አሕውሓት በ ሀገረ ኢትዮጵያ ምን እየሰራ ነው?
====∞===========∞==

በደቡብ ክልልና በመሀል ኢትዮጵያ እንዲሁም ከበስተሰሜኑ የአማራ ክልል በሚባለው በተለይ በሰሜን ጎንደር።

wegera

አሁን ላይ በኦሮሞ ወጣቶች የተጀመረው ጠቅላላውን የኦሮሞ ሕዝብ ለሕውሓት አንገዛም ብሎ ሕዝባዊ አመፅ እንቅስቃሴ ተጀምሯል በየቀኑም የኦሮሞ ሕዝብም እየሞተ ነው ።
በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ከ25 ዓመት በፊትም ደርግ ከመውደቁ በፊት የሚፈፅሙት ሰበዓዊ ወንጀል በአግባቡ ለሕዝብ ጆሮ ባለመድረሱ የወልቃይት ሕዝብ የዘር ፍጅት ለኢትዮጵያ ሕዝብ እንደ ባዕዳ ሆኖ ከሕዝብ ሳይቀርብ ባይተዋር ሁኗል አንዳንድ ሰዎች እንኳ የሚያውቁትን የአይን መረጃ ከጥፋት የተረፉትን ቤተ ሰብ የሚናገሩትን ልብ ያላቸው አልነበረም ወልቃይት ወደትግሬ መከለሉን ስትነግራቸው ምን ችግር አለው ትግራይም እኮ ኢትዮጵያ ነው ይሉኃል ።
ይህን የየዋሕነት ጥሪ ከሁሉም በላይ የትግራይ ጠላት ተብሎ ተፈርጆ በሕውሓት ማንፌስቶ ተመዘገቦ የዘር ፍጅት ከሚካሄድ ሕዝብ በአማራው አንደበት የወልቃይት ሕዝብ ጩኸት የቃየል ጩኸት ሆኖ እንዲቀር ተደርጓል ።
ከሕውሓት መካከል ለሕሊናቸው ያደሩ አልዋጥልህ ብሏቸው አፈንግጠው የወጡ በትክክል ሕውሓት ምን እንዳቀደም ምን አየሰራ እንደሆንም እነ ገብረ መድህን አርዓያ ለ30 ዓመታት ቢነግሩንም ሰሚ ጀሮ አላገኙም የተቀሩት ከሕውሓት ጎራ ያፈነገጡት የገብረ መድህንን ፈለግ እንዳይከተሉ ከኛ በኩል ተስፋ በማጣታቸው አፍረውና ተሸማቀው ራሳቸውን ደብቀው እንዲቀመጡ አድርገናቸዋል ።
እኛ አማራ ተብለን በዘር ከረጢት በሕውሓት የተከተትነው እየከነከነን እያቃረነም ቢሆን ወደተዘጋጀልን ከረጢት ሳንፈራገጥ እነሆ ለሩብ ምዕተ ዓመት ተቀምጠናል ።
በአሁኗ ሰአት እኔ ኦሮሞ መሆን ያምረኛል ኦሮሞ ሕዝብ እንቅስቃሴ ያስቀናኛል ።
አሁን በየደቂቃው በኦሮሞ ሕዘረብ ላይ የሚፈፀመውን ሰቆቃ የሕውሓትን አፈና ተቋቁሞ ለአለም ሕዝብ መረጃውን እየደረሰ ይገኛል ።
በአማራ ክልል በተለይ በሰሜን ጎንደር ደርዘን ደርዘን ሕዝብ በጁምላ ይገደላል ነገር ግን የሟቾን ፎቶ ግራፍ ይቅርና የሟቹቹን ስም ዝርዝር እንኳ መረጃውን አናገኝም ።
በቅርቡ መሀል ጎንደር ከተማ የበዓታ ወይን ቤት ታሳሪዎቹ እንደተዘጉ ቤቱ በእሳት ጋይቷል ።
ከነነፍሳቸው የተቃጠሉም አመልጣለሁ ያሉም በአልሞ ተኳሽ ተገለዋል ።
ከታሳሪዎች መካከልም ከግርግሩ በኋላም የተረሸኑ እናዳሉ ተነግሯል በተለይ የአንድ ወጣት ባለሀብት ለብዙ ሰዉ የሥራ ዕድል የከፈተ በፖለቲካ ኬዝ ሰማያዊ ፓርቲን ደግፈሀል ተብሎ የታሰረ ከግርግሩ በኋላ መረሸኑን ሰምተናል ።
አስከሬኖች ወደጎንደር ሆስፒታል ተወስደዋል አንድም የሙታን አስከሬን በፎቶም ሆነ ብዛት ማን የሚሉ መረጃዎች የውኃ ሽታ ሁነው ቀርተዋል ።
በዚህ ላይ የኔ ጉልህ ጥያቄ አለኝ ።
በፀረ ወያኔው ትግል የአማራው ሕዝብ አንድም ሕውሓት እንደሚለው የአማራ ሕዝብ አከርካሪው ተቆርጧ ካልሆነም በሕውሓት የሚፈፀመው ግፍ ተለምዷል ማለት ነው ።
ካልሆነም የሕውሓት የአፈና መዋቅር በአማራውና በኦሮሞ ክልል መካከል ልዩነት አለ ወይ? ብዬ እንዳስብ ያደርገኛል ።
አማራ የደረሰበትን ግፍና መከራ ማውራት ስለማያውቅበት ነው ብዬ አልገምትም ።
ምላሳችን ከማንም በላይ የኛው ይረዝማል ።
እውነት ሕውሓቶች እንደሞሉት የተግባር ሰዎች ስላልሆን ነው እንድልም ያደርጉኛል ።
ከሁሉም የሚገርመው ከመካከላችን የተለየ ሀሳብ ይዞ ራሱን ወጣ ሲያደርግ ከሕውሓቶች የቅርብ ከስጋ ዘመዶች በፊት የኔ ነው ያልከው የቅርብ ጓደኛህ ባንተላይ የሚሰነዝረው ትችና የማግለል የማስገለል እንቅስቃሴ ስታይ ሥጋህን አልፎ አጥንትህ ዘልቆ ይገባል ።
እርስ በርስ ስንጣረስ ስንጠልፍ ስንጠላለፍ ለሩብ ምዕተ ዓመት ባለንበት በቆምንበት እየረገጥን እንኖራለን ።

Shagiz Shagi's photo.12662531_10205652764059460_5745813341297194851_n