ሕውሓቶች የሚያስቡት እንደ ሰው ነው?

¶¶¶¶¶¶¶¶¶\\\/////¶¶¶¶¶¶¶¶
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
:— ይህን ለጋ ወጣት ያለፈ ናፋቂ እንዳልሆነ ያውቁታል ።
:— ወጣቱ የመብት ተሟጋች ለምን እንደሚሞት አስቀድሞ አውቆታል ሞት ምንጊዜም ከሁላችን የሚኖር ማንኛውም ሰው ሟች ና በስባሽ እንደሆነ ያውቃል ሞት ወደድነም ጠላነም አይቀርም ።
ስለሆነም የሞት ሞት የሚባለውን አይቀበለውም እየፈሩ ያለነፃነት መሞት ከጀግኖች አባቶቹ አልተማረም ።
ሕውሓት እንደሰው ማሰብ ቢችሉ ኖሮ የገደሉት ይህን ለጋ ወጣት ሳይሆን መላውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ነፃነት ፈላጊውን መሆኑን ይረዱት ነበር ።
በወጣት ሳሙኤል ልቡ ያልደማበት ሕሊናው ያልቆሰለበት በዓለም ዙሪያ ተበትኖ የሚኖር ኢትዮጵያዊ የለም ። የለም ።
:— ሕውሓት ደም የተቃባችው ከሚሊዬን የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ነው ።
:— ሕዝብ ቂሙን እንደማይረሳ ከደርግ መማር ይኖርባት ነበር ።
በደርግ ዘመን በበረሀ የትጥቅ ትግል ስታካሂዱ ለ17 ዓመት የፈጀባችሁ ዓላማችሁ ሕዝብ ባለመቀበሉ ነበር ።
:— ሕውሓት ልብ የምትይው ነገር አለ እሱም ደርግ ምን ያክል የኢትዮጵያ ሕዝብ ይጠላው እንደነበር ታውቃላችሁ ነገር ግን አሁን ላይ ሁነን ስናይ ደርግ መልዐክ ነበር ።
— እናንተን በትጥቅ ትግል ከሥልጣን ለማባረር 17 ዓመት የሚወስድ አይመስለኝም ውጊያ ውስጥ እስኪገባ ነው ።
ነገሩ ከተጀምረ በሕዝብ የተጠላ ምንም ኃይል ቢኖረውም ያለ ሕዝብ ድጋ ራሱን ችሎ እንደማይቆም መገመቱ መልካም ነው ። ሕውሓት ከዓመት ወደ ዓመት በሕዝብ ላይ የምትፈፅመው ግፍ የአስተዳደር መበላሸት ስርቆትና ቅጥፈት እንዲሁ መረን የለቀቀ መፍትሔ የማይገኝለት ሙስና ከሕዝቡ አልፎ እራሷን እየበላ ና እየገዘገዛት ይገኛል ።
ሕውሓት ሕዝብን አሸንፋ አፍና በኃይል በመግዛቷ ብትመካም የምትጋዛውን ሕዝብ አጥብቃ ትፈራዋለች የፍራቱ መጠን እየከፋ መምጣቱን የምናውቀው መቶ በመቶ ምርጫውን አሸንፌአለሁ እያለችም የመብት ታጋዮችን ከእስክረቢቶ ውጭ ምንም በጃቸው የለለውን የመብት ተሟጋቾች ትገላለች ታስራለች ትደበድባለች ።

Shagiz Shagi's photo.