ሳሙኤል አወቀ ማነው ??

( ሰለ ሳሙኤል ማንነት ለማወቅ በጠየቃችሁት መሰረት ይህን አጭር ጽሁፍ አቅርበናል። በዚህ ጽሁፍ ለተባበረኛ ለ GetachewShiferaw ታላቅ ምስጋና አቀርልለሁ ። )
ሳሙኤል አወቀ አለም ከአባቱ በምስራቅ ጎጃም ዞን ጎንቻ ሲሲነሴ ወረዳ ሰቀላ ገምቦሬ ቀበሌ ማህሉ በተባለች መንደር መስረም 24/1978 ከአቶ አወቀ አለም እና ከእናቱ ከወይዘሮ በላይነሽ አለሙ ዓ.ም ተወለደ፡፡
ሳሙኤል የመጀመሪያ ትምህርቱን እነጎዴ የመጀመሪያ ትምህርት ቤት፣ 7ና 8ኛ ክፍል ትምህርቱን ፣ ግንደወይን እምዲሁም 9ና 10ኛ ክፍል ትምህርቱን በደብረወርቅ ከተማ ተከታትሏል፡፡ ከዚህ በኋላ በህግ ዲፕሎማውን ከወይዘሮ ስሂን ኮሌጅ አግኝቷል፡፡ ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ በህግ ዲግሪውን እየተባለ የነበር ሲሆን በዚህ ዓመት (2008) ይመረቅ ነበር፡፡
2002 ዓ.ም ፈቃድ አውጥቶ ጠበቃ ከመሆኑ በፊት በተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ሰርቷል፡፡ ከጠበቃነቱ በፊት በእናርጅ እናውጋ የግብርና ፅ/ቤት ነገረፈጅ ሆኖ አገልግሏል፡፡ ለቤተሰቦቹ ሶስተኛ ልጅ የሆነው ሳሙኤል አወቀ ቦተሰቦቹን ሲያግዝ የነበር ሲሆን ከ2002 ዓ.ም ጀምሮ በጀመረው የጥብቅና ስራውም የአካባቢውን ህዝብ ሲያገለግል ቆይቷል፡፡ በተለይ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ እያለ በ1997 ዓ.ም የቅንጅት አባል ከሆነ በኋላ በህዝብ ላይ የሚደርሰውን በደል ለሚዲያ በማጋለጥ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች አጀንዳ እንዲያደርጉት በመግለፅ ሲታገል ቆይቷል፡፡ በሙያውም ህዝቡን አገልግሏል፡፡ ቅንጅት ከፈረሰ በኋላ የአንድነት መስራች አባል ሆኖ የቀጠለ ሲሆን ሰማያዊ ፓርቲ ሲመሰረትም መስራች አባል ሆኖ ቀጥሏል፡፡
በሰማያዊ ፓርቲ የዞኑ አመራር ዋና ፀኃፊ የነበረው ወጣት ሳሙኤል ህዝቡ ሰማያዊን እንዲቀላቀል የላቀ ሚና እንደነበረው የዘኑ አመራሮች ይመሰክራሉ፡፡ ሳሙኤል አወቀ በአካባቢው ህዝብ የሚደርሰውን በደል ለሚዲያ እንዲደርስ በማድረግ ትልቅ ሚና የተጫወተ ሲሆን የነገረ ኢትዮጵያ አምደኛ፣ ከመሆኑም ባሻገር ለኢሳት፣ ህብር ሬድዮ፣ ለቪዮኤና ለሌሎችም ሚዲያዎች በቀናነት መረጃዎችን በማቀበል የህዝቡን በደል ሲያጋልጥ ቆቷል፡፡
የህዝብን በደል ለሚዲያ በማድረስኑ በፓርቲው ጠንካራ እንቅስቃሴ በማድረጉም ከዞኑ አመራሮች ከፍተኛ ዛቻ ሲደርሰበት ቆይቷል፡፡ ለአብነት ያህልም የምስራቅ ጎጃም ዞን ፍትህ ቢሮ በ2006 ዓ.ም የእቅድ ግምገማ እና የ2007 ዓ.ም የስራ አፈጻጸም እቅድ በተወያየበት እና የሁሉም ጽ/ቤት ኃላፊዎችና የስራ ሂደት ባለቤቶች በተገኙበት፣ ‹‹ሳሙኤል አወቀ የሚባል በጥብቅና ሽፋን የመሬት ፖሊሲውን የሚታገል፣ ለተቃዋሚ ፓርቲ አባላትና ደጋፊ አርሶ አደሮች ጥብቅና የሚቆም፣ ከአሸባሪ ጋር ግንኙነት ባለው ድርጅት አመራር የሆነን ግለሰብ በህግ ሽፋን እስር ቤት እንዲወርድ ያላደረገ አቃቤ ህግ አቃቤ ህግ አይደለም›› ተብሎ በህግ ስም እርምጃ እንዲወሰድበት ትዕዛዝ መተላለፉን ሳሙኤል ለነገረ ኢትዮጵያ ገልፆ ነበር፡፡
በተለይ የደብረማርቆስ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት አቃቤ ህጎች ዋነኛ ችግራቸው ጠበቃ ሳሙኤልን በህግ ስም ማስቀጣት አለመቻላቸው እንደሆነ ተገምግመዋል፡፡ ጠበቃው ወዲያውኑ የፈጠራ ክስ እንደተመሰረተበት፣ የክልሉ ፍትህ ቢሮ ኃላፊ ‹‹ለፍትህ ስርዓቱ አጋዥ ባለመሆኑ›› በሚል መከሰሱንና ባልተከራከረበት ፍርድ ሂደትም 8000 ብር ቅጣት እንዲከፍልም ተወስኖቦታል፡፡

ወጣት ሳሙኤል እናርጅ እናውጋ ለቀጠሮ ባቀናበት ወቅትም የእናርጅ እናውጋ አስተዳደርና ጸጥታ ኃላፊ አቶ ስራው በረኩ እና የብአዴን የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አቶ መኳንንት አበበ እና ሌሎችም ከፖሊስና ከጸጥታ የመጡ አመራሮች ‹‹ምን ልታደርግ ነው? ልትቀሰቅስ ነው?›› በሚል እንዳዋከቡትና አቶ ስራው በረኩ ‹‹አንጠልጥዬ ነው እስር ቤት የማስገባህ፡፡ ማንም ሊያድንህ አይችልም›› ብለው እንደዛቱበት ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡

‹‹የሰማያዊ ፓርቲ አባል ሆነህ በፍትህ ስርዓቱ መገልገል አትችልም፣ ጥብቅናህን መልቀቅ አለብህ፣ ነገረ ኢትዮጵያ ላይ ትጽፋለህ፣ የፍትህ መምሪያ ሃላፊውን (ጸጋየ መንግስቴ) ችግር እንደሚፈጽምብህ በነገረ ኢትዮጵያና በሰንደቅ ጋዜጣ ላይ ጽፈህበታል፣ እንዲህ እያደረክ መኖር አትችልም፣ አንተን ገሎ መጣል ቀላል ነው፣ ለነፍስህ የምታዝን ከሆነ አገር ልቅቅ›› ብለው እንደዛቱበት በወቅቱ ገልጾ ነበር፡፡
ሌሎች ጠበቃ ጓደኞቹ ከእሱ ጋር እንዳይሄዱ ‹‹እሱ ማለት ሰማያዊ ነው፡፡ ሰማያዊ ደግሞ የአክራሪ ሙስሊም ፓርቲ ነው፡፡ እናንተ ለምን ከእሱ ጋር ትሄዳላችሁ?›› ብለው እንደሚያስፈራሯቸውና ደንበኞቹ ከእሱ ጋር እንዳይሰሩ ማስጠንቀቂያ እንደሚደርሳቸው ሳሙኤል በወቅቱ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡ ሳሙኤል የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት የሰማያዊ ፓርቲ አመራርና አባል ሆነው ማደራጀት መብታቸው መሆኑን ሲገልጹ የብአዴን አመራሮች ‹‹እናንተ እኛን ስለማትረዱን ነው፡፡ እኛ ጋር ሰላማዊ ትግል የሚባል አይሰራም፡፡ ወንድ ከሆናችሁ ጫካ ገብታችሁ ሞክሩን›› በሚል ለህግ የማይገዙና ለሰላማዊ ትግል ቁርጠኝነት እንደሌላቸው አሳይተውናል ብለዋል፡፡
ወጣት ሳሙኤል በወቅቲ የገዥው ፓርቲ ዛቻና ማስፈራሪያ እንዲሁም እርምጃዎች እየተጠናከሩ ቢሆንም እርምጃው ፓርቲው ተጽዕኖ በመፍጠራቸው የመጣ በመሆኑ ይበልጡን እንደሚያበረታታውና የሚከፈለውን መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆኑን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
ሳሙኤል የሰማያዊ ፓርቲ አባል ነህ በሚል ‹‹አገር ጥለህ ውጣ፣ ካልሆነ እንገድልሃለን›› የሚል ማስፈራሪያም ደርሶት ነበር፡፡
ከዚህ ባሻገር ሳሙኤል የሚሰራበት ፍርድ ቤት ውስጥ ‹‹መንግስት ያቋቋመው ፍርድ ቤት በአግባቡ ለህዝብ አገልግሎት መስጠት ሲገባው ሙስና እየተሰራ ስለሆነ ሊመረመር ይገባዋል›› በሚል የተሰጠን የህዝብ አስተያየት የአንተ ነው በሚል ማስፈራሪያ ደርሶበታል፡፡ ከማስፈራሪያው ባሻገር ክስም ተመስርቶበት ነበር፡፡
ፖሊስና ደህንነቶች በተደጋጋሚ ጊዜ ‹‹ይዛችሁ አምጡት!›› እየተባሉ የፖለሲና ሌሎች አመራሮች ማስፈራሪያና ዛቻ አድርሰውበታል፡፡ ይሁንና ሳሙኤል አወቀ እንደማይሰደድና ትግሉንም እንደሚቀጥል በማህበራዊ ድረ ገፅና ነገረ ኢትዮጵያ ጋዜጣ ላይ ሲፅፍ ቆይቷል፡፡ ለአብነት ያህልም በአንድ ወቅት ከስር ዛቻው ሲብስበት ነገረ ኢትዮጵያ ላይ የሚከተለውን ፅሁፍ ፅፎ ነበር፡፡
አልሰደድም! ትግሌንም አላቆምም!
ሳሙኤል አወቀ
(ከደብረ ማርቆስ)
ከዚህ ቀደም የሰማያዊ ፓርቲ አባል መሆኔን ካላቆምኩ እስከ ግድያ የሚደርስ እርምጃ እንደሚወሰድብኝ እና ይህ ከመሆኑ በፊት ከሀገር አንድወጣ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶኝ ነበር፡፡ ይህን ባለመቀበሌም ተደጋጋሚ አሳፋሪ የውንጀላ ክሶችን ሳስተናግድ ቆይቻለሁ፡፡ በጥብቅና ሙያየ አገለግሎት አንዳልሰጥ እና ሰርቸ እንዳልበላ ተረጋግቼ በሰላም እንዳልኖር የተከፈተብኝ ዘመቻ ቀላላ የሚባል ባይሆንም ይህንን ተቋቁሜ መስራቴ ያበሳጫቸው የኢህአዴግ ካድሬ ዳኞች ደግሞ በህግ አራዊትነት አስሮ ለማሰቃየትና እንዲሁም ከህዝብ በተሰወረ ሁኔታ ወደ ሌላ ወረዳ ማለትም ባሶ ሊበን ወረዳ /የጁቤ/ ታስሬ እንድቀርብ በፖሊስ የእስር ትዕዛዝ ወጥቶብኛል፡፡
ምንጮቼ እንዳረጋገጡልኝ የእስራቱ ምክንያት ደምበኛዬ /የወከለችኝ/ ግለሰብ ኪሳራ 2ዐዐ /ሀለት መቶ/ ብር ስላለባት ያለምንም ክስ እና መጥሪያ በመዝገቡ ላይ እንድታሰር እና ከተሰቃየሁ በኋላ በይግባኝ እንድለቀቅ የታቀደ መሆኑን ለማረጋገጥ ችያለሁ፡፡ ጠበቃ ደምበኛውን ወክሎ የህግ አገልግሎት መስጠት እና ክርክር ማድረግ እንጅ ደምበኛውን ወክሎ ወይም ተተክቶ ሊታሰር የሚችልበትም ሆነ ገንዘብ ሊከፍል የሚችልበት ምንም ዓይነት የህግ አግባብ ካለመኖሩም በላይ የህግ ድርጊት ለመጀመሪያ ጊዜ በእኔ ላይ የተፈፀመ መሆኑን በሃገሬ የፍርድ ቤት ነፃነት እና የዳኞች ገለልተኛነት እንዳሰፍን እንዲሁም የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ የአፓርታይድን ችሎት በማስታወስ ትግሌን እቀጥላለሁ፡፡
አልሰደድም!
ትግሌንም አላቆምም! ፍትህ! ነፃነት! እኩልነት!
ለአፋኝ የኢህአዴግ ካድሬዎች ሁሉ እንዲረጋገጥ የገበሁትን የትግል ቃልኪዳን እፈፅማለሁ፡፡
ሰኔ 8 ቀን 2007 ዓ.ም ምሽት ወደ ቤቱ በመግባት ላይ ሳለም በሁለት ግለሰቦች ከፍተኛ ተደብድቦ የተገደለው ወጣት ሳሙኤል አወቀ ከመገደሉ ሁለት ሳምንት በፊትም ‹‹ትግሌን አደራ›› በሚል በፌስ ቡክ ገፁ ፅፎ እንደነበር ይታወሳል፡፡
ሌሎች የሳሙኤል አወቀ መልዕክቶች
Samuel Awoke
May 31 at 11:56am •
ስለ የግፍ እሰራት እና አፈና ሰለፃፍኩት የደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ ኢሕአዴግ ኮሚቴ ” በዚህ ሳምንት አንተም ትገባለሕ ” ብሎ ዛተብኝ በጣም ገረመኝ እኔ ዜግኘቴ ኢትዮጵያውያን መሀኔን እንኳ ረሳው ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ለዚህ ግፈኛ ሥርዓት አባል መሆናችሁን እንድታውቁት ኮሜንቱንም ያየ ላላየ እንዲያሳይ በአክብሮት እያሳስብሁ ይሕን ዓይነት ዘረኛ አፈና አምርረን ታግለን ለነፃነታችን እንድንበቃ አሳስባለሁ!!!
May 31 at 9:58am •
ግን ኢሕአዴግ ምን ሆኖ ነው? ድንብርብር ያለበት መፍትሔ ያለውስ ማሰር ፤ ማሰቃየት ፤ ማፈናቀል ፤ ማፈን ፤ መሠወር ፤ ምርጫ መስረቅ ምንሆኖነው ግን ? የኢሕአዴግ አባል እና ደሕንነት ብቻ መኖሪያ ናት ኢትዮጵያ ???? ወጣቶች ን ማሠር ፣ማፈን ፤ መሳደድ የነጨረሻ አማራጭ ነው ግን ኢሕአዴግ ሆይ እኔ እኮ ሰፈጠር ኢትዮጵያውያን መሆን ፈልጌ አይደለም አረ ሌላ እናንት ኢሕአዴግ የሖናችሁትን የማናይበት አገር ካለ ውሰዱን ያኔ ምፅዐተ – ኢትዮጵያ እንፈጥራለን ፤ሕዝብ የታሰረበት አገር አገረ ኢትዮጵያ አዲሱን አንሰቸ ማንን ልተወው እኔ እኮ ትዝ ያለኝ ሰው ሲሞት ቀድሞ የሞቱትን እየጠሩ በሐዘን የማንባቱ ነገር ነው!!! የኢሕአዴግ አባላት ደርጅታችሑ ዘር እያጠፋመሆኑን ግን ታውቃላችሁ !!! እስከ መቼ???
Samuel Awoke
May 3 •
ወገኖቸ!!! በሰልክ፣በአካል፣በመሕበራዊሚዲያ ላደረጋችሁልኝ የመራል ድጋፍ እግዚአብሔርይ ስጥልኝ!!!!! ቃላት ያጥረኛል! ያለሁትበ ጭራቅ ሰወ በላ የኢሕአዴግ ሥርዓት ቢሆንም በጨዋው ወገኔ ኮርቻለሁ!!!!! በመደብቤ አላዝንም፤በመትረፌ ደሰተኛነኝ!!! ደጋፊዎች በምንም መንገድ ትግሉ እንደማይቀለበስ አውቃችሁ በምርጫ ኢሕአዴግን ቅጡ!!!!!!!! ያኔ ይማራሉ!!! ደበዳቢዎቸ አንደሰው እንጅ እንደአራዊት እንዳታሰቡ እመክራችኀለሁ!!! እኔ ግን አዝንላችኋለሁ እንጅ አላዝንም የሥርአቱ አሜከላናችሁ እና ከፖለቲካም በላይ ሰውን እና ሰብአዊነትን ፈጣሪንም አትርሱ እኔ የምታገለው ለናንተም ለልጆቻችሁም መሆኑን አትርሱ!!! አንተ የማላወቅህ ግን በዚያ ሰዓት ከነዚያ አውሬዎች አሰጥለህ በመኪናሕ ወሰደሕ ሕይወቴን የተረፍካትሰው አመሰግንኃለሁ አሁንም ካላረፍክ አንገደድልኃለን የምተሉኝ ጌቶች አናንተ ሁልግዜ ገዳዮች እና ዘላለማዊ ሰለመሆናችሁ አርግጠኞች አይደላችሁም እላችኋለሁ። ግን ኢሕአዴግ ዘላለማዊ የጨለማ ገዥ ሰለመሆኑ እርግጠኞች ናችሁ??? ግን አይደለም!!!! የቀማችሁኝ ገዘብ እንናንተ ከሕዝብ የቦጨኩት ሳይሆን ነጭ ላብ ያፈስሁበት ነው!!!
#menber kassay