——የትግራይ ፖለቲከኞች ለምን——?
÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷///////÷÷÷÷÷÷÷÷÷
★ የትግራይ (ሕውሓት) ፖለቲከኞች ለምን? በአማራው ላይ ቢላዋ ሳሉ ( ሰይፍ መዘዙ ) ?
ዕውን በኢትዮጵያ በብሔር ፣ በቋንቋ እንዲሁም ዕምነትን ፣ መሠረት አድርጎ በሕዝቦች መካከል የነበረ ጦርነት አለ ?
ከነበረም ዘመኑን እስከታሪኩ ንገሩን
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
በኢትዮጵያ ውስጥ በታሪክ የረስ በርስ አያሌ ጦርነቶች ተካሂደዋል ።
የጦርነቱ መንስኤም አንድና አንድ ነው እኔ እገዛ እኔ እገዛ ነበር ፣ ይህ ደግሞ ጎሳን ወይም ዕምነትን ብቻ መሰረቱ አድርጎ ነበር ከደቡብ ተነስቶ ወፈሰሜን ግዛት ለማስፋፋት ዘመቸሰ ሲደረግ በደቡብ የሚኖሩ ሁሉም ወደሰሜን ይዘምቱ ነበረ ።
ከሰሜኑ ተነስቶ ወደቡብ ለማስገበር ሲዘመት በሰሜኑ ያሉት በሙሉ ዘር ቋንቋ ሳያግደው ሁሉ ወደ ደቡብ ይዘምት ነበረ ።
ከምሥራቅ ተነስቶ ወደመሀል አገር የተደረጉ ጦርነቶች ነበሩ በምሥረቅ የሚገኙ የሁሉም ብሔሮች በአንድ ላይ የዘመቱበት ።
ዞሮ ዞሮ ያ በዘመኑ የነበረ የጦር አበጋዝ
እንዴት ተፈጠረ በብለን ስንጠይቅ
የጦር አበጋዝ መሪ ለመሆን ከናት ልጅ ወንድሙ ጋር የሱን መሪነት አምኖ ካልተቀበለ በጭካኔ ይቀጣዋል ።
በኢትዮጵያ የንጉሣውያን ሥርዓት በታሪክ እንደምንረዳው አዲሱ ንጉሥ የቀደመውን ንጉሥ በተ ሰብ ቁርባን ይሆናሉ ዳግም እንዳያምፁ እንዳያሳምፁ አይቀጡ ቅጣት ይፈፀምባቸዋል ለዚህም ምሳሌ የቅር ትዝታዎችን መጥቀስ ተገቢ ይመስለኛል ።
አፄ ቴዎድሮስ በመሳፍንቶች ተከፋፍላ እጅግ ተዳክማ የነበረች ሀገር አንድ ለማድረግ የመጀመሪያ ጦርነት የጀመሩት ከባለቤታቸው አባት ጋር ነው ። ሲቀጥልም ከወጡበት የአማረኛ ቋንቋ ተናጋሪው ሕዝብ ጋር በመዋጋት ብዙ ደም ከፈሰሰ በኋላ በአማራ ክልል የሚገኙትን የመሳፍንትና ንጉሦችን ካስገበሩ በኋላ ነው ወደሰሜን ኢትዮጵያ ያቀኑት ።
ሕውሓት ከትግራይ ሲመሰረት ሰባት ሁነው ይጀምሩት እንጅ አቅም እየፈጠሩ ኃይላቸው እየጠነከረ ሲመጣ ከትግርኛ ተናጋሪው ውጭ ያሉ ሕብረ ብሔሮች አብዛኛው ጠላትብሎ ሕውሓት ከፈረጀው የአማረኛ ተናጋሪው ሕዝብ ከፍተኛ የሰው ኃይል ድጋፍ በማግኘቱ በነፃነት አማሮች ሰፍረው በሚኖሩበት አካባቢ ከገበሬው ከፍተኛ ድጋፍ እያገኘ ነበር ወደ መሀል አገር የገሠገሠው ። ምክንያቱም የደርግ አንባ ገነን አገዛዝ ያለፍርድ በጎንደር ፣ በጎጃም በወሎ ሕዝብ ላይ ከፍተኛ ሰዎችን የገደለበት አካባቢ ስለነበር ። በደርግ ላይ ከፍተኛ ቂም የነበረበት ሕዝብ የኋላውን ሳይገምት በግብታዊነት ሕውኃት የደገፈው ከደርግ አገዛዝ የበለጠ አረመኔ አንባ ገን ይመጣል የሚል ግምት ያልነበረው የየዋሁን ሕዝብ በጎና ቅንነት እንደሞኝነት ተጠቅመውበት ኢትዮጵያን ከተቆጣጠሩ በኋላ እያበላ እያጠጣ መንገድ እየመራ ድብላቸው በትክሻው እንደ አህያ ተሸክሞ እንዳላገለገላቸው ውለታውን ክደው በዘሩና በቋንቋው ምክንያት እራሱን እየረዳ በሚኖርበት በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች አማራ አገርህ አይደለም እየተባለ ተገሏል ፣ ሀብት ንብረቱን ተወርሷል ፣ ከሥራ ገበታ ፣ከትምህርት በፀት ልጆቹ ተባረዋል አይ ሲስ ተብሉ ከሚጠራው ድርጅት ከፈፀመው ጭካኔም በላይ ከሕውሓት ሥልጣን በያዘ ማግሥት ምንም ስለፖለቲካ በማያውቁት ገበሬዎች ላይ ካድሬ አሰልጥኖ የጎሳ ሚሊሻዎችን መሳሪያ አስታጥቆ በአማራ ተናጋሪ ገበሬዎች የጅምላ የዘር ማጥፋት እንዲካሄድባቸው ተደርጓል ።
ሕፃናት እንደ ዶሮ አንገታቸው እየተቆረጠ ተጥሏል ።ሰው ከነ ሕይወቱ ቆዳው እንደስልቻ ተገፏል ነፍሰ ጡር እናት በማሕፀኗ ያለን ፅንስ ቀደው በማውጣት ሽሏን ከመሞቷ በፊት እንድታይ ተደርጓል ።
ለዚህ አሳዛኝ የዘር ማጥፋት ድርጊት የኦሮሞው ኦነግ ተብሎ የሚጠራው ድርጅትን የሚወነጅሉ አሉ አብዛኛው ሰው የግፉ ቀማሽ ሰለባዎች ከእልቂቱ የተረፉትም በዚህ አይስማሙም ።
ከበስተኋላ ሁኖ ነገሮች የሚያቀናብረው ሕውሓት እንደነበር በተለይ ጄኔራል ሰዓረ መኮነን ጀኔራል ሳሞራ የኑስና የወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስተር የነበረው ታምራት ላይ በቅርበት የነበሩ ናቸው ።
ሁሉም ነገሮች የሚፈፀሙት ግን ከመለስ ዜናው ፈቃድ ሲገኝ ብቻ ነው ።
በየትኛውም ቦታ አማሮች የሚናቀሉበት አካባቢ በኢንበስተር ሥም ቦታውን የሚረከቡት ደግሞ የሕውሓት አባሎች የትጋራይ ተወላጆች ናቸው ።
ኢትዮጰ ጵያ ታሪክ ዘርን መሰረት ያደረገ ፖሊሲ ዘርግቶ በስላጣን የወጣ ሕውሓት ከቀደሙት ሁሉ ልዩ ያደርገዋል ።
ሕውሓት ከሥልጣኑ በኋላ ለቀሪው ትውልድ ምን እያወረሰ እንደሆን አያውቀውም ።
በርግጥ ሀገር እንዱህ በድንቁርና ለሩብ ዓመት ስትመራ ለምን የማይል ሕብረተ ሰብ እጅግ አጠያያቂም ከመሆኑም በላይ ታሪክ የማይረሳው የዚህ ትውልድ አሳፋሪ ጊዜም ነው ።
ሕውሓት ኢትዮጵያዊ አይደለም ኢትዮጵያ በባዕድ ዕጅ ተይዛ ሀገር በቀል ኒኦ ኮሎኒያሊዝም ሥር ወድቃ አሜን ብሎ ነፃነቱን በባርነት ቀይሩ መብቱን ተነጥቆ በአሽከርነት ለማገልገል ራሱን አሳልፎ የሰጠ ትውልድ ነው ።

Shagiz Shagi's photo.