በወልቃይት ጠገዴና ቃብቲያ ሁመራ ህዝብ ላይ የታቀደው ድቡቁ የህወሓት ሴራ ሲጋለጥ

March 15, 2016

  ( የወያኔን ሚስጥራዊ ሰነድ በpdf ለማንበብ ከዚህ ላይ ይጫኑ)     መጋቢት 2008 ዓ.ም

 


TPLF-Page-2

 

ያ ኣካባቢ በልማት ተጠቃሚ የሚሆንበትን በተጠቃሚነቱ በጎረቤቱ ከሚገኙት የኣማራ ክልል ወረዳዎች የተሻለ የልማት ተጠቃሚ ሆኖ በሚያይበት ግዜ ትግሬነቱ ኣጠናክሮ የሚቀጥልበትና ለሚመጡ የትግሬነቱ ጠላቶች በጣም ኣጠንክሮ የሚዋጋበት ሁኔታ ስለሚፈጥር በዚህ ጉዳይ በጣም ተጠናክሮ ቢሰራበት ዘላቂ መፍትሔ ያስገኛል። በተጨማሪ ከምዕራባዊው የትግራይ ዞን ውጭ ብንመለከት እንኳን በደርቅ የተጠቁ የኣማራ ክልል ወረዳዎች ዋግሀምራና ራያ ቆቦን በቂ የሰውና እንሰሳ ምግብና የመጠጥ ዉሃ ሲቀርብላቸው በኣንፃሩ ደግሞ በእነዚህ ኣከባቢ የሚገኙ የኣማራ ክልል ኣዋሳኝ የሆኑ የትግራይ ወረዳዎች እንደ ጣንቋ ኣበርገሌ፤ ሰሓርቲ ሳምረና ራያ ለሰዉና እንሰሳ የሚያስፈልግ ምግብና የመጠጥ ውሃ ከጅምር በዘለለ የሚታይ ስራ  ኣለ የሚያስብል ኣይደለም። ራያ ቆቦ ከከርሰ ምድር በሚገኝ  ውሃ በመስኖ ሲለማ በኣንፃሩ ደግሞ ቀድሞ የተጀመረው የራያ መስኖ ስራ በትግራይ ስላልተሰራበት የራያ ትግራይ ህዝብ ለልማት ተጠቃሚነት ሲል ወደ ኣማራ ክልል ከሔድን እንደራያ ቆቦ እንለማለን የሚል መንፈስ ፈጥሮ ችግር እስከሚፈጠር ድረስ እንዲያድግ ሰለማያስፈልግ በፍጥነት መፍትሔ ቢደርግለት ኣሁንም ጠቀሜታን ያስገኛል።cropped-t4.jpg

ሀ. በውስጣዊ ኣሰራር ሊተገበሩ የሚገባቸው መርሃ ግብሮች

1.    ለእነዛ ከህግ ውጭ ኮሚቴ ኣቋቁመው በኣካባቢውና በውጭ (በኣሜሪክ ኣውሮፓና ሌሎች ኣግሮች) እየተንቀሳቀሱ ያሉትን ኮሚቴና ኣባላቶቹ ጉዟቸው የሚደናቀፍበትና በተጓዙበት ሁሉ እንቅፋት እንዲያጋጥማቸውና ተስፋ እንዲቆርጡ ጠንክሮ መስራት ያስፈልጋል። ይሔም በዛ በሚንቀሳቀሱበት ቦታ ባሉ ትግሬዎችና የትግራይን ጣዕም በሚገባ የሚያውቁ ኣካላት በሚስጥር ሊሰራና ሊከናወን ይችላል።

እነዚያ ኣባላቶቹ ጉዟቸው የሚያቋርጡበትና ከሕብረተሰቡ እንዲሁም ከቤተሰቦቻቸው ጫና እንዲያድርባቸው መስራት ያስፈልጋል። በዚህ የማይመለሱ ከሆነ ደግሞ ከሕብረተሰባቸውና ቤተሰቦቻቸው የሚለዩበት ስራዎች መስራት የግድ ይለናል። ለዚህ ሃሳብ የሚያንቀሳቅሱ ኣባላት፣ ኮሚቴውና ተባባሪዎቻቸው ከማህበራዊ ኣገልግሎት እንዲገለሉ መስራት፤ሆቴል ፣ መኪና ወዘተርፈ እንዲጠቀሙ በሚቀርቡበት ግዜ ለባለንብረቶቹና ኣግልግሎት ሰጪዎቹ የማንቂያ ሰራ በመስራት እነርሱ የሚፈልጉትን ኣገልግሎት እንዳያገኙ በማድረግ ባለንብረቶቹ ግዴታዎቻቸው እንዲወጡ መስራት  ያስፈልጋል።

2.    ይህ የትግራይ የቆላ ኣካባቢ ህዝብ (ምዕራባዊው ዞን)በደጋ ከሚኖረው የትግራይ ህዝብ ጋር ስነ-ልቦናዊና ማህበረ-ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት እንዲደለደል ማድረግ። የወልቃይት ጠገዴና ቃብቲያ ሁመራ ወረዳዎች ካለፉት መንግስታት ጀምሮ እስከ ኣሁን ድረስ ማህበረ-ኢኮኖሚያዊ ግንኙነቱና ማዕከሉ የጎንደር ከተማ ብቻ እንዲሆን ነው የተፈረደበት። የንግድ ሸቀጣ ሸቀጦች ከፋብሪካ ውጤቶች እስከ ኣትክልቶችና ፍራፍሬዎች የሚቀርብለት ከጎንደር ብቻ ነው። ለተጨማሪ የግል ትምህርት ልጆቹ የሚጓዙት ወደ ጎንደር ነው፤የሱዳን ሸቀጣ ሸቀጦች የሚገኝበት በመተማ በኩል ነው፤ በትግራይ ምዕራባዊው ዞን (በወልቃይት ጠገዴና ቃብቲያ ሁመራ) እንደምንም ተጠጋግቶ ተጣቦ ኣርሶ ብር ያጠራቀመ ሰው ሲኖር ህንፃና የንግድ ቤቶች የሚሰራበትና የሚከትምበት ጎንደር ወዘተርፈ…ይህ በጣም ሓይለኛ የሆነ ስነ-ልቦናዊና ማህበረ-ኢኮኖሚያዊ ጫና ፈጥሮ ስለሚገኝ ይሔን ችግር ለመቀልበስ ደግሞ ደረሰኝ የሌላቸው ሸቀጣ ሸቀጦች ከጎንደር እንዳይመጡ የክልከላ ጫና ሰለባ እንዲሆን በማድረግ በተቃራኒው ከደጋማው የትግራይ ኣካባቢ ጋር ግንኙነት ለማጠናከር ደግሞ በሽሬና መቀሌ የሚገኙ ታላላቅ ነጋዴዎች በልዩ ሁኔት በማናገር በኣከፋፋዮች ደረጃ ከሁሉም ዓይነት የንግድ ዉጤቶችና ሸቀጣሸቀጦች ከጎንደር ከሚመጣው ንብረት ሁሉ በጣም በቀነሰ የዋጋ መጠን ቢያንስ ግን ተመጣጣኝ በሆነ ዋጋ ሙሉ ብሙሉ የሚሸፈንበት መንገድ በኣጭር ግዜ ውስጥ መፈጠር ኣለበት። ከሽሬ ጀምሮ በሉግዲ በኩል የተዘረጋው ጥርጊያ (ሱዳንና ትግራይ የሚያገናኘው የጥርጊያ መስመር) በጣም ተጠናክሮ በፍጥነት እንዲሰራበትና ይህ የጥርጊያ መስመር  እንዲጠናከር በጣም ጠንክሮ መስራትና ማገዝ፤ በዚህ ጉዳይ ከሱዳን ጋር በጥልቅትና በፍጥነት መወያየት ያስፈልጋል።

የትግራይ ኪነ-ጥበብ በተለይ የትግርኛ ዘፈኖች ብናያቸው በሁሉም ዘፈኖቹ ሲጠሩ የምንሰማቸው የኣካባቢ ስሞች ትግራይ ማለት ከሽሬ የሚመለስ እንደሆነ የሚሰብኩ ናቸው። ይህን ችግር ከመሰረቱ በማረም ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ጠለምትና ሁመራ ያካተተ እንዲሆን የትግራይ ጥበበኞች እንዲያስቡበት ማድረግ፤ ምክንያቱም በኣማርኛ ቋንቋ የሚዘፈኑ የጎንደር ኣካባቢ ስም የሚያነሱ ዘፈኖች ሁሉ ብንመለከት ኣሁንም ያልተዋቸው በሽታ የእነዚህ ኣካባቢ (ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ሰሜን፣ኣርማጭሆ፣ጠለምትና ሁመራ) ስም ሳይጠሩ ኣያልፉም። ስለሆነም የጥበብ ድርሻ በሰው ልጅ ስነ-ልቦና ከፍተኛ ተፅእኖ ስላለው የትግራይ ጥበበኞች ልንሰራበት ይገባል። የቆላው የትግራይ ተወላጅ (ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ሁመራ፣ ቃብቲያና ጠለምት) ከጎንደር ታሪክ በላይ በኣክሱምና ይሓ ታሪክ ኩራት እንዲሰማዉና የእኔነት ስሜት እንዲያድርበት ማድረግ የግድ ያስፈልጋል።  ከኣጤ ቴድሮስ ታሪክ በላይ የኢትዮጵያን ዳርድንበርን ለማስከበር ላይ እና ታች እያለ ሳለ የሞተውን የኣጤ ዮሃንስ ኣራተኛ ጀግንነት ኣውቆ እንዲኮራበትና እንዲመካበት ቢደረግ የትምክህተኞቹ የኣማራዎቹ ተግባር ማለትም ከድሮ ጀምሮ በተዋረድ የመጣውን ክፋታቸውና ዉሸታቸው እንዲሁም የትግራዋይን ስም የማጥፋትና በወሬ በማስተጋባት ብልግና እንደሰሩ በማስተማር በተቃራኒው ደግሞ የትግራይና ትግራዎትን  የበላይነትንና ብሔርተኝነትን ከፍ በማድረግ በውስጣዊ ስብከት እንዲያስተጋባ በማድረግ ጫና መፍጠር።

3.    የሐይማኖት ኣባቶች ግዴታዎች፦

በኣካባቢው ኣብዛኛው የኦርቶዶክስ ሐይማኖት እምነት ተከታይና የትግርኛ ቋንቋ ተናጋሪ በመሆኑ በኣብያተ-ክርስቲያናት ላይ የሚደረጉት ስብከቶችና ኣገልግሎቶች ከኣማርኛ ሙሉ በሙሉ ነፃ እንዲሆኑ በማድረግ በትግርኛ እንዲገለገሉ ማድረግ። በኣከባቢው ወደ ሚገኙ ኣብያተ-ክርስቲያናት የሚመደቡ ገበዝ፣ ቀሳውስትና ዲያቆናት ከኣካባቢ ሰዎች እንዳለ ሆኖ በተጨማሪ ሙሉ በሙሉ ትግርኛ ብቻ የሚናገሩ ኣገልጋዮች ከሁሉም የደጋው የትግራይ ኣካበቢ  የሚመደቡበት ሁኔታ በማመቻቸት የመስበኪያ ቋንቋ ትግርኛ እንዲቆጣጠረው ማድረግ። ይህም ማለት ያ ኣሁን ያለው የኣካባቢው የኣብያተ-ክርስቲያናት ኣገልግሎት የኣማርኛ ቋንቋ የበላይነት የሚያራምዱ የጎንደሬዎችና የጎጃሞች ቋንቋ ለትግርኛ  ቋንቋ የሚቆጣጠረው ስለሆነ ነው።

4.    የኣካባቢው ተወላጅ የሆኑ ተሰሚነት ያላቸው የኣገር ሽማግሌዎች፣ የሐይማኖት መሪዎችና ሃብታሞች ትግሬነታቸው እንዲኮሩበትና ለእነዛ በመሓል ስሜት ያሉ ሰዎች ሰብከው የሚያመጡበት ሁኔታዎች ለመፍጠር መነጋገርና መግባባት በመፍጠር እንዲሰሩበት ማድረግና በልዩ እንክብካቤ መያዝ ያስፈልጋል።

5.    የኣካባቢው ኗሪ ተወላጆች በመንግስት ስራዎችና በግል ስራዎች  በሁሉም የትግራይ ደጋማው ኣካባቢ ከሚኖሩብት የተሻለ ስራ እንዲሰሩ ማድረግና ከትግራይ ነጋዴዎች ጋር ጥብቅ ሁኔታዎችና ግንኙነት እንዲኖር መፍጠር። በተቃራኒው ደግሞ ወደ ትግራይ ምዕራባዊው ዞን የደጋማው የትግራይ ህዝብ በብዛት በማምጣት ቋሚ ኑሮ የሚኖርበትና የሚመራበት ሁኔታዎች በመፍጠር ይህ መርሃ ግብር በፍጥነት እውን እንዲሆን ማድረግ ኣስፈላጊ ነው።

6.    ኣዳዲስ የሰፈራ ማዕከሎችን በማቋቋም በሸራሮና ሁመራ የጥርጊያ መስመር ፈTPLF-Page-3ቃደኛ የወልቃይትና የጠገዴ ተወላጆች በዛ ኣድርገን ከሌላ ኣካባቢዎች ኣደባልቆ በሰፈራ ማዕከሎች ማስፈር። በኣማራ ክልል ድንበር የሚገኙ ኣዋሳኝ የወልቃይትና የጠገዴ ቀበሌዎች ላይ ከትግራይ በሚመጡ ሰፋሪዎች በቋሚነት እንዲሰፍሩና በእርሻና ንግድ በጣም ፈጣንና ጠንካራ እንዲሆኑ በማድረግ የተለያዩ የብድር ኣገልግሎት እንዲያገኙ በማድረግ እንዲሁም ግብር እንዳይከፍሉ በማድረግ በቋሚነት የሚኖሩበት ሁኔታ ማመቻቸት።

7.    በባላባት የወልቃይት ጠገዴ ተወላጆችና ለስራ ከደጋው የትግራይ ኣካባቢበሔዱትና በሚሔዱት የትግራይ ተወላጆች መካከል በትዳር በሰፊው እንዲገናኙ በማድረግ የትግራይ ልጆች ኣንድነት እንዲጠነክር መስራት ያስፈልጋል። በመጨረሻ እነዚህ የመሳሰሉትን የሚነሱ ጥያቄዎች የሚከታተል ውስጣዊና ሚስጥራዊ ኮሚቴ በማቋቋም መፍትሔዎችን ያፈላልጋል፤ በትምክህተኛ የኣማራ ሓይል በኩል የሚደረጉ ዉስጣዊና ዉጫዊ እንቅስቃሴዎች በትኩረት መከታተል ያስፈልጋል።

 

 

TPLF Page -1

 

TPLF Page -2

 

TPLF Page -3