የጎሳ ፌዴራሊዝም፤ የአማራው ጎሳ የጅምላ መፈናቀልና አማራውን ለማጥፋት የሚደረገው ስልታዊ የወያኔ ትግሬዎች ዘመቻ – አሰፋ ነጋሽ * (ሆላንድ – ጥቅምት 2006 ዓ. ም)

ክፍል አንድ

የወያኔ ትግሬዎችና ስለ አማራ ህዝብ ያላቸው ግንዛቤና የቆየ ጥላቻ ምን ይመስላል?  Read In PDF …

Amhara-People-in-Benshangul-Kilil

የወያኔ ሃርነት ትግራይ መሪዎችም ሆኑ ተከታዮቻቸው የትጥቅ ትግላቸውን ሲጀምሩ ለትግራይ ህዝብ ችግርና ኋላ ቀርነት ተጠያቂዎቹ ከዳግማዊ ዐጼ ምንሊክ ጀምሮ እስከ ደርግ መውደቅ ድረስ በስልጣን ላይ የነበሩት ወያኔ አማራ ብሎ የሚጠራቸው መንግስታት እንደ ነበሩ በፖለቲካ ፕሮግራም ደረጃ ቀርጸው የትግራይን ህዝብ እንዳስተማሩ ቀድሞ የወያኔ ድርጅት አባል የነበረውና ዛሬ በስደት በሚኖርበት አስውስትራሊያ ሆኖ የወያኔን እኩይ ዓላማ በቆራጥነትና በሃቅ እያጋለጠ ያለው አቶ ገብረ መድህን ዓርዓያ በቅርቡ “እነማን ነበሩ” በሚል ርእስ በመረጃ አስደግፎ አሳውቆናአል። የወያኔ ድርጅት የአማራው ህዝብ በእነዚህ የአማራ መንግስታት ብሎ በሚጠራቸው ከዐጼ ምንሊክ እስከ ደርግ መውደቅ ድረስ በነበሩት መንግስታት ዋነኛ ተጠቃሚ እንደነበረና የእነዚህም መንግስታት የስልጣን መሰረት እንደ ነበረ ሲያስተምር ቆይቶአል፤ ዛሬም ይህንኑ እያደረገ ነው ያለው። በዚህ ዓይነት የአማራን ህዝብ የእነዚህ ያለፉት መንግስታት የስልጣን መሰረት ነው በማለት ወያኔ የአማራውን ህዝብ ሲፈርጅ ቆይቶአል። የወያኔ ትግሬ መሪዎች የትግራይ ህዝብ ዐጼ ምንሊክን በመሳሰሉት የአማራ ተወላጆች የሆኑ የኢትዮጵያ መሪዎች እንደ ኢትዮጵያዊ እንደማይታይ ለትግራይ ህዝብ ያስተምሩ ነበር። እነዚህም የትግራይን ህዝብ እንደ ኢትዮጵያዊ የማይቆጥሩ የአማራ መሪዎች የትግራይን ህዝብ ሆን ብለው እንዴት ለችግር፤ ለጎስቁልናና ለእንግልት እንዳበቁት የወያኔ ድርጅት መሪዎች (ዛሬ በስልጣን ላይ ያሉትም ሆኑ ድርጅቱን ጥለው በመውጣት ዛሬ ተቃዋሚ ነን ብለው የዛሬው የትግራይ ህዝብ ሰቆቃ ከደርግ ጊዜው የባሰ ነው ብለው የሚነግሩን ጭምር) በሰፊው አስተምረዋል። እንግዲህ የወያኔ መሪዎች የአማራ ንጉስ ብለው በሰየሟቸው በዐጼ ምንሊክ ተጀመረ ያሉት የትግሬዎች ጭቆና ተከታዮቻቸው ናቸው በሚሏቸው የዐጼ ሃይለ ስላሴና የደርግ መንግስታትም ዘመን ቀጥሎ የትግራይ ህዝብ በመጨረሻ ተማሮ “የአማራውን የደርግ” መንግስት ለመጣል እንደ ተነሳ እንረዳለን። የወያኔ መሪዎች የትግራይን ህዝብ ችግር የአማራ ተወላጆች በሚላቸው የኢትዮጵያ መሪዎች እንደተፈጠረ አድርገው እንዴት እንደሚያዩና እንደሚቀሰቅሱ ሩቅ ሳንሄድ እዚሁ እኔ በምኖርበት በሆላንድ ሀገር በስደት የሚኖረው የቀድሞው የወያኔ ድርጅት መሪና ጠቅላይ የጦር አዛዥ አረጋዊ በርሄ ወያኔን ተቃዋሚ ነኝ ብሎ ካለ በኋላ እንኩዋን በሚከተለው መልክ ከጻፈው ጽሁፍ እንረዳለን።

የሸዋው የፊውዳል ባላባት የሃይለ መለኮት ልጅ (ምንሊክ) እንደ ማናቸውም የሸዋ መኳንንቶች ሁሉ ከጥንት ጀምሮ በጣም የስልጣንጥመኛና ፀረትግሬ የነበረ ሰው ነበረ። በንግስ ዘመኑ ሁሉ ዳግማዊ ምንሊክ የዘመናዊ የጎሳ ቅራኔና ግጭት ዋና ፈጣሪ ነበር። ዳግማዊ ምንሊክበአድዋ በጣሊያን ላይ የተጎናፀፈውን ድል ተቀናቃኞቹ ሊሆኑ በሚችሉት በተለይም በመንገሻ ዮሃንስና በአሉላ አባ ነጋ አመራር ሥር በነበሩትየትግራይ መኩዋንንቶች ላይ ከፍተኛ የበላይነትን እንዲቀዳጅ አደረገው። ዳግማዊ ምንሊክ ትግራይን የመከፋፈልና የማዳካም ዕድል ነበረው።የምንሊክ ጦር የጣሊያኑ የቅኝ ገዢዎች ጦር ያደረሰውን ያህል ጥፋት እንዲያደርስ በትግራይ ላይ መረን ተለቀቀ። የትግራይ ህዝብ ይህንን ጊዜዘመነ ሸዋ ብሎ ያስታወሰዋል፤ ይህም ማለት ትግራይ በሸዋ አገዛዝ ሥር  የወደቀብት ዘመን ማለት ነው።  የምንሊክ አቋም የተመሰረተውበሥልጣን ወዳጅነቱና ትግራይ ሊናቅ የማይገባው ጠላት ነው በሚለው አመለካከቱ ላይ ነበር። በርካታ የትግራይ ምሁራን ምንሊክ ትግራይንእንደራሱ ህዝብ የማያይ አድርገው ይቆጥሩታል። የምንሊክ ሰሜኑን የመከፋፈልና የማዳከም ሃሳብ የትግራይን ግማሽ ጣሊያን በቅኝ ግዛትነትይገዛው ዘንድ በመስጠት ሂደት የታጀበ ነበር[i] ምንሊክ አፍሪካ ለቅርጫ በቀረበችበት ዘመን ጣሊያን ኢትዮጵያን ቅኝ የማድረግ ፍላጎትእንደነበራት እምብዛም እውቀት አልነበረውም። ምንሊክ ትግራይ አንዴ ለሁለት ከተከፈለች እሷን እንደፈለጉ መግዛት ይቻላል ብሎ ያምንነበር። ትግራይን ለመቅጣት ምንሊክ በየዋህነት የወቅቱ የቅኝ ገዢዎች ወጥመድ ውስጥ ገባ። ኢጣሊያ የምንሊክን ድክመት በመጠቀም ወደደቡብ (ማለትም ከኤርትራ ወደ ትግራይ) መስፋፋት ቀጠለች። ምንሊክ ጣሊያኖች ኤርትራን ይዘው እንዲቆዩ ያደረገበትን ምክንያትበተመለከተ ክርክር ውስጥ ሳንገባ አንድ የማይካደው ሃቅ ግን ትግርኛ ተናጋሪው ህዝብ ለሁለት ጌቶች ማለትም ከመረብ በላይ ያለው ህዝብለጣሊያን፤ ከመረብ በታች ያለው ህዝብ ደግሞ ለምንሊክ ተከፍሎ ተሰጠ። ይህ ለወትሮው አንድ ወጥ በነበሩትና አንድ ላይ ቢሆኑ(የምንሊክን) ሥልጣን ለመቀናቀን በሚችሉት ትግሬዎች መካከል የተፈጠረው ከፋፋይ መስመር (fault line) መነሻ ወይም ምንጭ ነው።በዚህም ምክንያት ነው የሸዋ አማራ የገዢ መደብ ትግሬዎችን የማዳከም ዘመቻ በዚህ ታሪካዊ ወቅት የተጀመረው:: (Aregawi Berhe, ”Origins & Development of the National Movement in Tigrai; a Socio-historical Analysis”,  Institute of Social Studies, the Hague, 1993 (Aregawi Berhe was former chairman of the TPLF አረጋዊ በርሄ እንደ አውሮፓ አቆጣጠር በ ዓ.ም ሆላንድ ውስጥ ሄግ ከተማ በሚገኘው ኢንስቲትዩት ኦፍ ሶሻል ስተዲስ በተሰኘው ተቋም ውስጥ ለማስተርስ ዲግሪው በእንግሊዘኛ ቋንቋ ከጻፈው የተወሰደ (ጥቅሱን ከእንግሊዘኛው ወደ አማርኛ የተረጎምኩት እኔው እራሴ ነኝ)። 

 ከላይ ከጠቀስኩት የአረጋዊ  ጽሁፍ እንደምንረዳው አረጋዊና ተከታዮቹ ታሪክን በመከለስ ኢትዮጵያን ከጣሊያን የቅኝ አገዛዝ እንዲከላከልና ነጻነቷን እንዲያስጠብቅ የተደረገለትን ጥሪ ተቀብሎ በዐጼ ምንሊክ መሪነት የዘመተውን ከመላው የኢትዮጵያ ክፍሎች የተውጣጣ የኢትዮጵያ አርበኛ ትግራይን ወሮ ዘረፈ፤ አደኸየ ብለው ወነጀሉ። በዚህም ምክንያት የአድዋ ዘመቻ አዝማችና መሪ የነበሩት ምንሊክንና  የአማራ ህዝብ በትግራይ  ልሂቃን ዘንድ እንደ ጠላት ተቆጥረው ከትውልድ ትውልድ የተላለፈ የትግሬዎች ጥላቻ ዒላማ ሆኑ። እስቲ ከዚህ በታች የወያኔ ድርጅት የፖለቲካ ፕሮግራም ስለ አድዋ ጦርነትና እሱን ተከትሎ መጣ ስለሚለው የትግራይ መጨቆን ያለውንእንመልከት።

1881 .ትግራይ እንደገና በሸዋ አማራ ገዢዎች አፈናና ጭቆና ስር ወደቀች። ከባድ ታክስ በትግራይ ህዝብ ላይ ተጣለ። በመቶሺዎች የሚቆጠሩ ሆን ተብሎ ካለ ስንቅ የተላኩ የምንሊክ ጦር ወታደሮች የትግራይን መንደሮች ዘረፉት። ባጭር ጊዜ ውስጥ የትግራይ ህዝብየኢኮኖሚና የማሀበራዊ ሁኔታ በፍጥነት አሽቆለቆለ። ከዚህ በተጨማሪ ሆን ብሎ የትግራይን ህዝብ ቋንቋ ባህልና ታሪክ ለመጫን እርምጃዎችተወሰዱ። እነዚህ የጭቆና እርምጃዎች የትግሬዎችን ብሄረተኛ ስሜት በመቀስቀስ ኃይለኛ የሆነ ብሄራዊ ቅራኔን ፈጠሩ TPLF Political Program adopted at the Second Congress,1983 (ለዝርዝሩ በሁለተኛው  የወያኔ ሀርነት ድርጅት ጉባኤ ላይ የጸደቀውን የ1975 ዓ.ም. የፖለቲካ ፕሮግራም ይመልከቱ) (ከላይ የጠቀስኩትን ከእንግሊዘኛው ወደ አማርኛ የተረጎምኩት እኔው እራሴ ነኝ)። 

 የትግራይ ብሄረተኞች እየሰሙ ያደጉት ሀሰተኛ የምድጃ ዳር ታሪክ በተመለከተ የሚከተለውን ለአንባቢ ላስተዋውቅ፤

 በዚያ ቀን የሸዋ ሰራዊት መቀሌን ሙሉ በሙሉ ዘረፈው፤ በአካባቢው የነበሩ መንደሮችም በሙሉ ተዘረፉ። እንደርታም እንዳልነበረች ሆነች።በየመንገዱ ትልቅ ትንሽ ህፃን ሳይሉ ሰለቡት። ቀጥሎም የምንሊክ ሰራዊት እንደርታን አወደማት። እንዳልነበረች ሆነች። ብቻ የወንድ ልጅይሁን እንጂ የተገኘ ሰው ሁሉ ይገደላል። የእንደርታ ሰዎችም ቢሆኑ ዝም ብለው አልታረዱም። በየቋጥኙና በየጫካው እየተደበቁ የምንሊክንሰራዊት ሲፋለሙት ነበር። የምንሊክ ሰራዊት የመግደልና የመስለብ ሱስ ያለበት ነው። ሰዎችን በገደለና በሰለበ ቁጥር ይፎክራል። ሌላው ይቅርናበመላ ኢትዮጵያ የተከበረውን የአብርሃ ወአጽብሃ ገዳምም እንዳለ ዘርፈውታል[ii] (ምንጭ፤ ገብረ ኪዳን ደስታ የትግራይ ህዝብናየትምክህተኞች ሴራ ከትላንት እስከ ዛሬ በሚለው መጽሃፉ ውስጥ ከጠቀሰው ታሪክ ኢትዮጵያ በሚል ርዕስ በትግርኛ ቋንቋ ከታተመው መጽሃፍ የተጠቀሰ።

ስለ አማራ ህዝብና ስለ እነ ዐጼ ምንሊክ፤ ዐጼ ሃይለስላሴ ወዘተ በወላጆቻቸው ጥላቻን እየተጋቱ ያደጉት የዛሬዎቹ የወያኔ መንግስት መሪዎች ከልጅነት ጀምሮ ጥርሳቸውን ሰብረው ያደጉበትን በምድጃ ዳር የተማሩትን የጥላቻና የውሸት ታሪክ ከዘመናዊ የብሄረተኛነት አስተሳሰብ ጋር አዳቅለው አክራሪውንና ዛሬ ኢትዮጵያን እያፈረሰ ያለውን የትግራይ ብሄረተኛነት በማቀንቀን ኮትኩተው አሳደጉ። ዛሬ የትግራይ ብሄረተኛነት ጥቂቶች የሚጋሩት እብደት ሳይሆን እንደ ጀርመኑ የናዚ ወይም እንደ ጣልያኑ የፋሽዝም ርዕዮተ ዓለም በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ የጎሳ ተወላጆቹን አስተሳሰብ በመቀየርና ከሰውነት ደረጃ በማውጣት የወያኔ ትግሬዎች ከትግሬ ጎሳ ውጭ ያለውን ኢትዮጵያዊ በተለይ ደግሞ የታሪክ ደመኛችን ነው የሚሉትን የአማራን ህዝብ እንደ አደገኛ አውሬ የሚያዩበትና የዚህንም ህዝብ ህልውና ጨርሰው ለማጥፋት የተነሱበት ደረጃ ላይ አድርሶአቸዋል። የትግሬዎች አካላዊ ገጽታ፤ መልክ፤ ባህልና ታሪክ ከሌላው ኢትዮጵያዊ ጋር መመሳሰል ሌላው ኢትዮጵያዊ የወያኔ ትግሬዎችን እንደ እራሱ ወገን እንጂ ለኢትዮጵያና ትግርኛ ተናጋሪ ላልሆኑ ኢትዮጵያውያን ይህን ያህል ጥላቻ ያላቸው ወገኞች ናቸው ብሎ እንዳይገምት አድርጎታል፤ አዘናግቶታልም። ስለዚህም የኢትጵዮጵያ ህዝብ የወያኔ ትግሬዎችን እዚህ ደረጃ ላይ ሳይደርሱና ብዙ ጥፋት ሳያደርሱ ሊያቆማቸው የሚችልበት ብዙ አጋጣሚዎች አልፈውታል። ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ በሀገራችን በህዝቡ ዘንድ ቀርቶ የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ነን በሚሉት ዘንድ ስለ ጎሳ ብሄረተኛነት (ethnic nationalism) ያለው ግንዛቤ እጅግ የሚያሳዝን በመሆኑ ዛሬ ወያኔ እያደረሰ ያለውን የጎሳ ጽዳትና ጎሳን መሰረት የጅምላ ፍጅት ይከሰታል ብለው ለማሰብ አልቻሉም። በኢትዮጵያ ረጅም ታሪክ ውስጥ ያንድ የኢትዮጵያ ጎሳ አባሎች (ትግሬዎች) የመንግስት ስልጣን ይዘው አንተ ይኸ ክልልህ ስላልሆነ ከዚህ ለቀህ ውጣ በማለት የሌሎችን ጎሳ አባላት (አማራን፤ አፋርን፤ አኑዋኮችን ወዘተ) እንደ አውሬ በጦር መሳሪያ የሚያሳደዱበትን፤ ህጻናትና አሮጊቶች ሽማግሌዎችና አቅመ ደካማዎችን ለሞትና ለዘግናኝ ስቃይ የሚዳርጉበት ዘመን ታይቶ አይታወቅም።

የወያኔ ትግሬዎች ዓላማ አማራ ብለው የሰየሙትን ጨቋኝ የደርግ ስርዓት ጥለው ለትግራይ ህዝብ ህይወት የሚያሻሽል ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ለውጥ ማምጣት ነበር። ይህንን ዓላማቸውን አስመልክቶ የቀድሞው የወያኔ መሪ በ ዓ.ም በጻፈው ጽሁፍ የሚከተለውን ብሎ ነበር። የትግራይ ህዝብ የወል ምኞት ጨቋኙን የአማራ (የደርግ) መንግስት መጣል ብቻ ሳይሆን የራሳቸውን (የትግሬዎችን) ህይወት የሚያሻሽል የማህበራዊና የኢኮኖሚ ለውጥን ማምጣት ነበር”። አረጋዊ በርሄ “How the Media of the TPLF Emerged and Countered the Dominant Media of the Ethiopian State: Can it be a Viable Alternative for Social Transformation?”, a paper written by Aregawi Berhe for a degree at the Hague Institute of Social Studies, 1992) (ጥቅሱን ከእንግሊዘኛ ወደ አማርኛ ትርጉም የራሴ የአሰፋ ነጋሽ ነው)። ይህን ከላይ አረጋዊ በርሄ የገለጸውን የወያኔ ዓላማ በማሳካት በኩል ባለፉት ሃያ ሁለት ዓመታት የወያኔ ትግሬዎች መንግስት ምን እንዳደረገ፤ እንዴት የትግራይን ገጽታና የትግራይ ተወላጆችን ህይወት ጉልህና አዎንታዊ በሆነ መልክ እንደቀየረ ማንም የኢትዮጵያን ጉዳይ የሚከታተል፤ እንደዚሁም በራሱ ሀገር የበዪ ተመልካች የሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ ስለሚያውቀው ዝርዝር ውስጥ ለመግባት አልፈልግም። የትግራይ የጎሳ ብሄረተኞች ግን ባለፉት ሃያ ሁለት ዓመታት ለህዝባቸው ያለሙትን ልማትና ማህበረሰባዊ ለውጥ እንዳመጡ መካድ አይቻልም።

 የጎሳ ፌደራሊዝም፤ ማንነት ላይ የተመሰረተ ፖለቲካና የጎሳ ግጭት በኢትዮጵያ 

የወያኔ መንግስት የተመሰረተበትና በዛሬይቱ ኢትዮጵያ የመንግስታዊ ስርዓት መሰረት የሆነው የጎሳ ፌደራሊዝም የጎሳን ማንነትና ልዩነትን ዓይነተኛ የፖለቲካ ማደራጃ አድርጎአቸዋል። የጎሳ ፌዴራሊዝም ዲሞክራሲያዊ ሳይሆን ኢ-ዲሞክራሲያዊ ነው። ዲሞክራሲ ሁሉን አሳታፊ እንጂ አንድን ግለሰብ በጎሳ ማንነቱ ምክንያት ከፖለቲካ ተሳትፎ ውጭ የሚያደርግ አይደለም። ፖለቲካ በጎሳ ማንነትና መስፈርት ላይ ተመስርቶ አንድን ሰው አንተ የእኔ ጎሳ አባል አይደለህም ብሎ በጎሳ ማንነቱ ምክንያት ሲያገል፤ ሌላውን ደግሞ አንተ የጎሳ አባሌ ነህ ብሎ ሲያሳትፍና ሲያቅፍ፤ ይህን አይነቱ ጎሳን መሰረት ያደረገ ፖለቲካ ዲሞክራሲ የሚባለውን አስተሳሰብ በጽኑ ይቃረናል። በዚህም ምክንያት በጎሳ ማንነት ላይ ተመስርቶ የሚደራጅ የፖለቲካ ስርዓት በአንድ ማህበረሰብ ውስጥ ያሉ የተለያየ የእምነት ተከታዮች፤ የተለያዩ የጎሳ ተወላጆች እንደ ሰው ወይም እንደ ሰብዓዊ ፍጡር በሚያስተሳስሯቸውና በሚጋሯቸው በርካታ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ እንደ አንድ ሀገር ዜጎች እንዳይገናኙ የሚያደርግ በመሆኑ አፍራሽ እንጂ ገንቢ አይደለም። የጎሳ ፌዴራሊዝም በአንድ ሀገር ውስጥ የሚኖሩ ዜጎች በልዩነቶቻቸው ላይ እንዲያተኩሩ በማድረግ ሊያቋርጥ የማይችል ጥላቻን በማራገብ ለጋራ ጥፋትና እልቂት የሚጋብዝ፤ በባህል መጠበቅ፤ በጎሳ መብት መጠበቅ ስም ያንድ ጎሳ ልሂቃን እኛ የዚህ ጎሳ ብቸኛ ተወካዮች ነን ብለው ባንድ ነጻ ማህበረስብ ውስጥ ሊደረግ የሚገባውን በጎሳ ማንነት ሳይሆን በፖለቲካ አስተሳሰብ ላይ የተመሰረተ ጤናማ የፖለቲካ ውድድር ወይም ፉክክር የሚሸሹበትን ኢ-ዲሞክራሲያዊ አመለካከትና አሰራር ያራምዳል። ይህም የጎሳን ማንነት መሰረት ያደረገ የፖለቲካ ስርዓት ወደ ፋሽስታዊ የዘር ፍጅትና የእርስ በርስ ጥላቻ የሚያመራ አደገኛ ርዕዮተ ዓለም ነው። የፈረሰችው የትላንትናዋ ዩጎዝላቪያ የጎሳ ፌዴራሊዝም በአንድ ሀገር ላይ የሚያስከትለውን ጥፋትና ፍጅት አሳይታናለች። የጎሳ ፌዴሊዝም አንዱን ሕዝብ በሌላው ላይ ያነሳሳል ምክንያቱም የጎሳ ፌደራሊዝም ባፈጣጠሩ ህዝብን በሚለያይ ማንነት ላይ የተመሰረተና በልዩነት ላይ  ያተኮረ ስለሆነ ነው። የጎሳ ፌደራሊዝም የጎሳን ማንነት ብቻ በማጉላት ሌሎች የማንነት መገለጫዎችን ያደበዝዛል፤ ያንድ ሃገር ዜጋዎች በመካካላቸው የግንብ አጥር እንዲሰሩ ያደርጋል፡ ያለያያል፡ ያቃቅራል። አንድ-ወጥ ጎሳ ለመፍጠርና “ንጹህ ደም ያላቸውን የአንድ ጎሳ ተወላጆች” ባንድ ኩታ-ገጠም ክልል ውስጥ ለማሰባሰብ የሚደረገው ጥረት በግድ ከዚያ ከንጹሁ ጎሳ ተወላጆች ውጭ ያሉትን የሌሎች ጎሳ ተወላጆችን “ከንጹሁ ጎሳ ተወላጆች” ክልል በሃይል ወደ ማስወጣቱ የጭፍጨፋ ሂደት ያመራል። ትላንት በምስራቅ ወለጋ፤ በጉራ ፈርዳ ዛሬ ደግሞ በቢኒሻንጉል የታየው ዘግናኝ ድርጊት የጎሳ ፌዴራሊዝም ውጤት ነው። የጎሳ ፌዴራሊዝም ዋና አራማጅ የሆኑት የኦሮሞ ብሄረተኛ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ አሜሪካን ሀገር ይታተም በነበረ ኢትዮጵያን ኤክዛምነር (Ethiopian Examiner) በሚባል መጽሄት እንደ አውሮፓ አቆጣጠር በሰኔ ወር 1993 በጻፉት አንድ መጣጥፍ ውስጥ የሚከተለውን ሃሳብ አስፍረው ነበር።  “ኦሮሞዎች የኦሮሞ ዞኖች ወይም ቀጠናዎች ሁሉ ባንድ ላይ ተጠቃለው አንድ የኦሮሞ ክልል ሥር እንዲሆኑ ይፈልጋሉ (Bulcha Demeksa, Ethiopian Examiner, June 1993)ይህ የአቶ ቡልቻ ሃሳብ በረጅም ትልሙ አንደ-ወጥ (ethnically homogenous) የሆነ ያንድ ጎሳ ተወላጆች ብቻ የሚኖሩበት ክልል ለመፍጠር፤ ብሎም ከኦሮሞ ጎሳ ውጭ ያሉ ሌሎች ጎሳዎችን በማስወገድ ራሱን የቻለ አንድ ነጻ ሀገር ለማቋቋም ያለመ ሂደት መሆኑን ማንም የማገናዘብ ችሉታ ያለው ሰው ይረዳል። ጎሳን መሰረት ያደረገ ክልል በመጨረሻ እናንተ የእኛ ጎሳ አባሎች ስላልሆናቸሁ ከዚህ ውጡ ወደሚለው የጎሳ ጽዳት ( ethnic cleansing ) እንደሚያመራ ትላንት በምስራቅ ወለጋ፤ በጉራ ፈርዳ፤ በቤኒሻንጉልና በኦጋዴን የተከሰተው ሁኔታ ያሳየናል። አቶ ቡልቻ ደመቅሳ የጎሳ ፌዴራሊዝም በኢትዮጵያ ተቀባይነት ያለውና ጭራሽ ሊቀለበስ የማይችል እውነታ መሆኑን በሚከተለው መንገድ እርግጠኛ ሆነው በዚሁ ኢትዮጵያን ኤክዛምነር በተሰኛው ባንድ ወቅት በአሜሪካ ይታተም በነበረው ወርሃዊ መጽሄት ላይ እ. አ. አቆጣጠር በግንቦት 1993 በጻፉት ጽሁፍ ውስጥ ይነግሩናል። “በኢትዮጵያ በጎሳ ላይ የተመሰረተው ፌዴራሊዝም ወደ ኋላ ሊመለስ አይችልም ምክንያቱም አብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ ይፈልገዋልና”( Bulcha Demeksa, Ethiopian Examiner, May 1993) አቶ ቡልቻ ይህንን ከፍተኛ ድፍረት የተሞላበት፤ በጥናትና መረጃ ላይ ያልተመሰረተ አስተያያት ሲሰጡ ድፍን የኢትዮጵያ ህዝብ ቀርቶ እሳቸው በደንብ አውቀዋለሁ፤ ጥቅሙን አስጠብቅለታለሁ የሚሉትን የኦሮሞን ህዝብ እንኳን ጠይቀው፤ አስተያየቱንና ፍላጎቱን ሰብስበው አይደለም። በወያኔ ትግሬዎች መንግስት ከተደረገው ከአስራ አራት ዓመታት የጎሳ ፖለቲካ ሰበካ እንኳን በኋላ የኢትዮጵያ ህዝብ ለጎሳ ፌዴራሊዝም ልቡን እንዳልሰጠ በግንቦት ወር 1997 ዓ. ም የተደረገው ብሄራዊ ምርጫ አሳይቷል። በጎሳ ሳይሆን ሀገር-አቀፍ አጀንዳ አንግቦ ውድድር ውስጥ የገባው የቅንጅት ድርጅት ያገኘው ከፍተኛ ድጋፍ የአቶ ቡልቻንና ከወያኔ ጀምሮ እስከ ዛሬዎቹ የመድረክ አባሎች ድረስ ያሉትን የጎሳ ፖለቲካ አራማጆች ክፉኛ አስደንግጦአል። መድረክም የዚህ የጎሳ ፖሊቲካ ክስረት ያስደነገጣቸው የጎሳ ፖለቲካ ድርጅቶች ስብስብ ሆኖ ብቅ ያለው ይህንን የጎሳን ፖለቲካ ውድቀት በጋራ ሆኖ ለመከላከል፤ ጎሳ-ዘለልና ሀገር-አቀፍ ኢትዮጵያዊ የፖለቲካ አጀንዳ ያላቸውን ወገኖች በኢትዮጵያ ህዝብ ውስጥ ያላቸውን ተቀባይነት ለመዋጋት ነው። የእነ ሰዬ አብርሃም ከወያኔ ወጥቶ መድረክ መግባት አልሸሹም ዞር አሉ ነው፤ ወደዚያው ጥርሱን ወደነቀለበት የጎሳ ፖለቲካ የደራበት የመድረክ ሰፈር ተመልሷል።

 

 

 

* የዚህ ጽሁፍ ጸሀፊ አሰፋ ነጋሽ በሆላንድ የሚኖር ኢትዮጵያዊ ስደተኛ ሲሆን በዚሁ በተሰደደበት ሀገር በተማረው የህክምና ሙያ የአይምሮ ሀኪም (ሳይካትሪስት ሆኖ እየሰራ ይገኛል)። አንባቢያን ይህን ጽሁፍ አስመልክቶ ለሚሰጡአቸው አስተያየቶችም ሆነ ትችቶች ጸሀፊውን በሚከተለው የኢሜይል አድራሻ ማግኘት ይችላሉ። ——–›  Debesso@gmail.com 

 

———————————-/////————————————–