መስቀል ፍላወር
14494622_10154009811787517_350119314488513967_n·
part 2
አያቱ ቀኛዝማች ፅጌ ከግዞት ሲመለሱ አስራትን ወደ አዲስ አበባ አመጧቸው። አያትና አስራት እንግዲህ እንደ ጓደኛ ሆነው በየትም ቦታ የማይለያዩ ሆኑ። ያን ጊዜ በየአደባባዩ ሬድዮ ነበርና አያት አስራትን ከሰው ጋር ይልኳቸዋል። በሚገር ሁኔታ የተባለውን አንድ ሳያዛንፉ ለአያት ይነግሯቸዋል። በችሎታው የሚደነቁት አያት ቤተሰብ ሲጣላ እያሟገቱ “ና! ፍረድ” ይሏቸዋል። አስራት በመሰላቸው ይበይናሉ። ቀኛዝማች የተሳሳቱትን አስተካክለው፤ ልክ በሆነው ያሞግሷቸዋል። በዚህም የተነሳ የህግ ጉዳይ በአእምሯቸው ይቀረፅ ጀመረ። እኚያ አያቱ በየመንገዱ ሲሄዱ በክርስትና ስማቸው ‘መላከ ብርሃን’ ብለው ይጠሯቸውና፤ “ሃገራችን ጥበብ የሚያውቁ ሰዎች ቢኖሯት እኮ ትልቅ ሃገር ነበረች።” ይሏቸዋል። በህፃን አእምሯቸው ነገሩ ባይገባቸውም፤ ስለ ጥበብ የማወቅ ጉጉት በመንፈሳቸው ውስጥ ያኔ ተጫረ። “መላከ ብርሃን! ሃገራችን እኮ የማይናቅ ህዝብ እና ባህል ያላት እኮ ናት።” ይሏቸዋል። በዚህም የወገንና የሃገር ፍቅር በልባቸው አደረ። የፕሮፌሰር አስራትን ስብእና የቀረፁት እኚህ አያታቸው ነበሩ ማለት ይቻላል።
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
ነፃነት ሲመለስ አስራት ተፈሪ መኮንን ት/ቤት ገቡ። የዛን ጊዜ የትምህርት ደረጃ እንደዛሬው አልነበረም። እስከ ሰላሳ የሚሆኑ ክፍሎች ሲኖሩ፤ ጎበዝ የሆነው ተማሪ ከሰላሳ ዝቅ እያለ 29፣ 28፣ 27፣ 26…. እያለ ከክፍል ክፍል ይሸጋገራል። ታድያ አስራት ሆዬ ንባብ ሲጠየቁ ፉት ነው፤ መፃፍ ሲጠየቁ ግጥም ነው፤ በአንዴ ወደ 13ኛ ክፍል ጥልቅ አሉ። በዝያው አመት ከተማሪዎች በሙሉ ልቀው ወደ1ኛ ክፍል ተሸጋገሩ። ከት/ቤቱም አንደኛ ወጡና ካሜራ ተሸለሙ። አረ እንዲያውም የውጭ ሃገር ትምህርት እድል አገኙ! እና ግብፅ እስክንድሪያ ተላኩ።
Image may contain: 1 person