ሕውሓትን ወደጥፋት የሚወስዱት ጎዳናዎች ምቹ ናቸው!
እንቅፈት መሰናክልም የለበትም።
ይህ ደግሞ መታደል ሳይሆን መበደል ነው!!!
ሕውሓት ከሕዝ የተጣላ በመሆኑ ለዕርቅ የሚሆኑትን ሁሉ ጨርሶና አሟጦ ስለጨረሰው መመለሻ የለውም ።
ሕውሕት የተሳፈረበት ባቡር አንድ አቅጫን ብቻ ነው ያለው ፣ እሱም በስልጣን እስካለ ድረስ ለበደል ለምዝበራ ለወረራ የሚጠቀምበት አቅምና ጉልበት ለዚህ ደግሞ ተባባሪ የሚሆኑት ግለ ሰብና በአማሳሉ የፈጠራቸው ድርጅቶች አሉት ።
ለዚህም እንደ ምሳሌም: —
— ብአዴን ትልቁ ተጠቃቭ ይሆናል ።
የጎንደርን ታሪክ ለማጥፋት መሬቱን ለመውረር የጎንደርን ሕዝብ የአስተዳደር በደል ለመፈፀም ብአዴንን እንደትልቅ መገልጋያ እቃ ይጠቀምበታል ።
በተለይ ከጎንደር ተከፍሎ ወደትግራይ ከተከለሉት አካባቢ በሚኖሩት ቀበሌዎች በብአዴን ሥም ሕውሓት የሚፈፅማቸው ሰቆቃ በቃላት ለመግለፅ ይከብዳል ።
እድለኛው ሕውሓት ሲፈልግ አአማራ ሲፈልግ ኦሮሞ የሚሆኑልት የሥጋ ዘመድ ተርፈውታል ።
በአማራው ሕዝብ ጥፋቱን በብአዴን አማካኝነት ይተገብራል ።
ኦሮሞውን ለመበደል እንደ ኦህዴድ የሚች አገልጋይ የትም አይገኝም ።
ዳግም በሥመ ፌዳራል ችግሩን ልፍታላችሁ እያለ ያን የዋህ ገበሬ መልሶ መላልሶ ያታልላቸዋል ።
ብለጣብልጡ ሕውሓት ቀጥሎም የዋህ ገበሬ እንዲህም ይላቸዋል ።
የአማራ ክልል መስተዳድር በደል እየፈፀመባችሁ ስለሆነ ወደትግራይ ክልል ብትሄዱ ሁሉንም ችግር በትግራይ ክልል ይፈታላችኋል ይላል ። ጅብ ከማያውቀው ሀገር ሂዶ ቆርበት እንጥፉልኝ ነውና የሕውሓትን መሰሪነት እንደማይታወቅ ሁሉ ።
ሕውሓት እንደሚያስበው የዛ አካባቢ ሕዝብ ስለ ሕውሓት ማንነት ጠንቅቆ ያውቃል ፣ ዳሩ ምን ያደርጋል ሕውሓት እድለኛም ነው ።
ለሱ የሚያገለግሉ የሕሊና ድውያኖችን መጠቀምን ይችላል ሕውሓት ይሽራል ይሾማል ፣ ይገድላል ያድናል ።
ብአዴን ማነው ?
በማን ተመሰረተ?
በነማንስ ነው የሚዘወረው ?
—: ፎረጅዱ ጎንደሬ በረከት ስምኦን
የምዕራብ ሀረርጌው ተወላጅ አዲሱ ለገስ ፣ ካሳ ተክለ ብርሃን ፣ተፈራ ዋልዋ ፣ ሕላዌ ዮሴፍ ወዘተ እያልን መዘርዘር እንችላለን ።
ሕውሓት አማራን ለማዳከም ብዙ አማራጮች አሉት
በሀገር ቤት አደህይቶ ና አስርቦ መጨረስ፣ ከሚገደሉት ከሚታሰሩት ከሚሳደዱት ተጨማሪ ለማለት ነው ።
አማራ ወደጎረቤት ሀገር ተሰዶ ሕይወቱን ማትረፍ እንዳይችልታላቅ የስምመነት ውሎችን ዲፕሎማሲን ተጠቅሞ ለጎረቤት ሀገራት የአማራውን መሬት በገፀ በረክት እየሰጠ በኔ በኩል ችግር የለም መሬት ውሰዱ ችግር የለብኝም ነገር ግን የአማራ ክልላዊ መንግሥት ነው እንቅፋቴም ሲል ለሱዳን ባለሥልጣን አስታውቋል ። ሱዳኖች ዘሬ እኛ ኢትዮጵያውያንን ዛሬ ዛሬ በዘር ለይተውናል አንተ አማራ ያነኛውም ትግሬ ይሉናል ።
ሱዳኖች እንደሚሉት የምንዋሰነው ከትግራይ ሪፓብሊክ እንጅ አማራ ክልላዊ መንግሥት አይደለምም ይሉናል ።
አማራ ከሌለ ከትግራይ ጋር የዘለዓለም ወዳጅ እንደሚሆኑም አምነዋል ።
በፖለቲካው ዓለም የዘለዓለም ወዳጅ የዘለዓለም ጠላት አለመኖሩን ሕውሓት አይረዳም ዛሬ ሕውሓት የሚሞዳሞዳቸው ሱዳኖች ትናንት የተግራይን ጀግኖች መተማ ላይ ያፈሰሱትን ደም ያስተወሰው አይመስልም ።
ጎነደሮች መተማ ላይ የተከሉትን አብያተ ክርስቲያን መተማ ዮሐንስ ያሉበትን ምክንያት ረስተውታል ።
በጎንደሪያን አባበሰል አፄ ዮሐንስ እንደሰማዕት ተደርገውም ስለሚቆጠሩ አንገቱ የሰጠው ዳግማዊ ዮሀንስ ይሉታል ።
አፄ ዮሀንስ በጎንደር አብያተ ክርስቲያን እንደ ፃድቅ ሲቆጠሩ በተቃራኒው አፄ ቴዎድሮስ እንደከሀዲ በኦርቶክስ እምነት የተነሳ ጠላት ሲሉ ሌላ ጊዜም የአበደው ንጉስ እየተባልን በቤተ ክርስቲያ የሚነገሩን እንደነበር የልጅነት ትዝታዬም ነበር ።
ሱዳኖቹም በዚህ በሕውሓት ማጭበርበሪያ አምነው ተቀብለውታል።
ለዚህም ማስረጃ የሚሆን ባሳለፍነው ሳምንት በአዲስ አበባ የሚገኘው የሱዳን አንባሳደር እንዳለው ህዳር 2008 ዓ/ ም
ከትግራይ መንግሥት ጋር ችግር የለብነም ችግሩ ያለው ከአማራ መንግሥት ጋር ነው ሲል ለሚዳያ የሰጠው ታላቅ መረጃ ነው።
ይህ የሱዳኖች አባባል የአማራን ክልላዊ መንግሥት ለደንቀራነት የሚጠቀሙበት ለመሆኑ ታላቅ ማስረጃ ነው።
ሕውሓት የቅማንትን ብሔረ ሰብ ለጎንደር መፍረስ ለመጠቀም ሲል ራሱ አስታጥቆ የቅማንትን ገበሬዎች ብአዴንን ሥም በልዩ ኃይል ሥም አስታጥቆ እንዲጨፈጨፉ ካደረገ በኋላ የፌደራል ካባውን ደርቦ መጣና ያን የዋህ ገበሬ ሰብስቦ ይህን በደል የፈፀሙትን የአማራ መንግሥት ዋጋቸውን እንሰጣለን በአማራ መንግሥት ለደረሰባችሁ ጭፍጨፋ እናዝናለን ።
ከዚህ በኋላ የአማራ መንግሥት ምንም አይነካችሁም አለነላችሁበማለት ከፈለጋችሁ የጎንደርን መስተዳድር በእጃችሁ ነው ፣አለነላችሁ ከናንተው ጋር ነን በማለት ታላቁን ድራማ በአማራውና በቅማንት ላይ እየተወነው ያለው አንድና አንድ የሆነው ሕውሓት ከጥፋት ላይ ጥፋት ከበደል ላይ በደል በሰሜን ኢትዮጵያ በጎንደር ይፈፅማል ።
የሰሞኑን የጎንደሬዎች ገበሬ አፈናቅሉ ለሱዳን የሚሰጠው ታላቅ ለምና ውኃ ገብ መሬት ሁለት አላማ ያለለበት ነወረ ።
አንደኛው አማራዎች ለመቅጣት ከሱዳን ጋር በመስማማት በመሀል ጎንደር ገበሬዎች ሳንዱች በማድረግ ሲሆን ።
ሁለተኛም በሱዳን ምድር ለሁልጌዜም የሚፀና ሕውሓትን የሚቃወሙ በሱዳን ምድር እንዳይኖሩ የሚያደርግ ይሆንል ብሎም በማሰብ ነው ።
ለዚህ የግል ጥቅም ለሚያልፍ ስልጣን ሀገር ቆርሶ ሲሰጥ አያሳዝንም?
ከዚህ በመነሳት በሕውሓት ውስጥ ያሉት ግለሰቦች ከአድማስ ባሻገር ያለውን የማያዩ ዕውሮች የማይሰሙ ደንቆሮዎች ናቸውም ብንል ስህተቱ የት ላይ ነው ።
ሕውሓት ቁጭ ብሎ የሰቀለውን ቁሞ ለማውረድ አይችል ።
ሕውሓት የሚሰራቸውን ስመለከተው በእረኝነት በልጅነት ጊዜ የምናስበውን ይመስለኛል ።
ሕውሓት የ21ኛው ሴንቸሪ አስተሳሰብን አያውቀውም ከሰይንስና ፍልስፋና ከዘመኑ ስልጥንና አብሮ ለሜሄድ ደረጃው አይፈቅድለትም ።
እጅግ ኋላ ቀር ነው ።
ሕውሓት የሚገዛትን ሀገር የገደለ የዘፀጎቿንም ክብር ያስደፈረ ቡድንም ።
ኢትዮጵያዊ መሆን በአሁኑ ሰዓት
ውርደት ነው ።
ዛሬ ኢትዮጵያዊ ያ በነፃነቱ ይኮራ የነበረ ሕዝብ በአፍሪካ ምድር የተናቀና የተጠላ ሁኗል ።
ኢትዮጵያውያ በአፍሪካ ምድር ላይ
በማላዊ ፣በሞዛምቢክ ፣በኬንያ በሱዳን በጅቡቲ ህገ ወጥ ተብለው ቁም ስቅል ያያሉ ከአፍሪካ ምድር ዲፖርትድ ይደረጋሉ በገዛ ሀገራቸው ክልልህ አይደለም ተብለው በሕውሓት መንግሥት ዲፖርትድ ይሆናሉ ።
ይህን ስል ቁጥር አንድ ዜጋዎችን አያጠቃልልም አይመለከትም ።
ማንኛውም ባዕዳን በኢትዮጵያ ምድር ይኖራሉ የነፃ ትምህርት ያገኛሉ ።
ኢትዮጵያውያኖች ግን በሀገራቸው አንድ የሱማሌ ስደተኛ የሚያገኘውነን ክብር አያገኝም ።
ከኤርትራ ፣ከሶማልያ ከደቡብ ሱዳን የመጡ ስደተኞች በሚገባ መብታቸው ሲከበር ኢትዮጵያውያን ተሰደው የሚኖሩበት ምድር እንዳይኖር በሕውሓት ተደርጓል ።
ለኢትዮጵያውያን ግፍና መከራ ሲደርስ ።
እንደመንግሥት መቃወም ይቅራና በኢትዮጵያውያን ስቃይ መከራ መረጃ የሚሰጡትን በማሳደድ ላይ ይጠመዳል ።
በቤሩት ፣በሳውዲ ፣በየመን ፣በሊቪያ የሚፈፀሙት የተናገሩ የተቃወሙ ፣
—በሀገር ቤት የሚኖሩ ታስረዋል ሕዝብ በአደባባይ ተደብድቧል ከሀገር ውጭ ባለው ለወገን ተቆርቋሪዎች ላይም ዲፕሎማሱውን ተጠቅሞ በየሀገሩ መንግሥታትን አስተባብሮ ያሳስራል እንዲባረሩም ያደርጋል ፣
ደንበር ተሻጋሪም አፋኝ ብድንም ይጠቀማል ።
በየመን በጋዜጠኛ ግሩም ተክለሃይማኖት ፣በሳውዲ ነቢዩ ሲራክ ፣ በቤሩት በራሄል ዘገየ ላይ ብዙ ክልትም እንደደረሰ እናውቃለን ።
ስለ ኢትዮጵያውያን በደል መናገር አሻባሪነትም ያስብላል ።

Shagiz Shagi's photo.