ሰብዕሰ ከንቱ ይመስል
ወመዋዕሊሁሰ ከመ ፅላሎት የኃልፍ
—: ######/////######### :—
የሰው ልጅ ከንቱ ነገርን ይመስላል
ቀኖቹም እንዲሁ እንደ ጥላ ያልፋሉ ።
ወጣት ሳሙኤል አወቀ በዚች ምድር የኖረው ለ27 ዓመት በቻ ነው ።
ነገር ግን ወጣት ሳሙኤል ሰው ከንቱ እንደሆነ የተረዳ ይመስላል ።
ወጣቱ ይችን አጭር ሕይወቱን በከንቱ አላሳለፋትም ።
እንደሌሎች የዕድሜ እኩያቶቹ በሱ ደረጃ መድረስ የነበረበትን የትምህርት ደረጃ በሕግ የዩኒበርስቲ ተመራቂ ነው ።
ሀገሪቱ በለላት አቅም ሳይማር ላስተማረው ሕዝብ ወረታውን ለመክፈል ብዙ ጥረት አድርጓል ።
በሕዝብ ላይ የሚደርሰውን ብልሹ አስተዳዳር በማጋለጥ በተለይ በጎጃም ገበሬዎች ላይ ሕገ ወጥ የመሬት ወረራን ፣ሙስናን አድልዎን ያጋልጥ ነበር።
በዚህ የተነሳ በሥልጣን ያሉ አካላት ይህ ነው የማይባል ወከባና እንግልት እስከገደሉባት ቀን ድረስ ለወጣት ሳሙኤል የለት ተዕለት ዕጣ ፋንታው ነበር ።
ወጣት ሳሙኤል ትዳር የመመስረት እንደ እኩያቶቹ ብር አንባ ሰበረልዎ እስኪባልለት ድረስ ጠላቶቹ ትዕግሥት አልነበራቸውም ። እሱን በህይወት የመኖር ሕልሙን ለማሳጠር ተጣደፉና በተወለደ በ27 ዓመቱ ተወልዶ ባደገባት ከተማ በደብረ ማርቆስ እንደ ዕባብ ራሱን ቀጥቅጠው ገደሉት ። የወጣት ሳሙኤል አስከሬን ከአንገቱ ባላይ የደረሰበት ከመቀጥቀጡም በላይ በስለት መቆራረጡ እሱነቱን መለየት እሰከ ማይቻልበት ሁኔታ ነበር የታየው ።
R.I.P. 2007

Shagiz Shagi's photo.