ከሲኦል የተጣለች ፍትህ የተራበች ነፍስ
®®®®®®®\\\///®®®®®®®
አዲስ አበባ ምድራዊው ሲኦል ማዕከላዊ እስር ቤት ።
ብዙ ያልተሰሙ የፀዓር ድምፆች ቢኖሩም እንደ ተዓምር ሁኖ እስትንፋሳቸው የተረፈ ሁሉ ስለ አዲስ አበባው ምድራዊ ገሀነም በየጊዜው የስቃዩ ሰለባዎች ይነግሩናል በርግጥ ከራስ በላይ መረጃ ስለማያስፈልግ ከራስ በላይ ለራስ መረጃ መጥራት አይሻም ።
በዚህ አስቀያሚ እስር ቤት ከአንድ መንደር በመጡ ዘረኞች ከሚጠሉት ዘርም በላይ የስልጣን ተቀናቃኛቸው ላይ የሚፈፅሙት ብዙም ላያስደን ይችላል ።
ምክንያቱም ታሪክን ወደኋላ ብንመረምር ።
ዘረኝነት ስብዕናን ስለሚጋርደው ለአዋቂ ቀርቶ በናቱ ማሕፀን ለተቀመጠ ሕፃን የሚራራ ሕሊና ለዘር አምላኪዎች አይኖራቸውም ።
ከዚህ ቀደም እንደታዬው በኦቶማን ቱርኮች የዛሬ መቶ ዓመት በአርመኖች የተፈፀመው ጭካኔ አይተናል ።
ከዛሬ ሰባ ዓመት በፊት ዘረኛው የጀርመኖች ናዚ ሴት ወንድ ፣ ሕፃን ሳይል ማጥፋት በፈለገው ዘር ላይ ሰውን ያክል ክቡር ፍጡር ከመግደልም በላይ እንደትል ተጫውተውበታል ።
በሰው ልጅ ላይ እንደአይጥ በቤተ ሙከራ በማስገባት ለምርምር አውለውታል ።
በሩዋንዳ የዛሬ ሀያ ዓመት የተፈፀመውን ሁላችን እናውቀዋለን ።
አሁንም በሶርያ በኢራቅ እየተፈፀመ ያለ ነው ።
ኢትዮጵያ የሚካሄደው የዘር ጥላቻ ሰለባ የሚደረጉት ስልታዊ በሆነ አካሄድ ፈፃሚው አካል ደግሞ የተረጋጋና የአንዲት ሀገርን ሁለንተናዊው የተቆጣጠረ በኘሆኑ የዓለምን ሕብረተ ሰብ ማታለል የሚችልበት አቅሙ ከፍ ያለ በመሆኑ በሽብርተኛ ሽፋን ዘር ማጥፋት መፈፀሙ ልዩ ያደርገዋል ።
ዘረኛው ቡድን ያልተረዳው ቢኖር 21 ኛው ምዕተ ዓመት
—18ኛውና 19ኛ 20 ኛው ክፍለ ዘመን
አለመሆኑን ነው በአሁኗ ሰዓት መረጃው ባደገበት ሰዓት ዓለምን ወደ አንድ ጎራ ባመጣበት ወቅት የዘር ማጥፋት ሥራን ቀላል እንደማያደርገው ማወቅ የተሳናነው ነው ።
አበበ ካሴ አሁን የሚገኘው ዘረኛች በሚቆጣጠሩት በር በተዘጋበት ሲኦል ነው ።
አበበ መለዕክቱን ያስተላለፈው ያለበት ሁኔታ ከዛ አስከፊ ሲኦል በሕይወት እንደማይወጣ ስለሚያውቅ ነው ።
አበበ ሁሉንም አጧል መልዕክቱን በማስተላለፉ የሚያጣውም የሚያገኘውም የለውም ።
ለዚህ ነው በዘረኞች መንጋጋ ውስጥም ሁኖ መልዕክቱን ከምድር በላይ ለሚኖሩ የሰው ልጆች እንዲደርስ ያስተላለፈው ።
አበበ ለሱ ሞት እንደፀጋ እንደሆነችለት ከመልዕክቱ እየተረዳን ነው ።
የአበበ ካሴ መልዕት ዓላማ እሱ ያለፈበትን በሌሎችም ላይ እንዳይፈፀም አጥብቀን እንድንቃወም ነው ።
ብዙ አበበ ካሴዎች በዚህ አልፈዋል መልዕክት የማስተላለፍ ዕድሉን ባያገኙም ።
አዎ ብቸኛዋ የሴት “ መንግሥት ገልባጯ”
በወ/ሪት የካባ አለሙ ላይ የተፈፀመውን እናስታውሳልን ።
በነጀኔራል ተፈራ ማሞና በነጀኔራል አሳምነው ላይ እንዲሁ ነው ። በእስር ቤት የተገደሉም አሉ ብዙዎች
ነፍጠኛ ተብለው በቅርቡ ከሶስት ወር በፊት 2007
በሌሎች ሀገሮች ብዙ ነፍስ ያጠፉ አሸባሪዎች አንዴ በቁጥጥር ከተያዙ ፍርድ ቤት የሚወስንባቸውን ቅጣት እስኪቀበሉ የሚደረግባቸው ምርመራ መረጃን ለማግኘት ዳግም በሰው ሕይወት ላይ ጥፋት እንዳይደርስ ነው ።
የኞዎቹ አሸባሪዎች ከብዕር የዘለለ ምንም ዓይነት ጦር መሳሪያም የላቸው በሕይወታቸውም ለሰው ልጅ መብት መቆርቆር የሀገር ፍቅር ነው ባሕርያቸው ።
በባዶ እጃቸው መብት ለመጠየቅ በወጡ ሰላማዊ ዜጎች ላይ ድብደባ ይፈፀምባቸዋል ከዕስራት ባሻገር ።
የሚደበደቡትም ከኑን ጠብቆ ሊያመረቅፅ ና ለካንሰር የሚዳርጉ ስስ አካላቸው ላይ ነው ።
ሴት ልጅ የምትመታው ጡቷና በማፀኗ ዙሪያ በመርገጥ በተደጋጋሚ ኩላሊቷ ላይ ነው ።
ወንዶች የዘር ፍሬና ኩላሊት ጭንቅላታቸው ላይ ነው ።
በወጣት ሳሙኤል ያየነው ከመገደሉ ቀደም የተፈፀመበት ድብደባ የእግሮቹን መገጣጠሚያ ባሻገር በጭንቅላቱ የደረሰበት ድብደባ ደም ወደውስጥ እንዲፈስ ነው የተደረገው በውስጥ አካሉ ላይም ከባድ የሕክምና አገልግሎት እንደሚያስልገው ካልሆነ ወደካነሰር እንደሚቀየር ሀኪሞች እንደነገሩት በኑዛዜ ቃሉ አስቀምጧል ።
አማራን መገደል ማፈናቀል ማሰር መደብደብ ወንጀል ሳይሆን ለገዡ ቡድን ታማኝ የሚያደርግ ወደሥልጣንና ወደሀብታም ጎራ የሚያሻግር ታላቅ መሰላል ነው በሕውሓቶች ክራይቴሪያ
ይህን ያልኩበት ከዚህ ቀደም በዘረኝነት ተነሳስተው በተላያዩ አካባቢዎች በኃላፊነት ተቀምጠው የዓለም ዓቀፍን ሕግ ተፃረው የዘር ማፅዳት የሰሩ ዛሬ በሚኒስተር ማዕረግ ላይ ይገኛሉና
አይካድም ብዙ መረጃዎች አሉን ።

Shagiz Shagi's photo.
Shagiz Shagi's photo.
Shagiz Shagi's photo.
Shagiz Shagi's photo.
Shagiz Shagi's photo.
+4