<<<<<ወይ ዘመን ወይ ጊዜ >>>>>>>
“”””””””””””””””######””””””””””””””
ዘመን ሲጥል ውሻ ባለቤቱን ይነክሳል
=]==========[]============[=
—: ዓለም በኮሎኒያሊስቶች ቅኝ ግዛት የቀንበር ሥር ሁኖ ሲማቅቅ እኛ ኢትዮጵያውያን እንዲህ በዘር ሳጥን ሳንቀመጥ በጎሳ ከረጢት ሳንገባ ነፃነትን የሚቀማ ባዕዳን ሀገራችን ነፃነት ለመግሠሥ ሲመጣ ማንኛው በዚች ነፃ ምድር ኢትዮጵያም በሏት ሐበሽ እንዲሁም አቢሲንያ ውስጥ የሚኖር ማንኛውም ብሔር ዘር ቋንቋ ዕምነት ሳያግዳቸው በአንድ ላይ ሁነው ጠላት ድባቅ እየመቱ ለዘመናት የራስን ቋንቋ የራስን ዕምነት ተገደው ሳይቀይሩ እሰከ ዘመነ ሕውሓት መቆየቱን የሚክድ ያለ አይመስለኝም በዚህ የተነሳም ምዕራባውያን ለዘመናት ለባርነት የማይመቹ የሚል ቅፅል ሥም ሰጥተውን ጥርሳቸውን ነክሰውብን ቆይተዋል ።
— ምዕራባውያን ወራሪዎች ይችን ታላቅ ነፃነቷን ጠብቃ በአፍሪቃ ምድር የኖረች ሀገር ለሌሎች በቅኝ አገዛዝ ሥር ለወደቁም ከአፍሪካ ውጭም ሩቅ ምስራቆችንም ጭምር የሚያነቃቃ በመሆኑ ። የተገነዘቡ እንደ እንግሊዝ ያሉ የወራሪ ቁንጮ አውሮፓዊ ተመካከሩ ጥናትም አደረጉ ኢትዮጵያን እንዴት ማዳከም እንደሚችሉ እቅድም ነደፉ በተለይ እንግሊዝ ለዘመናት ልንወጣው ወደማንችለው ታላቅ የቤት ሥራ የሰጠችን ሀገር መሆኗን ኢትዮጵያዊ ሁኖ የማያውቅ ካለ በኔ ግምት አለ ብዬ አልገምትም አፈር አለመልበስ ካልሆነ በስተቀር በቁሙ የሞተ ነው እላለሁ ።
በተለይበአሁኑ ሰዓት ወያኔን በሞግዚትነት ተንከባክበው ከማሳደጋቸው በተጨማሪም አሁን እየሞተ በመምጣቱ ያሳሰባቸው በመሆኑ ወያኔን ከሞት ለማዳን የማያደርጉት ነገር የለም ።
የእንግሊዝ ግብር ከፈይ ሕዝብ ሀብት ለሕውሓት የማይነጥፍ የሁልጊዜም ከሰማይ የሚወርድለት ሲሳይም ነው ።
,★★★★
ነገርን ነገር አነሳው እንጁ የጽሑፌ ዓላማ ዘመን የጣለው ሰው የአባቱ ውሻ ነከሰው እንዲሉ ።
ኢትዮጵያውያን በዓለም የነፃነት ፋና ወጊ የማንደፈር ጥቁር አንበሶች እንደነበር ታላቋ ብሪታንያ ታላቅ ምስክር ናት ።
ታላቋ ብሪታንያ ፀሀይ በመንግሳቷ የማይጠልቅባት ይባል በነበረበት ወቅት አፍሪካን ከደቡብ አፍሪካ እስከ ግብፅ ከህንድ እስከ ፓኪስታን ይገዙ በነበረበት ወቅት የኢትዮጵያን ደንበር ለመዳፈር ምን ያክል አስግሯት እንደነበር በሱዳን እና በኢትዮጵያ ያለውን እንዲሁ በኬንያና በኢትዮጵያ ያለውን ደንበር መወሰን አልቻሉም ነበር ለዚህ ነው ስምነት በሚል በተንኮል ብዙ ሻጥሮችም ቢደረግም እስከ ዘመነ ሕውሓት ድረስ ምንም አላመጡም ነበር ።
እኛ በማናውቀው የአባይ ውኃን ለምንም ጉዳይ እንዳንጠቀም የሚያደርግ ሰነድ አዘጋጅተውም ነበር ።
እንግሊዞች ኢትዮጵያ ለምትባል ሀገር አሁንም ቢሆን በ21ኛው ክፍለ ዘመንም ጭምር ከራሳችን ያልወረዱ መሆኑን የማይገነዘብ ካለ በቁሙ የሞተ ነው ብዬ እደመድማለሁ ።
እንግሊዞች በዘረኛው የሕውሓት ድርጅት በገሀድ አንያቸው እንጅ በመንፈስ ተጣምረው ተቀምጠዋል ።
ሕውሓት ኢትዮጵያዊ አይደለም ስንል እንዲሁ ከምድር ተነስተን አይደለም በአሁኑ ሰዓት ሕውሓት የኢትዮጵያን ለምና ውኃ ገበ መሬት እስከነ ወንዞቿ ለሱዳን ለማስረከብ ሽር ጉድ የሚለው ከፈጣሪዎቹ ከነእንግሊዝ የወረሰውን ሌጋሲ ለመተግበር ነው ብለን እናምናለን ።
ኢትዮጵያውያን በዚህ ዘመን የለንም ጠፍተናል ሀገርን ለባዕድ አስረክበን ተበትነናል ።
ኢትዮጵያውያን በዓለም ተንቀናል ተዋርደናል በየትኛውም ሀገር ኢትዮጵያውያን በአደባባይ ይታረዳል ይገደላል የተለያዩ በደሎች ይፈፀሙብናል መንግሥት አልባም ሁነናል ።
በአረብ ሀገራት እሴት እህቶቻችን ይደፈራሉ በባርነት ይሸጣሉ በአሰቃቂ ሁኔታ ይገደላሉ ።
በአረብ ሀገራት በመንግሥት ደረጃም በአደባባይ አንገት በመቅላት ይገደላሉ ነገር ግን በዛች በስመ ኢትዮጵያ የተከፈቱ የኢንባሲ ፅ/ ቤቶችም ቢኖሩ የኢትዮጵያውያንን ጉዳይ ምናቸው አይደለም የሕገወጥ ንግድ የኮንትሮባንድ ተግባር ከመፈፀም ባሻገር የአንድ መንደር ሰዎች የግል ድርጅት ነው ማለትም ያስደፍራል ።
በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያውያን ከአፍሪካውያን በታች በጣም የተዋረድን በመሆኑ በሱዳ በኬንያ በታንዛንያ በማላዊ በደቡብ አፍሪካ የሚፈፀምብን በደል ጣራውን ነክቷል ።
ኢትዮጵያውያን ነፃ እንዲወጡ የረዳናቸውና ያገዝናቸው የአፍሪቃ ሀገሮች ብቻዋን ኢትዮጵያ በመሪዎቿ በአለም መድረክ ለአፍሪካ የተሟገተች ሀገር ዛሬ ኢትዮጵያውያን ሕገ ወጥ ተብለው በባርነት ሲገዙ የነበሩ ቀን ተቀይሮ በፋንታችን እኛ በባርነትና በቅኝ አገዛዝ ሥት ስንወድቅ ድሮ ወንድሞቻችን እንላቸው የነበሩ ሕዝቦች ዛሬ ሕይወታቸውን ለማቆየት ከለላ ይሆኑናል ብለን በእንግድነት ወደሀገራቸው ብንገባ ሕገ ወጥ ተበለን እስራት ግድያ አፈና የሚፈፀምብን ሁነናል በኬንያ በጅቡቲ በሱዳን ቁም ስቅል የሚቀበሉት ለምንድን ነው?
አወ ኢትዮጵያውያ በሀገራቸው ክብር ያልተሰጣቸው በሌላ ሀገር ክብር ይኖረናል ብሎ መጠበቁ ራስን ማሞኘት ነው ።
ውድ ወገኖቸ ራሳችን እንጠይቅ እኔ ማን ነኝ? ምን እየሰራሁ ነኝ ?
ለምንስ እንዲህ ሆን?
የሚሉትን ጥያቄ ለመመለስ መልሱ እኛው ጋ ይገኛል ነፃነት ያለው በዕጃች ነው ።
ከ # Shagiz Shagi
★★★★

Shagiz Shagi's photo.