ለኔ ሁሌም እንቆቅልሽ የተቃዋሚ ሥነ
።።።።።።።።።።።።።።።።። ምግባር ነው ።
ተቀዋሚ ነን ይሉና የተቃዋሚ ተቃዋሚ በመሆን እየጠለፉ መጣል የዘወትር መለያችን ከሆነ ቆይቷል ።
— አንዳንዶች በማሕበራዊ ሚዲያ የራሳቸውን ድሕረ ገፅ ይክፍታሉ ሁሉም እንደአቅሙና እንደችሎታው መጠን የመሰለው ይፅፋል የመሰለውን በምስልና በቪዲዮ አቀናብሮ ያቀርባል ።
በዚህ የታዘብኩት ነገር አለ በሌሎች የዓለማችን ሰዎችና በኛዋ ዘርፈ ብዙ ችግር በገጠማት ሀገር ሰዎች የሚያደርጉትን ሳወዳድረው እጅጉን ያሳዝነኛል ።
በሌ ላ ሐገር ሰዎች በአንድ የሕብረተ ሰብ በሆነ ድኅረ ገፅ ከተከፈቱ ዓላማው ዓንድ ከሆነ የበለጠ ታዋቂ እንዲሆን ሁሉም በያለበት ላይክ በማድረግ ሌሎችን እንቫይት በማድረግ ሸርና ኮሜንት በመስጠት ባጭር ጊዜ ውስጥ ማሳደግ ፣ በመቶ ሽህ የሚቆጠሩ ሰዎች ባንድ አድርጎ ወቅታዊ በሆኑ ጉዳዮች በሀገር ጉዳይ ላይ ሀሳብ መለዋወጥ ይቻል ነበር ።
—በኛ ማሕበረ ሰብ የሚታየው በተቃራኒ ነው አንድ ጓደኛዬ በከፈተው ድኅረ ገፅ ገብቸ ኮሜንት ባዳርግለት ገፁን ሸርም ባደርግለት ጓደኞቸንም ጥሩ ድኅረ ገፅ መሆኑን አስታውቄ እንባይትም ባደርግለት ቢቻል አስተያየት መስጠት ካልሆን ጊዜ የማይወስደውን አንዴ በመጫን ላይክ ማድረግ ልማዱ የለም ።
ከሁሉ በላይ የሚገርመኝ አነተ የለጠፍከውን እንዳለ ወይም በሱ ሥም ቀይሮ ሲያቀርበው ላንተ ምንም ክሬዲት ሳይጥ ነው ።
ይህ የተለመደ የኢትዮጵያውያን በተለይ በአንድነት እናምናለን በሚሉት የበለጠ ይጎላል ።
እንዴት ነው አንድነትን ማጎልበት የምንችለው? ይህ የጥሎ ማለፍ አካሄዳችን የትም አያደርሰንም ባለነው እየረገጥን ተስፋ እየቆረጥን ምንም የማያውቅ ትውልድ እየተካን እናልፋለን ።
በሁሉም መስክ አንድነታችን ለማጠንከር የምንሄድበት መንገድ ሊታስብበት ይገባል ለወያኔ መሻሪት መድኃኒቱ አንድነት መሆኑ ታውቋል ተረጋግጧል ።

Shagiz Shagi's photo.
Shagiz Shagi's photo.
Shagiz Shagi's photo.
Shagiz Shagi's photo.