፋ ቀና የሚለዉ ታዳጊ
ከስሙ በቀር አይኑን አይቶት የማያዉቀዉ አባቱ ጦስ ሳንጃ ላይ ሌላ ፈተና ገጠመዉ፡፡

ነገሩ እንዲህ ነዉ፡፡
አባቱ ከመንግስት ጋር በነበረዉ ቅሬታ በርሀ ይወርዳል፡፡
ከአስራ አራት አመታት ቆይታ በሁዋላ በምህረት ለመመለስ አማላጅ ይልካል፡፡
መልእክተኛዉ ታዲያ ያ በመንግስት ተፈላጊ የሆነዉን ሽፍታ (ከፋኝ በመባል የሚታወቅ የአርበኞች ቡድን መስራች ) ለማስረከብ ይደራደራል፡፡
በርካታ ወታደሮችን አስከትሎ በርሃ ይወርዳል፡፡ ያሰበዉንም አደረገ፡፡
ይሁን እንጅ አረበኛዉ በቀላሉ እጁን አልሰጠም፡፡ የሚገለዉን ገሎ ደመኛዉን ተናግሮ አለፈ (ራሱን አጠፋ)፡፡
ያ ያባቱ ገዳይ የምስኪኑን ተማሪ ሳንጃ መግባት ሲሰማ ሳይቀድመው ለመቅደም ያሳድደዉ ጀመር፡፡ ማሳደድ ብቻም አይደለም በአደባባይ ሁለት ጥይት ተኩሶ ሳተዉ፡፡ ሁኔታዉ ያስደነገጠዉ ታዳጊ ተስፋ ያደረገበትን ትምህርት ተስናብቶ ጎንደር ከተማ ገባ፡፡
የምስኪን እናቱ ተስፋ መጨናገፍ፣ ተስፋ ያደረገበት የነገ ሂዎቱ መሰረት ይሆንኛል ያለው የትምህርቱ መቋረጥ፣ በማያዉቀዉ አባቱ ጦስ መሳደዱ፣ የ አባቱ ደም ረፍት ንሱት፡፡ እናም እሱም እነዳባቱ በርሃ ወረደ፡፡
ሞላጃዉ ሙላዉ፡፡
ያች በባዶ ቤት ያሳደገችዉ እናቱ ያንጊዜ ነበር የለጇን መጨረሻ ያወቀችዉ፡፡ ጨረቋን ጥላ ሄደች፡፡ አበደች፡፡ ያ በ ባዶ ቤት አንጀትዋን አስራ ያሳደገችው ልጅ…….ያ የችግሬ ማብቂያ፣
የርሃቤ ፍጻሜ ይሆናል ብላ ትስፋ የጣለችበት ልጇ ከአይኗ ተሰወረ፡፡
የእናቱን መታመም የሰማዉ ሞላጃዉ በምህረት ተመልሶ ገባ፡፡ የተወሰነ ጊዜ ታሰሮ ተፈታና ወደቀደሞ ሂዎቱ ተመለሰ፡፡ ይሁንእንጅ ከቀድሞ ታሪኩ ጋር በተያያዘ መስራትም መማርም አልቻለም፡፡ 15178189_351282415224432_8043490465879028331_n
ርሀቡ ጠናበት፡፡ ችግር እጣ ፋንታው ይመስል እየተከተለ መድረሻ አሳጣዉ፡፡ የእልት ጉረሱ ሸፋኝ አብሮ አደግ ጓደኞቹ ሆኑ፡፡
በዚህ ጊዜ ነበር ከሞላጃዉ ጋር መደዋወል የጀመርነው፡፡
ለእለት ጉርሱ ከመደጎም ይልቅ የተረጋጋ ሂወት እንዲኖርዉ ተወያየን፡፡ ስራም ጀመረ፡፡
ከጥቂት ጊዜ በኋላ ስራዉን ትቶ መሄዱን ሰማሁ፡፡
ከዛም መታስሩን እና ቆይቶም ከ እስር ቤት ማምለጡን ሰማሁ፡፡
ከዛ በኋላ ስለሞላጃዉ የሰማሁትና ያየሁት ከቀናት በፊት በፌስቡክ ነዉ፡፡
ከመንግስት ጋር ውጊያ የሚያደርጉ አባላት ተብሎ ቬዲዮ ተለቋል፡፡
ለእኔ ያ ቪዲዮ ለግድያ እንደቀረበ ማስታዎቂያ ነበር የተሰማኝ፡፡
እንዲህ በቅርቡ ይሆናል ባልልም፤ አልቀረም ሆነ ሞላአጃው ሙላው ተገደለ፡፡
የዛሬ ማለዳ የኢሳት ዜና የወንድሜን መጨረሻ አረዳኝ፡፡
ነብስ ይማር ሞላጃዉ፡፡
ያች ምስኪን እናትህ እንዴት ሁና ይሆን?

ምንጭ

Truneh Yirga