ሐመረ ኖኅ

የወረታ ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል የቅኔ ጉባኤ ቤት የማኀበር ቤት በመፍረሱ ተማሪዎች ለመማር መቸገራቸው ተገለጸ

 

የጉባኤ ቤት በከፊል

የጉባኤ ቤት በከፊል

በደቡብ ጎንደር ሀገረ ሰብከት   ከሚገኙት ታላለቅ ጉበኤ ቤቶች  በወረታ ከተማ  ያለው  የወረታ ደብረ ብስራት ቅዱስ  ገብርኤል   የቅኔ ጉባኤ ቤት  አንዱ  ነው፡፡፡

የወረታ ደብረ ብስራት የቅኔ ጉባኤ ቤት በጣም ታላለቅ የአብነት መምህራን ያፈራ አሁንም በማፍራት ላይ የሚገኝ ጉባኤ ቤት ነው፡፡መምህሩም ሊቀጠበብት መሠረት ዓለሙ  አብነቱ   ያለአብነት እንዳይቀር  እየተጉ የሚገኙ ታላቅ የጸሎት አባት ናቸው፡፡

ሊቀጠበብት መሠረት ዓለሙን

               ሊቀጠበብት መሠረት ዓለሙን

ሊቀጠበብት መሠረት ዓለሙ   ቅኔ፤  ቅዳሴማርያምና ውዳሴ ማርያም  ፤መጽሐፈ ነገሥት፡ዳዊት አንደምታ፡ባሕር ሐሳብ ያሰተምራሉ፡፡ ምንም እንኳን  ቢያማቸውም  ወንበር አያጥፉም ፡፡ለተማሪዎቻቸው   ልዩ የሆነ ፍቅር  አላቸው፡፡

ሊቀጠበብት  መሠረት ዓለሙ   በ13/11/2008  ዓ.ም  በተንቀሳቃሽ  ስልክ በጠዋቱ ደውለው  አለቀሱብኝም ፡፡ምነው  የኔታ  ስላቸው” የጉባኤ  ቤቱ የማኀበር   ቤት  ሣር ስለነበረ ክዳኑ  በመፍረሱ ተማሪዎች ለመማር  ተቸግረው አይቼ ነው” አሉኝ ፡፡ እኔም ታላቁ  የቤተ ክርስቲያን አባት እንዲህ ሲሉ   ምን ላድርግ ብየ ከሕሌናየ ጋር መታገል ጀመርኩኝ ፡፡

ሊቀጠበብት  መሠረት ዓለሙም     የጉባኤ ቤት   የማኀበር ቤት 40( አርባ)  ዜንጎ  ቆርቆሮ እንደሚፈጅም ጠየቁኝ   እባካችሁ እንዲህ ዐይነቱን ጉባኤ ቤት ከመፍረሱ   የቅኔ  ተማሪዎችም     ከመበተናቸው  በፊት   ጉባኤ   ቤቱን  እንታደጋቸው የዐቅማችን እንገዛቸው  ለማለት በሐመረ ኖኀ ጻፍኩት፡፡ዐቅም ቢኖረኝ  እኔ በሰራሁት  ግን አልቻልኩም   ውስጤ  በኀዘን  ተነካ  ምክንያቱም የወደፊቱ የቤተ ክርስቲያናችን  ተስፋዎች   ከእንዲህ ዐይነት  ጉባኤ  ቤት የሚወጡ ደቀ- መዛሙርት  ናቸውና ጳጳሳት፤ቀሳውስት ና ዲያቆናት የሚሆኑት፡፡

መንፈሳዊ ቅናት ያላችሁ ፤በበረከት ለመጎብኘት ያሰባችሁ ፡፡የሊቀጠበብት መሠረት ዓለሙ ስልክ  0918379809  ነው  ደውላችሁ የበለጠ መረጃ ማግኘት ትችላላችሁ፡፡ ተማሪዎች ከመበተናቸው  በፊት የማኀበር ቤቱን ተማሪዎች  ውዳሴ ማርያም የሚያድርሱበት ፤ለሀገረ፤ለሕዘብ   ሰላም የሚጸልዩበት  አዳራሽ ነው፡፡  ጋን  በጠጠር ይደገፋልና እንተባበርና እንስራው ፡፡