ያልተነካ ግልግል ያውቃል
:::::::::::::::::::////::::::::::::::
አንድ ሰው በተወለደበት እትብቱ ከተቆረጠበት አፈር ፈጭቶ ውኃ ተራጭቶ ባደገባት ምድር አንተ እንደዚህ ነህ ይባልና ለምንም አታስፈልግም ለምንም አትፈለግም ተብለህ ከባለ እንጀሮችህ ከዘመድ ቤተ ሰብህ ተገለህ በሀገር ባይተዋር ተደርገህ መኖር ምን ያክል ከባድ መሆኑን የደረሰበት ብቻ ነው አስከፊነቱን የሚያውቀው ።
ለዚህ ነው ያልተነካ ግልግል ያውቃል ያልኩበት ።
ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ በክልላችን ብዙም ባልራቀ ይንቀሳቀሱ ነበር ገና በበረኃ እያሉ ከሞላ ጎደል ባሕርያቸውን እናውቀው ስለነበር ።
ምን ይዘውልን እንደመጡ እናውቃለን የወያነን ዓላማና እስትራቴጂ እንረዳለን ።
ብዙኃን የሰሜኑ የሀገራችን አርሶ አደር የደርግን አገዛዝ ስለሚቃወም ብቻ ደርግ ይውደቅ እንጅ ከደርግ የከፋ ከሀገር በቀል መልካቸው መልካችን እምነታቸው እምነታችን የሆኑት ይቅርና ጣሊያን ተመልሶ ቢመጣ አሜን ብሎ የሚቀበል ሕዝብ ነበር ።
በተለይ በመላኩ ተፈራ የጭቃኔ ተግባር የጎንደር ሕዝብ ሞራሉ የተጎዳበት ሀገር ብሎ መሞት ምን ያክል ተስፋ የተቆረጠበት ዘመን በመሆኑ ለሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ መንገዱን እንቅፋት እንዳይነካው የጠረገለት መላኩ ተፈራ በኋላም እሱ መግደል ሲሰለቸው በኢሰፓ ማዕከላዊ አመራር በመንግሥቱ ኃይለማርያም ልዩ ትዕዛዝ አዲስ ነፍሰ ገዳይ ለጎንደር ሕዝብ ተመድቦለት ነበር ።
የመጀመሪያ ማዕረጉ መቶ አለቃ ገብረ ሕይወት ገብረ እግዚአብሔር የሚባል ሲሆን የተመደበውም የሰሜን አውራጃ አስተዳዳሪ እንዲሆን ነበር ።
ብዙም ሳይቆይ የወገራ አውራጃን ጠቅልሎ እንዲያስተዳድር ሥልጣን ተሰጠው ። በዚያ ወቅት በየደረሰበት ከገበሬ እስከምሁር ያለምንም ፍርድ ሞት በሎተሪ ሲደርስ ያየሁበት ነበር ።
ከዚህ ሁሉ በደል በኋላ የጎንደር ዕጣ በሕዝባዊ ወያነ ሓርነት እጅ እንደወደቀች የገጠማት ከደርግ የባሰ በደል ነበር የገጠመው ።
ደርግ ሲገድልም ሲያስርም በግልፅ ነበር ወያነ ድብቅና ሲስተማቲክ ነበር ።
ወያነ ገና ከጅምሩ ገበሬውን ምሁሩን ወጣቱን ከፋፍሎ ማየት ጀመረ ።
በዘር በሃይማኖት በጎሳ ከዛም ደጋፊና ተቃዋሚ በሚል እንደ ዕድል ሁኖ እኔ የተፈረጅኩት ተቃዋሚ ከሚባሉት ነበር ።
የተሰጠይ መደብ ሁለት ነበር ።
1/ ለገጠሩ ነዋሪ ኢድዩ እንደሆንኩ በኮር አባሎቻቸው ማስወራት ሲጀምሩ ።
2/ በከተማ ላሉት ባለእንጀሮቸና ዘመዶቸ መአድ ነው ይሉኝ ነበር ።
እኔ ግን አንዱንም አልነበርኩም ።
ኢድዩ ማለት ምን እንደሆን በዘመነ ደርግ መጀመሪያ ላይ ውጊያ በአካባቢ ይደረግ ስለነበር በሱም ሳቢያ ኢድዩ እየተባሉ ብዙ ተረሽነዋል።
ኢድዩ ማለት በገበሬ ዘንድ አስፈሪ ነበር ።
መአድ የሚባለው በመገናኛ ከመስማት በስተቀር በክልላችን የሚንቀሳቀስ አልነበረም ።
በዛን ወቅት ሥራ ለመወዳደር ከባለእንጀሮቸ ጋር ለውድድር ስቀርብ ሁሉን ክራይቴሪያ አሟልቸ 32 ሰው የሚፈለግ ሲሆን በሁለተኛ ደረጃ ያለፍኩት እኔ ስሆን በክልሉ የወረዳው ሥራ አስፈፃሚዎች ጣልቃ በመግባት የኔን ደክመንት በማንሳት አንተን አይመለከትም ይህ ሥራ ተብዬ የተባረርኩባትን ዕለት ከ22ዓመት በላይ ዕድሜ ቢያስቆጥርም በአዕምሮየ ዘወትር ይመላለስብኛል ።
ነገሩ በዚህ አላለቀም ከሥራ በማባረር ክትሎች ይበዙብኝም ነበር አብረው ሻሂቡና የሚጠጡ የነበሩ ጓደኞቸ እንዲርቁኝ ተደረገ ። በሀገሬ ባይተዋር መሆን ጀመርኩ ብቻየን ለመሄድ ያስፈራኝም ነበር ፀሀይ ከገባች መዘዋወር አቆምኩ ።በዚያ እሰከመቸ እንደምቀጥል አላውቅም ነበር ።
ከዛ በኋላ በሀገር የመኖር ዕድሎች ሁሉ ተስፋ የሚሰጥ ባለመሆኑ ከሀገር የመውጣቱ ግዴም ስለነበር የአምላክ ፈቃዱ ሥለሆነ ሳልወድ በግድ ለሀገር ያለኝ ፍቅር ባይቀንስም እንደሌሎች ወገኖቸ በሀገር ቤት ሁኘ ሞትም ቢሆን በፀጋ መቀበሉ እንደ አማራጭ ነበር።
አሁንም ከ24 ዓመትም አገዛዝ በኋላ እጅጉን እየከፋ እነደሄደ እረዳለሁ ለመረጃ በጣም ቅርብ ሁኘ የሀገሬን ሁኔታ እከታተላለሁ ።