ነግ ለኔ ነው ብሎ ማሰብ የሰው ልጅ ግዴታው ነው በሌሎች ላይ የተፈጸመው በኛ
_____________________________________________
አይፈጸምም ብሎ ማሰብ ዘበት ነው
____________________
ስለጀኖሳይድ ሳነሳ ይህ ሰው ምን ነካው ብላችሁ የምታስቡልኝ አንድም ስለኔ ጤንነት የምትጨነቁልኝ ያክል በዛው መጠን ደግሞ የሚረግሙኝ እናዳሉም አውቃለሁ።
በእስራኤል ምድር መኖር ከጀመርኩ በርካታ ዓመታትን አስቆጠርኩኝ ።
በእስራኤል ሀገር ኑሮየ ስለ ዘር ጭፍጨፋ ስለ ጥላቻ ፖለቲካ ብዙ መማር ችያለሁ ።
እስራኤላውያን እንደማንኛውም የሰው ዘር በምድር ላይ የመኖር መብት አላቸው ።
ነገር ግን በአውሮፓ ምድር መኖር አትችሉም ሀገራችሁ አይደለምና ዘራችሁን አጠፋለሁ ብሎ የጀርመን ናዚ በሂትለር የሚመራው ።
ምን ያላጠፉ ሕፃናትን ጭምር ከዛ በፊትም ያልነበረ ከዚህ በኋላም በሰው ዘር ላይ ይፈፀማል ተብሎ የማይታሰብ በከፍተኛ ጭካኔ በዙ ሚሊዬን ይሁዳውያን የሞት ካንፕ ተቋቁሞ እነሱን የሚፈጭ ማሽን ተተክሎ የሰው ልጅ እንደ አይጥ ለምርምር ሥራ የዋሉበት ነበር ።
ይህ በአውሮፓ ምድር ከስድስት ሚሊዬን በላይ የአውሮፓ ይሁዳውያን ይሁዲ ሁነው በመገኘታቸው ብቻ ተፈጁ።
በእስራኤል መኖሮ ከጀመርኩ ይዞ በየዓመቱ በዚች ወርህ ለተጨጨፈጨፉት የመታሰቢያ ቀን ይደረጋል በሀገረ እስራል በሙሉ ለበዓሉ መታሰቢያ የሀዘን ሳይረን ይሰማል ሰዎች በየአሉበት ይቆማሉ በሕሊና ፀሎት ይታሰባሉ ።
ከዚህ ባላይ የሙታኑ መታሰቢያ ከመደረጉShagiz Shagi's photo. በፊት በየመገናኛው ዘርፍ ከሞት የተረፉትን እያቀረቡ ታሪኩን እንዲናገሩ ይደረጋል ሁሌም የምንሰማው አዲስ አዲስ ታሪክን ነው ።
እናም በሀገራችን የሕውሓት ድርጅት የመለስ ሌጋሲ ይዞልን የመጣ ፖለቲካ በትክክል ከጀርመን ናዚዎች የተቀዳ ነው የሚመስለው ።
ናዚ ጀርመኖች በይሁዳውያን ላይ ይሰሩት የነበረው የማጥላላት ፕሮፖጋንዳው ከሕውሓት በአማራው ላይ በሥውርና በግልፅ የሚያካሂዱት ፕሮፖጋንዳ ተመሳሳይነት አለው ።
እንደማስበው ኢትዮጵያውያን የሽህ አመታት አብረን የመኖር እሴቱ አልጠፋ ብሎ ነው እንጅ እስካሁን እንደ ተሠራበት ኢትዮጵያ የብዙ ሚሊየኖች ሕይወት ይጠፋ ነበር ።
ጀርሞኖች አውሮፓ ለአውሮፓውያን የሚል መፎክር ነበር ።
ሕውሓት ኢትዮጵያ ለትግራይ ብቻ ብሎ አለማወጁ እንጅ በመላው ሀገሪቱ ያሉት የኢኮኖሚ ተቅዋማት ፣የሀገሪቱ የስልጣን ዘርፎች ፣የመከላከያው ፣የደህንነቱ በአንድ ዘር የበላይ ቁጥጥር የወደቀበት ፣ሕውሓት ከሕግም በላይ የሆነበት የፍትህ አካላት መቀለጃ ና የሰላማዊ ሕዝብን በሀገሩ መኖር እንዳይችል ማሳደጃ የሆነበት በጠረፍ በሚኖሩ አናሳ ጎሳዎች ተፈጥሮ የለገሰችላቸውን ተጠቅመው በሰላም ከሚኖሩበት የራሱ ዘር ወስዶ ለማስፈር የቁም ስቅል በነዋሪዎቹ ላይ ከማድረሱም ባሻገር ወደዘር ማጥፋት የተሸጋገረበት ፣
ሕውሀት የሀገር መከላከያ ብሎ የሚጠራው ሙሉ በሙሉ በአንድ ቋንቋ በሚናገሩ የሚታዘዘው ጦር ሀገር መጠበቅ ሳይሆን ሰላማዊ ዜጎችን እሴት ወንድ ሕፃናት አረጋውያን ነፍሰ ጡር እናቶችን ሳይለይ ደረትና ጭንቅላት የሚበረቅዙበት ሁኔታ እንዲሁ አይደለም በደንበር ተሻጋሪ ነፍሰ ገዳዮች ዜጎች ሲገደሉና ታፍነው ሲወሰዱ መከላከያ የሚባለው አልታዘዝነወም እየተባለ የሚታለፍበት ።
እውን ይህ አቅም ማጣት ወይስ ሌላ ምክንያት?
ምንም ሌላ ምክንያት የለውም ኢትዮጵያን አፍርሶ ሌላ አገር ለመመስረት የታለመ ብቻ እንደሆነ ይታየኛል ።
ሕውሓት የሚመራው መንግሥት ለዜጎች ደንታ የማይሰጥ በየትኛውም አለም ኢትዮጵያውያ በማንኛውም ዘመን ያልታየ የተሰደዱበት በየሄዱበት የሚታረዱና የሚዋረዱበት ነው ።
ታዲይ የሕውሓት መራሹ ጦር በጋንቤላ ስደተኛ ናቸው ብሎ ያሰፈራቸው የደቡብ ሱዳን የኑዌርሮች እንፈፈለጉ ዜጎችን የሚገድሉበት ዜጎች ራሳቸውን እንኳ እንዳይከላከሉ በአልሞ ተኳሽ የሚመቱበት ።
ምንም ሌላ ትርጉም የለውም
ሕውሓት ኢትዮጵያ ለኢትዮጵያውያን እንድትሆን አይሻም ተግባሮቹ ምስክር ናቸው ስለዚህ ይህ የዘር ፍጅት ደመና በሀገሬ ሰማይ ላይ አንዣቦ ይታየኛል ።
ሁላችንም ልናስብበት ሁላችንም በግልፅ ቋንቋ ድምፅ የምናሰማበት ወቅት አሁን ነው
የዘር ፍጅት ለይቶለት ከተጀመረ በኋላ ለማስቆም የሚችል ኃይል አይኖርም ።

Shagiz Shagi's photo.
Comments
Shagiz Shagi
Write a comment…
Kedir Abdu
Kedir Abdu ወዳጄ እውነት ብለሀል ጥላቻና በቀልን ዘርተህ መቼም በየትኛውም መለኪያ ሰላምን አታጭድም ።ስለሆነም ነው ሀገር ወዳድ ኢትዪጵያውያን አሁን ህወሀት እያራመደ ያለውን ብሄር ተኮር የጥላቻ ፖለቲካ ሊታረም ይገባል እያሉ ሚወተውቱት የሰማቸው ባይኖርም። ይባስ ብሎ አሁን ያሉት የዘውግ ፖለቲካ ከበርቴዎቻችን በ አፍቅሮተ ስልጣን ደንዝዘው እኛ ከለለን አማራውና ኦሮሞው ይተላለቃሉ ሲሉ ይደሰኩራሉ አብሮ ተሳስቦSee More

Unlike · Reply · 1 · 18 hrs

Twogo Melaku
Twogo Melaku · 19 mutual friends

Endeferedebet sayizegage anedinet eyale yemiyalkew Amharaw new , hulunim mayet new. Hayil yefetari new , esu yawkal! Amen .

Hailu G'Yohanes
Hailu G’Yohanes · 5 mutual friends

አስተዋይ አዕምሮ !!!