ከፀረ አማራው ትግሬ ለመላቀቅ የሞት ሽረት ትግል ማድረግ የግድ ነው ።
እስከመቸ ሙታንን አያዘከርን?download
በቃ ትግሎ ተጀምሯል ሞት የማይፈራ ወጥት ተፈጥሯል ሁላችንም ትንሽ ትልቅ ሳንል እሴት ወንድ ሳንል በሀገር ቤት ያለህ ከሀገር ውጭም ያለህ የአማራን ዘር ከጥፋት መለመታደግ ሆ ብለን ለመነሳት ጊዜው አሁን ነው ።
እገሌ ከገሌ እያልን የኋሊት እንደ አህያ ለመራገጥ የሚያስቡ በካከላችን የህውሀት ሰርጎ ገቦችንም በንቃት ልንከታተላቸው ይገባል ከመሀከላችን ሁነው የሚያፋልሱን ከማንኛውም ድርጅት ጋር ፀረ ትግሬ ሕውሓት ከሆነ ከኢዮር ሰማይ የወደቀው ሳጥናኤልም ቢሆን አብረን እንድንሰራ የግድ ይለናል እገሌ መሌ የሚሉን አንሰማም ሀቁን ልንነግራቸው ይገባል ለአማራ በዚህ ምድር ላይ ከትግረፀው ነፃ አውጭ ነኝ ከሚለው በስተቀር ማንም ምንም ጠላት የለንም አሰፋ  ማሩ
~~~~~~~~~~////////~~~~~
ምስጋና #ለጋዜጠኛ_ሙሉቀን_ተስፋው

ቀዳሚ ሰማዕት ሌ/ኮሎኔል ገናናው ሽፈራው፤ እንዲያቆጠቁጥ የማያስፈልግ ዛፍ

(ለመማሪያ ይሆን ዘንድ የቀዳሚ ሰማዕት ሌ/ኮሎኔል ገናናው ሽፈራው ታሪክ ከዚህ ቀጥሎ ቀርቧል፤ የዐማራ ሕዝብ ቀዳሚ ሰማዕታቱን እያሰበ ከባለፈው ስሕተት እየተማረ በወያኔ እንዳይሸወድ ይህን ታሪክ ማቅረቡ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡)
ሌተናል ኮሎኔል ገናናው ሽፈራው ይባላል፤ ተወልዶ ያደገው በ1950 ዓ.ም. በደንቢያ ወረዳ የጣና ሐይቅን ተንተርሳ በከተመችው የጎርጎራ ከተማ ነው፡፡ ስምን መላክ ያወጠዋል እንዲሉ የገናናው ሽፈራው ታሪክ የገነነ ነበር፡፡
1970ዎቹ ለዐማራ ወጣቶች የፍስሃ ዘመን አልነበረም፡፡ በቀይና ነጭ ሽብር ወንዶች ሁሉ አልቀው ነበር፡፡ በዚያ ዘመን ወጣት ሆኖ መገኘት ለቀይ ሽብር ሞት ብቁ ያደርጋል፡፡ ወጣቶች ከዚህ አስከፊ መቅሰፍት ለመዳን ሁለት አማራጭ ነበራቸው፡፡ አንደኛው አገርን ጥሎ መሰደድ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የብሔራዊ ውትድርናን መቀላለቀል፡፡ ከዚያን ዘመን ጀምሮ እሳካሁን የዐማራ እናቶች የሚወልዷቸው ወንዶች ለከርሳሟ መሬት ቀለብ የሚሆኑትን ነው፡፡
ገናናው አገርን ጥሎ መሔድ አልፈለገም፤ በ1970 ዓ.ም. በ20 ዓመቱ የሁለታ የጦር መኮነኖች ማሰልጠኛ ማዕከል ተገኘ- ገናናው፡፡ የመኮነንነት ሥልጠናውን እንደጨረሰ እረፍት አላደረገም፡፡ በኦጋዴን በርሃ፤ ከሲያድ ባሬ ጦር ጋር ፊት ለፊት ተጋፈጠ፡፡ የውትድርና ጀብደኝነቱን አስመሰከረ፡፡ ያኔ ከቀብሪ ደሃር እስከ ድሬደዋ፤ ከሞቃዲሾ እስከ ቦሳሶ እና ሀርጌሳ ድረስ የገናናው ስም ገነነ፡፡ በዚያን ዘመን ከነበሩ የሶማሌ ወታደሮች በስም ማንን ታውቃላችሁ የሚል ጥያቄ ቢቀርብላቸው ከኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስና ሌ/ኮሎኔል ገናናው ሽፈራውን እንደሚሉ ጥርጥር የለውም፡፡ ገናናው የሶማሌ ጦር ሲበታተን የአገር ገንጣይ ቡድኖችን ለመወጋት እንደገና በ609ኛ ኮር የዘመቻ መኮንን ሆኖ በ1974 ዓ.ም. ወደ ሰሜን አቀና፡፡ ከወያኔና ከሻቢያ ሽፍቶች ጋር በአዋጊነትና ተወጋኒት ተሰለፈ፡፡
ያኔ፤ ከሌ/ኮሎኔል ገናናው ጋር የጽሑፍ ዛር የሰፈረበት ሰው አብሮት ቢኖር ኖሮ ብዙ ገጽ ያለው ጥራዝ ማዘጋጀት በቻለ ነበር፤ የኤርትራ መሬት የበላው ስጋ፤ የኤርትራ ጋራዎች የጠጡት የሰው ደም፤ የናቅፋ የጦር ንድፍና ፍጻሜ፤… ወዘተ ወዘተ ሁሉ ቢጻፍ ኖሮ ከታሪክ ማስታዎሻነት ባሻገር ለዛሬ መማሪያነት ያገለግል ነበር፡፡
የሻቢያና የወያኔ ጦር አዲስ አበባን በ1983 ዓ.ም. ሲቆጣጠሩ የቀድሞው ጦር ‹‹ብረት አውርድ›› የሚል ስምምነት ሲደርግ ሌ/ኮሎኔል ገናናው ሽፈራው የአገር ትርጉም በማይገባቸው ሰዎች እጅ አገር ስትገባ ዝም ብሎ መቀመጥ አልፈለገም፡፡ የሚመራውን ጦር ይዞ ወደ ሱዳን ተሰደደ፡፡ በልጅነቱ የጠላው ስደት በዚህ ሰዐት ከፊቱ ተደቀነበት፡፡ ከኤርትራ እስከ ሱዳን በርሃዎች ያደረገው አስቀያሚ ጉዞ አማልክት ካልሆኑ በስተቀር የሰው ልጅ ያን ሁሉ ነገር አይቶ መዘገብ አይቻለውም፡፡ ያ ሁሉ ወታደር በውሃ ጥም በበርሃ አሸዋ ላይ ወድቆ ሲቀር፣ ስጋውን አሞራ ሲበላው፤ ከሰው ሕይወት ይልቅ እጣት ላይ ያለ ወርቅ ዋጋ ሲኖረው፤ እጅ ላይ የታሠረ ዲስኮ ሰዐት ሲቀማ፤ ሕይወት ውሸት ሲሆን የገናናው ሕሊና መታወኩ አልቀረም፡፡
ካርቱም በነበረበት ጊዜም ሌ/ኮ ገናናው ዝምታን አልመረጠም፡፡ በየቦታው የሚረግፈውን የቀድሞ ጦር ለማገዝና ለማሰባሰብ የሚችለውን አድርጓል፡፡ የገናናው ዕቅድ ወደ ሁለተኛ አገር በመሔድ የወገኑን ችግርና ሰቆቃ ማሰማት ነበር፡፡ ግን ነገሮች በአሰቡት መልኩ አልሔዱም፡፡ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከወያኔ ጋር አስታርቆ ወደ አገሩ እንዲመለስ አደረገው፡፡ ሌ/ኮ ገናናው አዲስ አበባ እንደ ደረሰ ወደ ጦላይ የጦር ትምህርት ቤት ተወስዶ ‹‹የተሀድሶ ኮርስ›› እንዲከታተል ተደረገ፡፡ በኋላም ነጻ ተባለና ወጣ፡፡
የገናናው አባት አቶ ሽፈራው ረዳት የላቸውም፡፡ ገናናው ከተሀድሶ እንደወጣ ወደ አባቱ እንደ አሞራ ሲከንፍ ቆላ ድባ፣ ደንቢያ ደረሰ፡፡ ብቸኛ አባቱ ልጃቸውን ሲያገኙ ደስ አላቸው፡፡ ገናናው ከቤት አይወጣም፤ አባቱን ያግዛል፤ ከአባቱ ጋር ብቻ ይጫዎታል፡፡ የኢትዮጵያ አንድነት እጅግ ቢያሳስበውም፤ የጦር ጓደቹ ሕይወት ቢያሳዝነውም ጊዜው ለወንበዴዎች በመሆኑ በአርምሞ መልከትን ይመርጥ ነበር፡፡ ግን ወያኔዎች የሚፈሩትን የዐማራ ቆራጥ ጀግና ቢፈቱትም ከመከታተል ግን አልቦዘኑም፡፡ አልፎ አልፎ ከአልጌና የጦር ግንባር የሚያውቀው ሰው እየመጣ ስለአለው ችግር ያወጋው ነበር፡፡ ከወያኔ የተላከ ሰላይ መሆኑን ግን የጠረጠረ አይመስለኝም፡፡
ነሐሴ 08 ቀን 1984 ዓ.ም. ምሽት 4፡30 ላይ የነ አቶ ሽፈራው ቤት በወያኔ ወታደሮች ተከበበ፡፡ ሌ/ኮ ገናናው ምንድን ነው ነገሩ በማለት በር ከፍቶ ሲወጣ የወያኔ ወታደሮች እጅ ወደ ላይ አሉት፡፡ የጣና ሐይቅ በታዛቢት ዝም ብሎ ይመለከት ነበር፡፡ ጎረቤት ሰተበሰበ፡፡ በቀይ ሽብር ጀግኖች ሁሉ አልቀው ስለነበር የወያኔ ወታደሮችን ለምን ብሎ የተዋጋ ሰው አልነበረም፡፡ ስንቱ የደንቢያ ወጣት እንዳለቀ የስላሴን ዋሻ ያየ ያውቀዋል፡፡
የገናናው የግል ንብረቶችና ሰነዶች ተለቅመው አብረውት ወደ ቆላ ድባ ተወሰዱ፡፡ በቀጣዩ ቅዳሜ ማለዳ ወደ ጎንደር ወስደው በቀድሞው ኮሚሳሪያት ጽ/ቤት ውስጥ አሸጉት፡፡ ብርድ ልብስና ጫማ ለመስጠት የሔዱ ዘመዶቹ በእርቀት አዩት፡፡ እንዲያነጋግሩት አልተፈቀደላቸውም፡፡ በኦጋዴን በርሃ ጀብድ የሠራው ጀግና፣ የኤርትራንና የሱዳን በርሃዎችን የቆራረጠው ቆፍጣና በወያኔዎች እጅ መውደቁ ሞራሉን ጎድቶታል፡፡ ተስፋ መቁረጥና ንዴት፣ የጀግንነትና የምንምነት ስሜት በገጹ ላይ ይነበባል፡፡ ያች ቀን ለመጨረሻ ጊዜ ዘመዶቹን ያየባት፣ ዘመዶቹም እሱን ያዩበት ጊዜ ናት፡፡ የጣና ሐይቅ አድባራት፣ የሥላሴ ዋሻ ዛር፣ የደብረሲና ማርያም ይህ እንደሚመጣ አልተናገሩም፡፡ ግን የሆነው ያ ነበር፡፡
ሰኞ የገናናው አብሮ አደግ ጓደኛ የሆነች ሴት ምሳ ልታቀብለው ወደ ታሰረበት ጎረኖ ሔደች፤ አላገኘችውም፡፡ ከሌሎች ታሳሪዎች ጋር ለምርመራ ሌላ ቦታ ሒዷል አሏት፡፡ ቤተሰብ ደጋግሞ ጠየቅ፤ ገናናው የለም ተባለና ፋይሉ ተዘጋ፡፡ አቶ ሽፈራው እንደሞተ የቆጠሩትን ልጅ ሲያገኙ እንዳልተደሰቱ ሁሉ እንደገና ሲነጠቁ ሐዘናቸው በረታ፡፡ ጠዋት ጠዋት ጣና ሐይቅ ዳር እየተቀመጡ እንባ ያፈሳሉ፡፡ የጣና ሐይቅን የእሳቸው እንባ ግን አላጎሸውም፡፡ ደብረ ሲና በመሔድ በባለቤታቸው መቃብር ላይ ትሰማቸው ይመስል ‹‹ልጃችን ጉድ ሰራኝ፣ ትቶኝ ሔደ እኮ›› እያሉ ይነግሯታል፡፡ በእርጅና ዘመን ‹‹ልጄ ልጄ›› ማለት የደረሰበት ያውቀዋል፡፡
ከዕለታት አንድ ቀን ያች ስንቅ ለማቀብል ስትደክም የነበረች አብሮ አደግ ጓደኛው ወደ ታሰረበት ቦታ በመሔድ የጥበቃ ሠራተኛውን ‹‹እባክ የገናናውን መዳረሻ ንገረኝ›› አለችው፤ ‹‹አንድ ዛፍ ያድጋል፤ ይቆረጣል፡፡ እንደገና ሲያቆጠቁጥ ደግሞ ይቆረጣል፤ ምክንያቱም እንዲያድግ ስለማያስፈልግ›› አላት፡፡ ደነቀጠች፡፡ ተገደለ ማለት ነው? ሰማይ ምድሩ ዞረባት፡፡ አፍና ያዘችው፡፡
በዓመቱ ነሐሴ 13 ቀን 1985 ዓ.ም. ሽማግሌው ምስኪን አባት ወደ ጎንደር ሒደው እዚያ ዘመድ ቤት እንዲያድሩ ይነገራቸዋል፡፡ ዕለቱ ረቡዕ ነበር፡፡ አባትም ያንን አደረጉ፡፡ የወያኔ ወታደሮች ሌሊት መጥተው ‹‹ልጅዎት ታስሮ በነበረበት ቤት ራሱን ስላጠፋ አስከሬኑን አዘዞ የጦር ካምፕ ሒደው መውሰድ ይችላሉ! ለማንም ግን መናገር የለብዎትም›› ከሚል ማስጠንቀቂያ ጋር መርዶ ተነገራቸው፡፡
አባት በድንጋጤ ወደቁ፤ ከዚያ የሆነው ለወሬ አይመችም፡፡ እርር አሉ፡፡ በሐዘን ተኮራመቱ፡፡ የሚናገሩትን አያዉቁም፡፡ እንባቸው ፈሰሰ፤ ልሳናቸው ተዘጋ፡፡ ሰው ከሟች ይልቅ ስለ አባት አነባ፡፡ ነሐሴ 14 ቀን 1985 ዓ.ም. አዘዞ የጦር ካምፕ በሳጥን የታሸገውን አስከሬን ይረከቡ ተባሉ፡፡
ሳጥኑ ሲከፈት የጀግናው አስከሬን ጠረኑ ለውጦ ተጋድሟል፡፡ ከአንድ ዓመት ስቅይት በኋላ የተገደለው ሌተናል ኮሎኔል አስከሬን ምርምራ አልተደረገለትም፡፡ የገናናው አጽም ደብረ ሲና ገዳም ከእናቱ ጎን አረፈ፡፡

ማስታወሻ፤ ይህ ጽሑፍ የተዘጋጀው በግንቦት 1986 ዓ.ም. በሙዳይ መጽሔት ስለ ሌ/ኮ ገናናው የታተመውን ግለ ታሪክ መሠረት በማድረግ ሲሆን አንዳንድ ሰዎችን በመጠየቅ የበለጠ ዳብሯል፡፡ መጽሔቱን ያደረሱኝ የሁልጊዜ ተባባሪየ ዶክተር አሰፋ ነጋሽ ናቸው፡፡

Eshete Kassa Zewudie's photo.