# እሴት ልጅ ደም አይመለስም

~~~~ እረፍት የነሳይ ነገር ~~~~~~~
~~~~~~===============~~~~~~~~
እኔን እረፍት የነሳይ የጠላቶቻችን ጭካኔ ሳይሆ የኛ የዋሕነት የጠላቶቻችንን ማንነት በደንብ ያልተረዳነው መሆናችን ነው ።
የጠላትክን ማንነት በትክክል ከማወቅም ባሻገር በሚገባ መግለፅ የማንችል መሆኑ ነው ።
ይህ ከሆነ እስከወዲያኛውም ጠላታችን ለመከላከል በቂ እውቀቱም ዘዴውም አቅምም የመፍጠር ዘዴው ሊኖረን አይችልም ።
ይህ ትኩረቴ “ለምሁሩ” ለሚባለው ማሕበረ ሰብአችን ኢትዮጵያዊ ነን ለምንል ነው ።
ያልተማረው የሚባለው ገበሬው አርሶ አደሩ የጠላቱን ማንነት ከተረዳው ውሎ አድሯል ።
የጠላትን ማንነት በሚገባ ካወቅህ እንዴት ከጠላትህ ነፃ መውጥት የሚሉትን ጥያቄ በደንብ ለመመለስ ዝግጅት ታደርጋለህ ።
የሀገሬ ገበሬ የጠላቱን ማንነት ስለተረዳ ውድ ሕይወቱን ለመስጠት እስካፍንጫው ከታጠቀ ከትግሬው ነፃ አውጭ ነኝ ባይ ነፍሰ ገዳይ ቅልብ የዓግአዚ ጦር ፊት ለፊት በመቆም ደረቱን ለጥይት እየሰጠ ይገኛል ።
—: ይህ የመንፈስ ዝግጅት ቁርጠኝነቱ ከየት መጣ ? ካልን የጠላትክን ማንነት በደንብ ስትገነዘብ አብሮ የሚመጣ የተፈጥሮ ሁናቴ እንደሆነ ትረዳለህ ። ይህን የተፈጥሮ ክስተት መሆኑን ለመረዳት እንደምሳሌ የምንወስደው በደመ ነፍስ የሚንቀሳቀሱ ግዑዛን ትናንሽ ነፍሳትም ከትል ጀምሮ ራሷን ከሚበላት ጠላቷ ጋር በመንፈራገጥ ከጠላቷ ለመዳን ሙከራ ታደርጋለች ።
ይህ ራስን ለማዳን በምሁሩና የአራዳ ልጅ ነን ነሚያምነው ወጣት ጨርሶ የማይታሰብ በአንድ ከርፋፋ ፖሊስ ነኘወ በሚል እንደ ኑግ እተተወቀጡ መኖር አሳፋሪ ነው ።
አንድን ገበሬ በጥፊ ብትመታው ዝም አይልህም ያኔ ምንም ባያደርግህም ቂሙን ቋጥሮ አንድ ቀን አንጀቱን ሳይስጎትተው አይቀርም ።
የኛ ” ምሁሩ ሕብረተ ሰብ ” የትግሬን ነፃ አውጭ ማንነት ጠንቅቀን ያላወቅን ።የ” ኩሩ ፖለቲከኛ ምሁሩ ክፍል ”
አይደለም እኛ እናውቃለን ይሉና ከምንም በላይ ራስ ወዳድነትን ያስቀድሙና ሌሎች ተሰውተው በሚያመጡት ለውጥ ለመጠቀም ከወዲሁ ለመዘጋጀት ማንም እንደማይቀድማችሁ እናውቃለን ። ይህ ደግሞ ባልደከሙበት መክበር በምድሩም በሰማዩም ህግ የተላለፈ ኢትዮጵያዊነትን የደመሰሰ የሻረ ነው እላለሁ ።
አይ? ይህ እግዜር አይወደውም የሚሏት ያች ኢትዮጵያዊነት በአራዳዎች ቤት ሞታና ተቀብራ ብትጠፋም ። ወደ ሀገር ቤት ጎራ ስትል ሕይወት ሰርታ ታገኘሰታለህ ።

” የተማረው ሕብረተ ሰብ ” የሚባለው ከተፈጠረ ከ50 ዓመታት ወዲህ የመጣ አዲስ የአራዳነት ዘይቤ ራሱን ካልተማረው ገበሬ ያገለለ አቀላጥፎ በመናገሩ ብቻ የተማረ የተመራመረ የሚመስለው ስንት ቦዘኔም እንዳለ የማይካድ ደረቅ ሀቅ አለ ።
አሁን ላይ በዘመናዊቷ ኢትዮጵያ የተፈጠረው ኢትዮጵያዊነት እንኳንስ ከውጭ ወራሪ ሀገርን ነፃ ለማውጣት ወደጠላት በባዶ እግሩ ነፃነት ወይም ሞት ብሎ መዝመት ይቅርና ጎረቤቱ በሌሊት እንደ ቤት እሳር ተመዞ ሲወሰድና ጎረቤቱ ከደጁ ላይ ሲገደል ለምን ማለት እርም ነው ።
” ምሁሩ ” ሀገር ማለት ምን ማለት እንደሆን በአፍ የሚነገር ቲወሪ እንጅ ሀገር ማለት እስከ ደም ጠብታ የሚከፈልላት ለመሆኑ ተማርኩኝ አወቅሁኝ ተመራመርኩኝ ከማለት በስተጀርባ እንዴት የሚሉትን ጥያቄና መልስ ያገናዘበ አይመስለኝም ።
ምሁርነት ወይም አራዳነት ያስከተለው ጦስ በኢትዮጵያ ።
አጭበርብሮ መኖር እውነትን መናገር መጋተር ነው ብሎ የሚያስብ ተዋርዶም ቢሆን በሕይወት መኖርን እንደ አማራጭ የሚወስን ።
ባገኘው ቀዳዳ ሁሉ ተጠቅሞ ሀገሩን ለማንም ዘረኛ ኋላ ቀር አስረክቦ ሀገርን ጥሎ መሰደድን የተቀበለ ነው ።
ምሁር ነኝ ባይ አያውቅ አያሳውቅ መንቀፍ መነቃቀፍ መጥለፍ መጠላለፍ ሁሉ አዋቂ የበሬ ዕቃ ሁሉ አለቃ መሪ መፍጠር የማይችል ከመተባበር መደናበር የሚበዛበት የደንቆሮዎች ስብስብ ብቻ ነው ።
ገበሬው ኢትዮጵያዊው መሪውን መፍጥር ያውቃል የሚሉትን ይሰማል ።
” ምሁሩ ” አይ ” ምሁሩ ” !!!
እነ ጆርጅ ዋሽንግቶን ፣ እነ አብርሃም ሊንኮን እንደ አሜሪካ ያለች ውብ ሀገር ለሰው ልጅ መኖሪያ ምቹ እንድትሆን የፈጠሩት ሁሉን ተጋፍጠው የሚጠይቀውን የወቅቱን መስዋዕት ከፍለው እጅግ አስከፊ ጦርነቶችን ተቋቁመው እንጅ እንዳሁኑ ምሁር የበላ ይብላይ ብሎ ሀገሩን ጥሎ የሚኮበልል አይደለም ” ምሁሩ ” ብሎ ራሱን መጥራቱ አስቂኝ ከመሆኑም በተጨማሪ እንቆቅልሽም ነው የሚሆንብን ።

Eshete Kassa Zewudie's photo.