ገጣሚና አክቲቪስት ሄኖክ የሽጥላ

ለአርበኛ አበራ ጎበውና ለጀግኖች የትግል አጋሮቹ የተቀኘው ቅኔ እነሆ በረከት፦14581296_1098532346881660_6245551280675643832_n

የባሩዱ ሽታ
የ አያ ጎኔ ሞዜር
ሲጮኽ ይሰማኛል
የማን ዘር ጎመን ዘር!

ዲበ ኩሉ እንዲሉ
ዲበ በስናድር
እልሞ ገንዳሽ ነው
ይሄ የኔ ወንድም !

ተኩስ ተኩስ በሉት
ሸልል ሸልል በሉት
የጎበዝ ሃገር ልጅ
የጀግና ዘር ውላጅ
ከጠመንጃው ሌላ
አያውቅም አማላጅ!

ሎጋው ሽቦ ሲሉ
ይሰማኛል ከሩቅ
አረ ጎራው ሲሉ
ይሰማኛል ከሩቅ
ጠሃይ ሳትገባ ፥ ጀምበርም ሳትጠልቅ!

«በለው በለው እና
አሳጣው መድረሻ
ዘመድ እንደሌለው
እንደ ሆደ ባሻ!»

ያገሬ አናብስቶች ፥የተቆጡ ለታ
ያገሬ ቆራጦች እምቢ ያሉ ለታ
ልባቸው መለከት ፥ ቁጣቸው ነጋሪት
ባንድ ጥይት አስር ፥ ይጥላሉ የኋሊት!

ወያኔን አየሁት ባፍጢሙ ተደፍቶ
እየሸሸ ሲሞት ፥ በመጁ ደም ተፍቶ!

አረ ወያኔ ይሙት ፥ ይደፋ ባፍጢሙ
ጥንብ ያንሳው ስጋውን ፥ ጅብ ይላሰው ደሙን !

ኄኖክ የሺጥላ14708335_1691859871141865_5459499302866830139_n