እነዚህ ሰዎች “100% ምርጫውን አሸንፈናል” ብለውም ተረጋግተው መቀመጥ አልቻሉም። ሰላማዊ ፖለቲከኞችን ማሰራቸውንና መግደላቸውን ቀጥለዋል። የአረና ፓርቲ የአመራር አባል የሆነው Amdom Gebreslasie ከትግራይ ዛሬ ይፋ እንዳደረገው አቶ ታደሰ አብርሃ የተባሉ የዓረና-መድረክ ኣባልና የምዕራባዊ ዞን የዓረና ኣመራር ኣባል ትናንት ማታ በሶስት ሰወች ታንቀው ተግድለዋል 09/10/ 2007 ዓ.ም

አምዶም እንዳለው “ . . . ኣቶ ታደሰ ኣብራሃ በቓፍታ ሑመራ ወረዳ ማይካድራ ቀበሌ ኑዋሪ ሲሆኑ በዘንድሮው ምርጫ ወቅት በቀበሌው ኣስተዳዳሪዎች፣ ካድሬዎች፣ የሚቀርቧቸው ሰዎች ከዓረና-መድረክ ኣባልነታቸው እንዲለቁ የተሸመገሉ፣ የተለመኑና በመጨረሻም ዛቻዎች ሲደርስባቸው እንደነበረ ይታወቃል። ኣቶ ታደሰ ማታ 03:00 በ3 ሰዎች ኣንገታቸው የታነቁ ሲሆን ሶስቱ ሰዎች ሙቷል ብለው የተዋቸው ቢሆኑም ሂወታቸው እስከ 09:15 ኣላለፈችም ነበር። ኣቶ ታደሰ ኣብራሃ የ48 ዕድሜ ጎልማሳ ነበሩ። ኣደጋው 3 ሰዎች እንደፈፀሙባቸው፣ በኪሳቸውም 300 ብር የነበረ ቢሆንም ሰዎቹ ሊወስዱት እንዳልቻሉ ተናገረው ነበር። “

“የኣቶ ታደሰ ሬሳ በሑመራ ሆስፒታል ላለማስመርመር የማይካድራ ፖሊስ ትራፊክ በዓረና ኣባላት ላይ ከፍተኛ ጫና የፈጠሩ ሲሆን የተለያዩ የመንግስት ኣካላትም ምርመራው እንዳይካሄድ የተለያዩ ጫናዎች እንደፈጠሩ ኣባሎቻችን ከስፍራው ገልፀውልናል። ሬሳው ወደ ሑመራ ወስዶ ለማስመርመር የሚጠቅም መኪና ለመከራይ ሲባል ኣባሎቻችን የተካራት ሞተር ሳይክ በፖሊስት ትራፊክ ተከልክላለች. . . “

አንድ ሰው የተለየ የፖለቲካ አመለካከት በመያዙ ብቻ የሚታሰርበት፣ የሚሰደብበት፣ ከስራ የሚባረርበት፣ ከሀገር የሚሰደድበት ብሎም የሚገደልበት ሀገር።

ፈጣሪ ለቤተሰቦቻቸው፣ ዘመዶቻቸውና ጏደኞቻቸው መጽናናት ይስጥ።

Abenezer B. Yisihak's photo.