ከአንድ  መንደር  በመጣ በግል  በባለቤትነት የሚመራዉ ጣይቱ ሆቴል ሆን ተብሎ በወያኔ ሴራ መቃጠሉን ፍንጮች እየጠቆሙ ነዉ
በቅርቡ ለዘመናት በወመዘክር ይገኙ የነበሩ የኢትዮዽያን ታሪክ በተለያዩ ያለም ቋንቋወች የያዙ መዛግብትና ጽሁፎች በወያኔ ትዕዛዝ ለስኳር መጠቅለያነት እንዲወገዱ መሆኑን ተከትሎ አህን ደግሞ በኢትዮዽያ ታሪክ የመጀመሪያዉ ሆቴል የሆነዉ የእቴጌ ጣይቱ ሆቴል በተቀነባበረ ሴራ እንዲቃጠል ሆኗል።እነዚህ ቂመኛ የባንዳ ዉላጆች በተመሳሳይ ከይሲ ድርጊታቸዉ ቀደም ሲል በልማት ስም የ አቡነ ዼጥሮስን ሀዉልት እንዲነሳ ማድረጋቸዉ፥የሉሲን ቅሬታ አካል ወደ አሜሪካ በመላክ በአሜሪካ ሰራሽ አርተፊሻል ቅሬት አካል መተካታቸዉ፣ጥንታዊ ገዳማትና አድባራትን በልማት ስም ማፍረሳቸዉናመድፈራቸዉ፣እንዲሁም የቅርስ ምዝገባ በሚል ሰበብ የተለያዩ የቤተ ክርስቲያን ንዋዬ ቅድሳትና ጽላትን ሳይቀር ለምዕራቡ አለም መቸብቸባቸዉ ያደባባይ ሚስጢር ከሆነ ሰነባብቷል።
ከላይ እንደተጠቆመዉና የዚህን ጽሁፍ መነሻ የሆኑኝ ሀገር ወዳድ ፀረ- ወያኔ አራማጆች በሚከተለዉ መልኩ እንዳጋሩን ቅርስን የማወደምና ለጥቅም ያመነዘረዉን ቦታ የማቃጠልና የመጠቅለል የካበተ ልምድ ያለዉ ይህ ቀናተኛ፣ምቀኛና ሁልጊዜ የበታችነት የሚሰማው፣ ከሃዲ የባንዳ ቡድን ዛሬ ከታሪካችን አንዱ የሆነውን የመጀመሪያውን የጣይቱን ሆቴል በእሳት እንዳጋየዉና እንዳወደመው ሁሉ የጀግናውን አርበኛና ከጣሊያን ጋር ለህይማኖታቸውና ለሀገራቸው ሲታገሉ በጣሊያን የተረሸኑትን የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልትንና የመጀመሪያውን በአፄ ምኒልክ የተሰራውን የባቡር መንገድ ከአፈረሰው ሰንበትበት ብሎአል። ይህ ምቀኛና የታሪክ ቀበኛ የሆነ የባንዳ ቡድን ኢትዮጵያንና ታሪኩዋን ለማፍረስ ከመጀመሪያው “የትግሬ ነፃ አውጭ ድርጅት ነኝ” በሚለው ማኒፌስቶው ላይ በግልፅ ያስቀመጠው ቢሆንም ፀረ-ኢትዮጵያነት አቋማቸው ገና ከጫካ ጀምሮ በነ መለስ ዜናዊና በነ ስብሃት ነጋ ሲንሸራሸር የቆየ ቢሆንም በኢትዮጵያና በኢትዮጵያዊነት ያላቸው ጥላቻ እንዲህ የከፋ መሆኑን በግልፅ የታየው ኢትዮጵያን በአረቦችና በምእራባዊያን ድጋፍ ወረው ከያዙ በኋላ ነው። ራሱን “የአልባንያ ኮሚኒስት ፓርቲ ፍልስፍና ተከታይ ነኝ” ይል የነበረው ይህ ከሃዲ የባንዳ ቡድን ዛሬ ጌቶቹን ለማስደሰት “የነፃ ገብያ አቀንቃኝ ነኝ” ቢልም ዋናው አላማው ግን ኢትዮጵያን ለማጥፋት ከማናቸውም የውስጥና የውጭ ጠላቶች ጋር መተባበር ነው። በመሆኑም ኢትዮጵያ የዓለም የጥቁር ሕዝቦች መኩሪያ የሆነችውን ኩሩ ሕዝቦቿን አንገት ለማስደፋት የማይፈጽመው ግፍ የለም። ይህ ዘረኛና ጎጠኛ ስርአት ለሃያ ሶስት ዓመት በሕዝባችን ላይ የፈፀመውን ግፍ ሁሉንም አሁን መዘርዘር ባይቻልም አሁንም ይህን ግፍ እያየ ሕዝቡ በተለይ ወጣቱ (ከጥቂቶች በስተቀር) እጁን አጣምሮ ዝም ብሎ ማየቱ በጣም ይገርመኛል። እውነትም ወያኔ እንደሚለው “ፈሪ፣ሽንታም …… ?” ለመሆኑ መቼ ነው ሕዝቡ አሁንስ በዛ!በቃ ብሎ የሚነሳው ? ለምንድ ነው ትግሉ ለተወሰኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ብቻ የሚተወው??? ጀሮ ያለው ይስማ ፣ልብ ያለው ልብ ይበል፣አእምሮ ያለው ያስተውል! ሕሊናና አገር በሆድ አይሸጥምና እባካችሁ ወገን የወያኔ መሰሪ አገርና ህዝብ አፍራሽ ሚና ለመረዳት ጊዜ ሳናባክን ራሳችንን ለመከላከል ለጸረ ወያኔ ሁሉን አቀፍ ትግል እንዘጋጅ፣እንቀላቀል።
የባንዳ ርዝራዥና ዉርዴ ዉላጅ “ወያኔ ሆይ”:- ቅስማችሁ እንክት ይበል እንጅ የጣይቱ ልጆች መነሳሳት፣አገዛዙን የሚጎሽሙ የተለያዩ የግጥም መድብሎች በእቴጌይቱ የሆቴል አዳራሽ ማንሰራራታቸዉ ጥንታዊ ቅርስን በማቃጠል አይቀለበስም፣ቅስምን መስበር መቼም ቢሆን አይሳካም ይበልጥ የማይቀረዉን ሞታችሁን ያፋጥናል እንጅ።
ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ለዘላለም ይኑር !!!

Abakostir Belay's photo.