አፈናውና ጭቆናው ሲጨምር ፤ትግሉም እየጠነከረ ነው።
ሰበር መረጃ!!!
ከአማራ ክልል የሕዝባዊ እምቢተኝነት አስተባባሪ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫና አዲስ የትግል ጥሪ!
አዲስ የትግል ጥሪ !!
_ቀጣዩ እቅድ አንባገነኑ መንግስት በአማራና በኦሮሚያ እንዲሁም በጋምቤላና በኮንሶ በሰላም ባዶ እጁን ለተቃውሞ በወጣ ህዝብ ላይ በአልሞ ተኳሽ ህዝብን መጨፍጨፍ ሥራ ብሎ ይዞታል። ዛሬም ወጣትነት እስኪጠላ ድረስ በጅምላ ይጨፈጭፋል ፤በጅምላ ያፍናል፤ በጅምላ ያስራል፤ አስሮም አድራሻ አጥፍቶ ይገላል፤ ወላጆችም በሞቱት ልጆቻቸው አንጀታቸው ተቆርጧል። ልጆቻቸው የታሰሩባቸውም በህይወት ይኑሩ አይኑሩ ለማወቅ ተቸግረው ሌት ተቀን እያለቀሱ ይገኛሉ።
በቁስል ላይ እንጨት እንዲሉ ሰሞኑን በቢሾፍቱ የተፈጠረው ሁኔታ ሁላችንንም የማይታረቅ ቅራኔ ውስጥ አስገብቶናል። ጠንከር ያለ እርምጃ እንድንወስድም አስገድዶናል። በመሆኑም ባለን ውክልና በአማራ ክልል የወሎ፣ የጎንደርና የጎጃም የህዝብ ትግል አስተባባዎች የሆንነው አካላት አዲስ የትግል ጥሪዎችን አውጥተናል።
የኦሮሚያ ክልል የህዝብ ትግል አስተባባሪዎችም እንዲህ አይነት የትግል ስልቶችን በመጠቀም ከወገኖቻቸው ጋር በመተባበር በአስር ሽዎች የሚቆጠሩ በማሰቃያ ቤቶች የሚገኙ ወንድሞቻቸውን እና 40 ሚሊዮን የሚገመተውን የኦሮሚያን ክልል ህዝብ ከሌላው ወንድሙ ጋር በማስተባበር ፤ህዝባችንን ነፃ ለማውጣት እንድንተባበር ይህን የትግል ጥሪ ስናቀርብ፤ሌሎችም በህወሀት አገዛዝ ታፍነው የሚገኙት የደቡብ ፣የጋምቤላ፣ የሶማሌ፣ የሀረሪ፣ የቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ የአፋር እና የትግራይ ክልል ሕዝብ ከሌላው ወገናቸው ጋር በትግሉ በመተባበር ሁላችንም ነፃ ልንወጣ ይገባል የሚል እምነት አለን።
እንዲሁም በአዲስ አበባ የሚኖሩ ነጋዴዎችና አጠቃላይ የመዲናዋ ነዋሪዎች፤ የንፁሀን ወገኖቻቸውን ያልተቋረጠ ስቃይ ለማስቆም የሌሎች ወንድሞቻቸውን ጥሪ ሊተገብሩ ግድ ይላቸዋል።
በመሆኑም እኛ የአማራ ህዝብ ትግል አስተባባሪዎች፣ አፋኙን አገዛዝ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስወገድ ህዝብን በማይጎዳ መልኩ ከዚህ በፊት ካካሄድነው የስራ ማቆም አድማ በበለጠ ጠንካራና ገዥውን ቡድን የሚያሽመደምድ ትግል የቀረጽን ሲሆን ህዝብም ይህን አንድ ሀሙስ የቀረው ቡድን አሽቀንጥሮ ለመጣል ይህን የትግል ስልት ያለፍርሀትና ያለመለያየት በጋራ ተግባራዊ ሊያደርገው ይገባል።
የትግል አይነቶች፦
የትግል ስልት1ኛ
-ለግል ድርጅቶች የ2008 ዓ/ም ግብር እስከ ተህሳስ 30 ታክስ አለመክፈል።
ከላይ እንደተመለከተው የወርሃዊ ቫት አለመክፈል ጥሪ ያስተላለፍን ሲሆን፤ አንድ ነጋዴ አገዛዙን ፈርቶ ታክስ እከፍላለው ካለ እስከ ታህስስ 30 ድርጅቱን የመዝጋት አማራጭ ቀርቦለታል። ምክንያቱም ህዝብ አንድ ከሆነ፤ አሸባሪው ቡድን ምንም ማድረግ አይችልምና።ይህን ጥሪ ጥሶ ለገዳዩ መንግስት ታክስ እየከፈለ ሌላውን የሚያሳጣውንና ለወንድሞቹ መግደያ ጥይት የሚገዛውን ድርጅትም ለመፋረድ ዝግጅት አድርገናል።
ምክንያቱም እኛ ወጣቶች ለነፃነት የህይወት መስዋትነት እየከፈልን ባለበት ሁኔታ አንዳንድ ነጋዴዎች ለንብረት ሣስተው ለገዳዩ መንግስት የጥይት መግዣ የሚሆን ግብር ከከፈሉ እኛም ለነሱ ዋጋቸውን እንከፍላለን። ከሌላው ወገኑ ጋር ያልተባበረ ነጋዴንና ከህዝብ ያልወገነ የታክስ መስሪያ ቤት ሰራተኛንም ከገዳዩ የህወሀት ቡድን በምንም አይነት ለይተን የማናያቸው መሆኑን ሊያውቁት ይገባል።
በተጨማሪም ነጋዴው ታክስ እንዳይከፍል የሂሳብ ባለሙያዎች ነጋዴውን በነፃ እንዲያማክሩት እናሣስባለን። ከምክሮቹም ውስጥ 1ኛ የወርሃዊ ቫት ሪፓርትና አመታዊ ታክስ ክፍያን ለወራት በማቋርጥ በወር በ2000 ብር ቅጣት ሳይከፍል እንደሚቆይ ማስገንዘብ፣ 2ኛ የአመታዊ የትርፍ ግብር የኪሳራ ሪፓርት ማቅረብ እና 3ኛ ተመላሽ ክፍያወችን መጠየቅ የሚሉት ይገኙበታል። ይህን በተመለከተ ለበጠ መረጃ የሂሳብ ባለሙያወችን ያማክሩ ።
እኛ የአማራ ክልል የህዝባዊ እምቢተኝነት አስተባባሪዎች ከሌሎች ወንድሞቻችን እና ከሕዝባችን ጋር በመሆን በነዚህ ወራት ይህን ዘረኛና ገዳይ ቡድን ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስወገድ እየጣርን ባለበት ሁኔታ የገዳዩን ቡድን እድሜ ለማራዘም ይህን ግብር ያለመክፈል ጥሪ የሚጥሱ ነጋዴዎችን ስምና አድራሻ የታክስ መስሪያቤት ሰራተኞች እንዲተባበሩን ጠይቀናል፣ አሁንም እንጠይቃለን።
በተጓዳኝ ከህዝብ ያልወገኑ የታክስ መ/ቤትና የንግድና ትራንስፖርት መ/ቤት ሰራተኞችን ስም ፣ የሥራ ቦታና እድራሻቸውን ነጋዴው ሊያደርሰን ይገባል።
የትግል ስልት 2ኛ
በአማራ ክልል የሚገኙ የመንግስት ተባባሪ ድርጅቶች ፦
ሀ- የጥረት ድርጅቶች ፣ለ- የሸህ ማህመድ አል አሙዲ ድርጅቶች፣ ሐ- በክልላችን የሚተላለፉ የህወሀት ተሽከርካሪዎችና ንግድ ድርጅቶች ስራችውን Yaderaw Esregna Gondar's photo.እንዲያቆሙ ጥሪ እያስተላለፍን፤ ይህን ጥሪ ከተላለፉ እርምጃ እንደምንወስድባቸው እናሳውቃለን!!!
የህወሀት ተሽከርካሪዎችን የሚያሽከረክሩ ሾፌሮች ወንድሞቻችንም በክላችን እንዳትንቀሳቀሱ በውንድሞቻችን ደም እንጠይቃለን!!!
የትግል ስልት 3ኛ
ንግድ ባንክ፣ ዳሽን ባንክ፣ አንበሳ ባንክ፣ አባይ ባንክ፣ ወጋገን ባንክ፣ አማራ ብድር እና ቁጠባ ባንክ ተጠቃሚ የሆናችሁ የአማራ ክልል ነዋሪዎች በ15 ቀን ውስጥ ገንዘባችሁን እንድታወጡ እንጠይቃለን። ከ15 ቀን በሗላ ማንም የአማራ ክልል ህዝብ ገንዘብም በነዚህ ባንኮች እንዳይገባና እንዳይወጣ፤ እንዲሁም ከነዚህ ባንኮች የወሰደውን ብድር እንዳይከፍል፤ በነዚህ ባንኮች በእዳ የተያዙና ለጨረታ የቀረቡ የግለሰብ ቤቶችን እና ተሽከርካሪዎችንም ማንም እንዳይገዛ እናሣስባለን። ይህን ጥሪ ጥሶ በእዳ የተያዙ ንብረቶችን የሚገዛ፤ ነገ ጧት ሀብቱ የህዝብ እንደሚሆን ከወዲሁ እናሳውቃለን!!!
በትጓዳኝ ሌሎች ባንኮችም ቅርንጫፎቻቸውን እንዲያሰፉ ባልተቋቋሙባቸው የአማራ ክልል ከተሞች ቅርንጫፎችን እንዲከፍቱ እንጠይቃለን!
የንግድ ባንክ፣ የአንበሳ ባንክ፣ የዳሽን ባንክ፣ የአባይ ባንክ፣ የአበቁተ ባንክ ስራ አስኪያጆች፤ ገንዘቡን ወጭ የሚያደርገውን ህዝብ ያለምንም ችግር እንዲያስተናግዱ በሞቱት ወንድሞቻችን ስም እንጠይቃለን!ከዚህ በሗላ በነዚህ ባንኮች እየተጠቀመ ለወንድሙ መግደያ ጥይት የሚገዛውን ግን እንፉረደዋለን!!!
ህዝብ ከከፈለው ግብር በአመታዊ በጀት ተመልሶ ለልማት ሊደርሰው ይገባ ነበር። የእኛ የአማራ ህዝብ ግን፦ “ሰነፍ ነው፤ አይሰራም” ተብሎ ግብር ከፍሎ ከተመደበለት 4.5 ቢሊዮን ብር (ልብ በሉ ሚሊዮን እይደለም)የአማራ ክልል ልማት ባንክ በጀት ገንዘብ፤ ወደ ትግራይ ተወስዶ ሕዝብን ለመጨፍጨፍ ለህወሀት ወታደሮች ስልጠና እየተሰጠ ባለበት ወቅት እኛ በህወሀት በሚሽከረከሩ ባንኮች ገንዘባችንን ማስቀመጥ ፈጽሞ የለብንም!!!
የትግል ስልት 4ኛ
በመድን ኢንሹራንስ፣ ኒያላ ኢንሹራንስ ፣አንበሳ ኢንሹራንስ፣ አባይ ኢንሹራንስ ፣አፍሪካ ኢንሹራንስ ፣ተጠቃሚ የአማራ ህዝብ ከነዚህ ድርጅቶች ገንዘቡን ተመላሽ በማድረግ ሌሎች ኢንሹራንሶች እንዲገባ ጥሪ እናስተላልፉለን!!ሌሎች ኢንሹራንሶችም ለህብረተሰቡ የተመጣጠነ ዋጋ እንድታቀርቡ እንጠይቃለን።
የትግል ስልት 5ኛ
በውጭ የሚኖረው ማህበረሰብ በወገኑ ላይ እየደረሰ ያለውን አይን ያወጣ ስቃይ እያየ ወደ ሀገር ቤት በባንክ ገንዝብ መላክ፤ ሕዝብን በተጋድሎው በማገዝ ፋንታ ወገንን ለማስገደል መንግስትን እንደማገዝ ይቆጠራልና ቢችሉ 3 ወር ላልበለጠ ጊዜ ገንዘብ እንዳይልኩ እንጠይቃለን!!
ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ግዴታ መላክ ካለበዎት በጥቁር ገበያ እንዲልኩ አለዚያም ዘመድዎ ሀገር ውስጥ ካለ ዘመድ ወይም ወዳጅ ተበዳድረው እንዲቆዩ ያደርጉ ዘንድ እንጠይቃለን። ይህ ውጪ ላለው ወገናችን ለራሱ ህሊና የሚተው ጥሪ ሲሆን፤ ይህን ጥሪ ጥሶ በባንክ ገንዘብ የላከን ከአጋዚ ለይተን አናየውም።
የትግል ስልት 6ኛ
ማንኛውም ህዝብ ከዛሬ ጀምሮ የመሬት ሊዝ ማንኛውንም አይነት ክፍያ ለአማራ ክልል ለከተማ አስተዳደር መ/ቤቶች እንዳይከፍል!!
የትግል ስልት 7ኛYaderaw Esregna Gondar's photo.
ትራፊኮች፣ አደጋዎችን ከመቆጣጠር ውጭ ተሽከርካሪዎችን በገንዘብ እንዳትቀጡ!
የትግል ጥሪ 8ኛ
የመንግስት ተላላኪዎች በሙሉ ከዛሬ ጀምሮ ከህዝብ ጎን የማትቆሙ ከሆነ በናንተና በንብረቶቻችሁ ላይ የማያዳግም እርምጃ እንወስዳለን!!
የትግል ስልት 9ኛ
የመንግስት ባለስልጣን እና ካድሬ ንብረቶችን ባልተጣሩበት ሁኔታ ከዛሬ ጀምሮ በእዳ መያዣም ይሁን በግዥ ማንም እንዳይገዛ ጥሪ እናቀርባለን! እነዚህን ንብረቶች ገዝቶ የተገኘ ፤ነገ ጧት ወደ ህዝብ ንብረትነት መመለሳቸው እንደማይቀር ከወዲሁ እናሳውቃለን!!!
ከላይ የተዘረዘሩት ከዛሬ ጀምሮ የሚተገቡሩ የትግል ስልቶች ሲሆኑ ፤አሸባሪው ቡድን የህዝብን ጥያቄ የማይቀበል ከሆነ፤ አስተባባሪ ኮሚቴው በየደረጃው ከዚህ የተሻሉ ሌሎች እርምጃዎችን ለመውሰድ ዝግጁ መኾኑን እናሳውቃለን።Yaderaw Esregna Gondar's photo.
የአማራ ክልል ሕዝባዊ እምቢተኝነት አስተባባሪ ኮሚቴ!
LikeShow more reactionsCommentShare