——እንዲህ ጦም አዳሪ በጎዳና ተዳዳሪ ሕጻናት ባሉባት ምድር ሌሎች በሀገር ቤት እንኳ ለመውለድ በተጠየፏት የእናት ሀገር ምድር ልጆቻቸውን ለመውለድ በሀገራቸው የልጃቸው እትብት ደም እንዳይፈስ ወደአሜሪካ ከሕዝብ በተዘረፈው የሕዝብና የሀገር ገንዘብ የትውልድ ቦታቸውን ሲያደርጉ ።
በኢትዮጵያ ትውልድ ገዳይ በሆነው ሥርዓተ ትምሕርት ልጆቻቸው እንዳይማሩ ከድሆችም ጋር ልጆቻቸው ተጠይፈው እንዳይማሩ ብዙ ሽህ ዶላሮች እተከፈሉ ወይም የነሱን ልጆት ተቀብለው ለሚያገለግሉ ሀገሮች የኢትዮጵያን የከርሰ ምድር ሀብቷን እንዲቦጠቡጡ ይደረጋል አንድም በነፃ የሀገሬውን ሕዝብ በማፈናቀል መሬት ቅርም ተጠቃሚ ይደረጋል ።
እኛ ና እነሱ የሚለው መድልዎ መቸና መቸ መጨረሻ እልባት እንደሚገኝ ባናውቅም አንዱ እየበላ ሌላው ጦም አዳሪ ሁኖ ግን አይቀጥልም ።
እነዚ ሕጻና በሀገራቸው ላይ ያላቸው ድርሻ ከነቴዎድሮስ አድኃኖም ልጆች ያነሰ አይደለም ። እኩል ነው ። ይህን እኩልነት ያፈለሰው ወይም ልዩነት የፈጠረው አንድም በዘር የተደራጀ አለበለዚያ በአፈሙዝ የመጣ በሕዝብ ላይ የተጫነ ግፍ ነው ።

Shagiz Shagi's photo.