‪#‎Shagiz‬/ እሸቱ /
ግራ የተጋባን ሁኔታዎችን ያልተረዳን
#=========[[[[[[========>>>
የአማራ ሕዝብ ተብለን የተሰየምን ።
ሕውሓትን ማንነት ያልተረዳን አማራ ነን እንላለን ከአማራነታችን ኢትዮጵያዊነት የሚቀድምብን ።
ነነገር ግን እኛ አማራ የተባልን ያች የምናልማት ታላቋን ሀገር ኢትዮጵያን እንዴት መጠበቅ እንዳለብን የማናውቅ ጠላታችንን በውል ያልተረዳን ።
አማራ ናችሁ የተባልን ለኢትዮጵያ ቀርቶ የራሳችን መብትና ሕልውናም እንዴት ማስበቅና መከላከል ያልቻልን ከፍተኛ ሽንፈት የደረሰብን ያን ሽንፈታችን ለመቀበል እንደ ኮሶ የሚመረን እየሞትን እየተሰደድን እየተወረስን በሀገር ባይተዋር ሁነን አሁንም የበላይነቱ ስሜት ያለን Shagiz Shagi's photo.
ይህ ስሜት መቀጠል ያለበት መጠበቅ ያለበት ቢሆንም ጠላታችን ሕውሓት በተናጠል እየበላን እየበላን እየጨረሰን እንደሆነ ማመንም አለብን እየሞቱ ማቅራራት ሳይሆን ብሶት ለመግለፅ እንጉርጉሮ መሆን ሲገባ እየሞቱ ፉከራ ባሕላችን አይደለም ።
እኛ አማራ የተባልን በባዶ እግሩ የሚሄድ አርሶ አደሩ ገበሬ ለ40 ዘመን በዘረኛው ሕውሓት እየተፈፀመበት ያለውን የዘር ማጥፋት ልንደርስለት ቀርቶ ስለሚፈናቀሉ ስለሚታፈኑ ስለሚገደሉት ቦታ ና አካበሰቢ በስም ጠቅሰን ስንናገር በደረጃ መዳቢ የአማራው ምሁር ነን በሚሉ ከደረጃ ወርደን ድምፃችን የሚቀበለን የለም ።
እውነታውን ለመግለፅ ያ የሀገር ቤቱ አርሶ አደር በራሱ ቋንቋ የተናገረው በቂ መረጃ ነው ።
ስለሚፈፀሙ ወንጀሎች የት እንደሚፈፀሙ በተጋጋሚ ስለሰሜን ጎንደር በመግለፃችን እኩል እንደ ሕውሓት ዘረኞች ጠባቦች ተብለን በራሳችን ሰዎች ከደረጃ ዝቅ ብለን የተመደብን አለን ።
አሁን በወልቃይት ላይ እየተፈፀመ ያለውን እድሜ ለኢሳት ሚዲያ በመገለፁ ሁሉ ታኩረት ይስጠው እንጅ ስለወልቃይትና ጠገዴ ስለ አርማጭሆ መተማና ቋራ ብዙ እጅግ ብዙ ብለናል ።
እንደዕድል ሁኖ ፕ/ ር ማስተር ፣ባለ ዲግሪ ባለመሆናችን በተጨማሪም ሁሌም ጎንደር እያልን በመፃፋችን ከጅምሩ ጀምንለው ሁሉ የቁራ ጩኸት የሆነብን እንዳለን አሁንም አለን ።
በሰሜን ጎንደር የወልቃይት ፣ የጠገዴን ፣የጠለምትን ፣ የወገራን የአርማጭሆን ሕዝብ ይቃወማል የተባለው ሁሉ ሴት ወንድ ሳይለይ እየታፈኑ የሚገደሉበት በትግራይ ከመሬት በታች የተሰሩለት የሞት ካንፖች አሉት ።
ስለዚህ ቦታ ጠቅሸ ስለጎንደር ብፅፍ የት ላይ ነወረ ስህተቱ?
ከኢትዮጵያዊነቴ ሊያወርደኝ የሚችለው?
በጠላት ወረራ ወቅት መገናኛ ባልነበረበት ወቅት ሁሉ በአካባቢው ተደራጅቶ ነበር ሀገሪቱን ከወራሪው ፋሽሽት ያወጧት ፣ አሁን ላይ በየአካባቢው እየተደራጁ አቅም በመፍጠር ጠቅላላ ሀገራችንን ነፃ ለማውጣተረ የሚያስለንን ዘዴ እኛው እራሳችን እየጠላን የግድ አንድ እንሁን ተብሎ እየተነገረ እራሳች አንድ ሰሰንሆን የአንድነት ናፋቂዎች አንድነት ራሱን መከላከል የሚችልበት አቅም መፍጠር የግድ ነው ያ የአንድነት አቅም ደግሞ በማንኛውም ቦታ ተወልዶና አድጎ አላማው ሕዝብ የሚቀበለው ከሆነ በኦሮሞ ሕዝብ ይሁን በጋንቤላው በአፋሩም ይሁን በሱማሌው ይጀመር ሕዝባዊ አላማ ከያዘ ሁሉም አቅም የሰነሰው ሁሉ መጠለያማ ደጀን መሆን የበቃ ድርጅት የግድ መፈጠር አለበት ብለን እናምናለን ።
ውድ የሀገራችን ምሁራን የሕውሓት ሰለባ ከሆኑት ወገን ጋር የቅርብ ክትል ታደርጉ ዘንድ እንማፀናለን በወልቃይት በኩሉ ሕውሓት እየገፀመው ያለው የጠቅላላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጉዳይ ነው የወልቃይት የጠገዴ የጠለምት ፣የታች አርማጭሆ የመተማ የቋራ ሕዝብ ትግል ከተመታ የኢትዮጵያ ጉዳይ አለቀለት ማልት ነው ሕውሓት በ17 ዓመቱ የትግል ወቅት የአርማጭሆን መሬት እግሩ አልተረገጣትም ነበር ።
ምክንያት የወልቃይት ሕዝብ ከባድ መስዋዕት ብቻውን እየከፈለ ስለተከላከለ ነበር ሕውሓት ከሽሬ ተገዜን ተሻግሮ ጎንደርን መቆጣጠር ቢችል ኖሮ መንገዱ አጭር ይሆንለት ነበር ።
ነገር ግን በጠለንትና በወልቃይት ጠገዴ ማለፍ እንደማይችል ስለተረዳ በወሎ በኩል ረዥም መንገድ ወስዶ በደብብ ጎንር ከባድ ዋጋ ከፍል የጎጃምን ምድር ከተረገጠ በኋላ በሶስት ወር ባልሞላ ጊዜ አዲስ አበባን ተቆጣጠረ ።
ከዛም መላው ሀገሪቱን ከያዘ በኋላ የሰሜን ጎንደር መቆጣጠር ጀመረ የ17 ዓመቱን የቋጠረውን ቂም በቀል አሁንም ሳይቀር የሰሜን ጎንደር ሕዝብ እየከፈለ ይገኛል ።
ስለዚህ መናገር እንደነውር ተቆጥሮ የራሴያልኳቸው የቅርብ ጓደኞቸ ጭምር የማይዋጥላቸው እንዳሉ የማውቀው ጉዳይ ነው ።
ስንገናኝ ብዙ ክርክር ከማድረግም በተጨማሪ እስከማግለልም የተሄደበት አጋጠሚየም ብዙ ነው በዚህ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ በዙዎቹስ ከነጭራሹም ብሎክ ያደረጉኝም አሉ ።
ከአንድ ወገን ሁነን በአንዲት መርከብ የረሳፈርን ሰዎች እኔ በተረዳሁት ሀቅ ተነስቸ የሀሳብ ልዩነት እስከዚህ የሚያደርሰን ከሆነ ከሕውሓት በፊት እኛው በኛው ተጠላልፈን ከመውደቅ ባቫገር ያች የምንመኛት አንድነት እንዴት መምጣት እንደሰለበት እውነቱን ተነጋግረን መፍትሄ ካልፈለግን ህውሀቶች በዚህ ክፍተት እየገቡ ሁሌም ነገራችን አረንደሰያምር እያደረጉ እንደተለመደው የ50 ዓመቱ የፖለቲካ አዟሪት እየዳከርን እስከ ውድቀታችን ደጃፍ እየሄድን እንደሆን ይታየኛል ።
ሕውሓት የሚፈፅማቸው ሁሉ መነገር አለበት ምክንያት ስለባዶ ስድስት ብዙም ያልታወቀ ነው ለኢትዮጵያ ሕዝብ በሕውሓት እስካሁን የተፈፀሙት ከተነገሩ ለወደፊቱ ለፈፀሙ የታቀዱት ማስቀረት እንችላለን ስለባዶ ስድስት ብንቃወምኑሮ በማዕካላዊ አዲስ አበባ ያለው ገሀነም ለ25 ዓመት ምንም ሳይደናቀፍ ሥራውን አይቀጥልም ነበር ።
// እሸቱ ካሳ //

Shagiz Shagi's photo.Shagiz Shagi's photo.
LikeShow more reactions

Comment