—#‪#‎የወገራና‬ ሕውሓት ቁርኝት##—
///////////\/\////////////////
: — ወገራ አውራጃ በሰሜን ጎንደር ከሚገኙት ሁለት አውራጃዎች አንዱ የነበረ
እጅግ የታወቁ ሀገር ወዳድና ታዋቂ ኢትዮጵያውያን የወጡባት ነበረች ለምሳሌም የምጠቅሳቸው የቅርብ ጊዜ የምናስታውሳቸው እነ ቢትወደድ አዳነ እነአባይ ጎሹ ና ሽባባው ጎሹ የወልቀይትና ጠገዴ ተወላጅ የነበሩ ።
ቢትወደድ አዳነ የወገራ አውራጃ አስተዳዳሪ እስከ ንጉሱ መውደቅ ስልጣን የነበሩ በኋላም በትውልድ ሀገራቸው ጠገዴ ይኖሩ በነበረበት ጊዚ የሕውሓት ሰዎች እንደራደር ብለው በማታለል ተከዜ ላይ የተረሸኑ ።
አባይ ጎሹ የትውልድ ቦታ ወልቃይት በደርግ ዘመን እስከ1970ዎቹ የወገራ አውራጃ አስተዳዳሪ የነበሩ ታናሽ ወንድሙ ሽባባው ጎሹ የወገራ ወረዳ አስተዳሪ የነበሩ
አባይ ጎሹን ሕውሓቶች ከትግራይ በመነሳት ቀን ከሌሊት ተጉዘው እሱን ለመግደል አቅደው የዳባትን ከተማ በመውረር ባልተጠበቀ ሁኔታ ዳባት ላይ ገድለው የዳባትን የመሰረተ ልማት ተቋሞችን አውድመው የዳባት ከተማ በማደግ ላይ የምትገኝ ከተማ ነበረች ።
የሁለቱ አውራጃ የሀገር ውስጥ ሸቀጥ ማከፋፈያ የነበረች ለሁለቱ ከተማ የሚያገለግል የንግድ ባንክ የነበራት ታላቅ የጤና ጣቢያና የመለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ት/ ቤት ነበራት ።
የወገራ አውራጃ አራት ወረዳዎች ነበራት
1/ ወልቃይት
2/ ጠገዴ
3/ ወገራ
4/ ዳባት ይባሉ ነበር ።
የወገራ አውራጃ እስከ ሱዳን ጠረፍ ሰቲት ሁመራን ያካተተ ነበር ።
ሕውሓት ሀገሪቱን ከመቆጣጠሩ በፊት ከደርግ እየተዋጋ በሰሜኑ የጎንደር ገጠራማ ቀበሌ የቀድሞ አርበኞችና የአርበኞች ቤተ ሰብ ቡርዣ እያለ ባለሁለት ጥማድ የነበሩ ታዋቂ አዛውንቶችን እያፈነ ይወስዳቸው ነበር ።
ከአፈናው እሴት መነኮሳትን የደብር አገልጋይ በእድሜ የጠኑ ቀሳውስትም ያጠቃልል ነበር ።
በዛን ጊዜ ከደርግ በኩልም በመጀመሪያው የአብዮት አመታት ይህንኑን ያደርግ ስለነበር ከደርግ አሰራር በማዛመዱ ዘመን ያመጣው ነው ብሎ የዘር ማፅዳት ነው ብሎ ማንም አላመነም ።
አሁንም ቢሆን ወዶም ይሁን ተገዶ ሕውሓትን እንደ ተለመደው አንባ ገነን መንግሥት ብቻ እየመሰላቸው ከአፍሪካ ዲሞክራሲ ጋር አዛምደው የተለመደ እንደሆነ በአፍሪካ ይቆጥሩታል ።
ሕውሓት በዓለም ተወዳዳሪ የሌለው ፋሽዝም ነው ።
ኋላቀር ከመሆኑ የተነሳ እጅግ አደገኛ ጨዋታ ጌም እየተጫወተ ነው ።
ሕውሓት የሚከተለው ፖሊሲ የአልጠግባይ ስግብግብነቱ ልክ ያጣ ነው ።
ሥልጣን ላይ ሁኖም ማሸነፉን አያውቅም።
ከአዋቂ የተጣላ ከወዳጅ ቁጥር ነው የሚባለው ትክክል ነው ሕውሓት የኢትዮጵያን ሕዝብ በዜሮ አሸንፎ መሰጥቃት መጠቃት ትርጉሙን አያውቀውም ።
መንገዱ ሁሉ ዝግ ነው በመጨረሻው ሰዓት እውር ለዕውር ይትጋብኡ ውስተ ድብ የሚለው የመፅሀፍ ቃል ይፈፀማል።

ከ1973—2008 ዓ/ ም
ሕውሓት ሰባት ሁነን ትግራይ ውስጥ ተመሰረትን ይበሉ እንጅ የትግራይ ተወላጆች ያልነበሩበት ድርጅት በኢትዮጵያ ምድር አልነበረም እንደኛ እምነት ትግራይን ልክ እንዳሁኑ ሕውሓት ከሌላው ኢትዮጵያ እያገለለ ሕብረተ ሰቡን ከሌላው ማሕበረ ሰብ ሳይነጥለው ትግራይ የኢትዮጵያ የታሪክና የዕምነት መነሻና መድረሻ እንደሆነች እናምናለን ።
ዛሬ አማራ እያልን የምንጠራው ማሕበረ ሰብ የዘር ግንዱን መዞ መቁጠር የሚችል ጥናት የተካሄደበት አይመስለኝም ።
ቋንቋው እንዲሁ እንዴት አደገ እንጅ እንዴት ተጀመረ ብሎ የመለነግረን የለም
አማረኛ የብዙ ቋንቋ ቅይጥ እንደመሆኑ መጠን አማራ የሚለው ማሕበረ ሰብም እንዲሁ የብዙ ማሕበረ ሰብ ቅይጥና ውሁዳን የኢትዮጵያን ማዕከል ከፈጠሩት ወደውም ይሆን ሳይወዱ ባዕዳንን ለመከላከል ሲሉ ቋንቋና ዘር ሳይለያቸው ጠላትን ለመመከት በአንድ ይሰለፉ እንደነበር የታሪክ ሀቅ ስለሆነ ልንክደው የማንችል ዕውነታ ነው ።
ከቀደሙት ነገሥታት ዜና መዋዕል ላይ ተፅፎ እንዳየነው በሰሜኑ የሀገራችን በቀይ ባሕር በኩል በተደጋጋሚ የወረራ ጥቃት ሲፈፀሙብን አብዛኛዎቹ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ የሚኖሩ የተላያዩ የማሕበረ ሰብ ክፍሎች የግልን የሥልጣን ሽኩቻ በመተው የጋራን ጠላት በጋራ ለመመከት ወደሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ይዘምቱና ከጦርነቱ በኋላ አባዛዎቹ ከሞት የተረፉት ወደቀያቸው አይመለሱ በዛው በሰሜኑ ክፍል ተለማምደው ትዳር መሥርተው ከነዋሪው ከሰሜኑ ሕዝብ ተቀላቅለው ወልደው ተዋልደው ተወሰሕደው ይቀሩ ነበር ።
የዚህ ውሁዳን የማሕበረ ሰብ ውጤት አንድ የጋራ መግባቢያ ቋንቋ የግድ ሊፈጠር ችሏል ይህ ቋንቋም አሁን አማራኛ ብለን ለተወሰነ ክልል ነዋሪዎች አድርጎ ሕውሓት ታሪክን አጣሞ አሳጥሮና ከርክሞ ያቀረበት ምክናያት አብዛኛው የሀገራችን የዋሕ ሕዝብ ጠንቅቆ የተረዳው አይመስለኝም ።
አማራ ጠላት ነው አማራ በአማራ ክልል ወደ አንድ ኮንሰንትሬሽን ካንብ እንዲጠቃለል የተደረገበተረም ምክንያት ማንም የተረዳው ያለ አይመስለኝም ።
ሕውሓት በአይናችን እንዳየነው በጆሮ እንደሰማነው በ25 አገዛዝ ዘመኑ በኢትዮጵያ ከሚኖሮት አ

Shagiz Shagi's photo.