——ዕለተ ሰንበት 01/05/2016—
ትንሳኤ በዓል
#=========®=====∞===#
እንኳን አደረሰህ የሚል ፖስት ከአንዲት እህት ደረሰኝ በጓዳ በር በኩል ።
ብዙ ጊዜ እንደማደርገው በመጀመሪያ ፕሮፋይል ገብቸ ከላይ እስከታች በምን እስታይል ፌስቡክን እየተጠቀመበት መሆኑን ቸክ ማደረግ ልማዴ ነው ልማታዊ ወይም ሃይማኖታዊ አለዚያም መርዶ ነጋሪ የኔ ቢጤ መሆኑን የግድ ማወቅ አለብኝ ።
ካልሆነ ያለ ቢጤው ሰው ገብቶ ከፉናና ደጉን መስማቱ ያስቸግራል ያውም በ እለተ ትንሳኤው በተከበረ በዓል ።
እናም በፕሮፊሏ የተመለከትኩት መሀል የተቀመጠች መሆኗን ወደ አንድ ወገን ያላጋደለች ትመስላለች የተጠቀመችበት ፎቶ ግራፍ የራሷ መሆኑንም አረጋግጫለሁ ያ ከሆነ ደግሞ ሥሟም የራሷ መሆኑን ገመትኩ ።
የሥም ነገር በአሁኑ ሰዓት ጣጣ መፍጠሩም አልቀረም ስለ ስም አወጣጧም ማሰብ ጀመርኩ በአባቷ በኩሉ ከኢትዮጵያ የብዙውን ቁጥር ከያዘው ማሕበረ ሰብ እንደሆነ አወቅሁ የራሷ ስምላይ ግን ጥርጥ ር ቢኖረኝም አይ እኔስ ለምን እንኳን አበሮ አደረሰን አልልም አልኩና ያነኑን አደረግሁት ።
ከዚያማ ጉዱ ፈላ ነው የምላችሁ !
አንተ ለመሆኑ በዓል ታከብራለህ?
አለችን! ወይኔ ጉዴ ይች ልጅ ታውቀኝአለች እንዴ ?
ዘወር ዘወር ብየ ተመለከትኩ ከቅርብ ሁና የምታየኝ የምታውቀኝ መሰለችኝ ።
ደግነቱ ከአካባቢየ ሰው አልነበረምና ተረጋጋሁ ።
ይች ልጅ አልተሳሳተች ብዙም ስለ ዕምነት አልታማም እምነት የግል ጉዳይ ነው ብየ አስባለሁ ።
እናም ምነው እህቴ በፋሲካው በዓል እንዲህ መዓት የምታወርጅብኝ አልኳት?
ቀጠል አረገችና የምትፀፈውና የምትለጥፈው ጥሩ አይደለም አለችኝ ።
እኔ ተቻኮለወኩና የነስም አይጠሬ የሥጋ ዘመድ እንደሆነች አስረዳኋት ።
አይደለሁም ብላ እንደ ቅዱስ ጴጥሮስ ምላ ካደች እኔም ሳላምናት ከአቅሟ በላይ የሆኑ ነገሮችን አዥጎደጎድኩባት ልጅቷ ግን ደግና አስተዋይ አዕምሮ ያላት ትዕግሥት የተላበሰች ነገር ነች አዳመጠችን አላቋረጠችኝም እኔ ትዕግሥቷን ሳይ ልጓሜን ያዝ አደረግሁና ማሰብ ጀመርኩ
በፍፁም አንተ እንደምትለው ሳይሆን የናንተ ጩኸት ሰውን ከማስጨረስ የሚፈይደው ነገር ስለለ ነው አለችን
᎓ አባባሏ ልክ ቢሆንም አልተቀበልኩትም ስለዚህ ዝም ብሎ እንደበግ ታረዱ እያልች ነው ስላት ፣
አይደለም አለችኝ ፣
እናስ ምን ይሁን አልኳት ?፣
ስለአንድነት ይወራል ነገር ግን እንኳን ሌላውን አንድ ልታደርጉት እራሳችሁ መቸ አንድ ናችሁ? አለችኝ ደነገጥኩ !
ከማን ጋር አያወራሁ ነው ብየ ሌላ ሀሳብ ማውጠንጠን ጀመርኩ ከዛም ሌላ ሃሳብ ለቀጣዩ መልስ መዘጋጀት ጀመርኩ ከንፈሬን ሰብሰብ ምራቄን መዋጥ ጀመርኩ በጣም ጓጓሁ (ኢንተረስትድ) ቀጠለች ።
አንድነት እንዴት ነው ከግለኝነት ጋር አብረው የሚሄዱት ? አለችኝ
_ አሁንም ፈታኝ ጥያቄ ።
አንድ ሰው መታገል ሲጀምር ማንኛውንም መስዋዕት ትግሉ የሚጠይቀውን ለመክፈል የተዘጋጀ ሳይሆን ከመካከሉ ሌሎች ዋጋ እንዲከፍሉለት ካሰበ እንዴት ለዓላማው ፀንቶ ይቆማል ?
* የዘመኑ ትውልድ በጣም አስቸጋሪ ነው ብሔራዊ ወኔው ተሰልቧል ሀሞቱ ፈሷል ሞራሉም ወድቋል ታዲያ ማነን ይዞ ጉዞ ይሉሀል ይህ ነው ። አለችኝ
ወጣቱ ሀገር ተረካቢው ስደት ምርጫው አድርጎ ስደት ሰንቆ የተቀመጠ ነው ።
ለሀገሩ ለጋራ ጥቅም ፣ ለጋራ መብት ፣ ለጋራ ነፃነት ታግሎ ከመሞት ይልቅ ወደየመን ወደ ደቡብ አፍሪካ ወደ ሱዳን ሊቪያ ተጉዞ ከዛ ከመንገድ ውኃ ውስጥ ገብቶ መሞትን ካልሆነም ውኃውን ቢሻገር ከዘመኑ ጭራቅ አረባውያንና ከኛው ከውስጣችን በወጡ ከሀድያይን እንደደሮ ተበልተው የውስጥ አካላቸው በብዙ ዶላር ተሽጦ ለበላዔስ መክበሪያ ይሆናል ።
ለዚህ ነው የዘመኑን ትግል አልዋጥልኝ አልታይህም ያለኝ አለችኝ
**** ታዲያ ለዚች ወጣት አጋጨ ቀልጥፎ ብዙ በዘባረቅሁ ሀፍረት ቢጤ ቢሰማኝም ቶሎ ብየ ማመንም መቀበልም አልፈለግኩምና ታዲያ አንች ማነሽ አላኳት?
የሷ መልስ እጅግ ያልጠበቅሁት አሳዛኝና ልብን የሚያደማ ነበር ።
ልጅቱ እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ በኢትዮጵያ ከታወቀው ዩኒቨርስቲ በዲግሪም የተመረቀች ነች ሥራ ለመቀጠጠር ደጋግማ ተወዳድራለች ።
ኢትዮጵያ በዘር ካልሆነም በገንዘብ እንጅ በእውቀት ሥራ እንደማይገኝ ነገረችኝ።
ብዙ ሙከራም እንዳደረገች ነገረችኝ በተለይ አንደኛው ላይ ያጋጠማትን የማትረሳውና የተወለደችበትን ቀን የረገመችበት ዕለት እንደ ነበር ነገረችኝ ።
ይች ልጅ የገዥዎች ካድሬ እንደሆነች አድርጌ እንዲያ እንዳላብጠለጠልኳት መጨረሻ ላይ እሷም እኔም በጋራ ማልቀስ ጀመርን ።
ቀጠለች ልጅቱ ለመጨረሻ ጊዜ ዳግም ለሥራ እንዳልወዳደር ተስፋ የቆረጠች በአንድ ቦታ ተወዳድራ ታ13138886_10206284394809834_2588875041907908253_nልፋለች ከዚያም አስፈላጊውን ክራይቴሪያ ታሟላለች የመጨረሻው ሥራ ለመጀመር በዝግጅት ላይ እንዳለች ሌላኛዋን በውጤት ከሷ በታች የነበረች ነገር ግን ከነሥም አይጠሬ የሆነች ልች ያን እሷ ያለፈችበት ሥራ ይሰጡባታል እንዴት ወደት ለምን ተብሎ የሚጠየቅበት ሀገር አይደለም የሚጮህበት የለም ።
ለምን ብሎ መጠየቅና ለምን ለልጅቱ የኔን ሥራ ሰጣችሁ ብሎ መጠየቅ ትግሬን ስለምትጠላ ይባልና ሌላ መዘዝ ያስከትልና ለአንዴና ለመጨረሻ ሥራ በሀገሪቱ ዳግም መቀጠር ይቅር በግልህ መሥራት እንደማትችል ትደረግና በአሸባሪነት መከሰስ ም የሚያስከትል በመሆኑ ምንም ሳልናገር ።
የትምህርት መረጃዬን ሁሉ እሳት ውስጥ ጨመርኩት ።
በቃ ከዚህ ላይ የኔ ሕይወት አበቃ ትላለች ።
ከዛስ ሆነ የኔ ጥያቄ ?
ከዛማ ሆድ አስቸጋሪ ነ ዋ !!ዋ !ብሎ ጉርስ ስላለ በተማርኩት ሙያ ሳይሆን በሌላ የእጅ ሥራ ለመስራት ሞከርኩ የሰው ጠጉር መስራት ጀመርኩ ።
ከዚያ ቀጠልኩና የፀጉር ቤት ለመክፈት ፈቃድ ወሰድኩ ከአንድ ዓመት በኋላ
10 000 ብር ግብር ክፈይ ብለው ያዙኝ ይህ አስር ሽህ ብር አንድም ቀን በእጀ ይዠው አላውቅም የት አመጣለሁ ብየ የፀጉር ቤት ፈቃዴን መልሸ ወደስደት ዓለም ወጣሁ ትለኛለች ።
አንጀት የሚበላ
አሳዛኝ ታሪክ!