ይድረስ ለኢትዮጵያዊ ወገኔ——
::::::::::::::::::://////    ይድረስ ለኢትዮጵያዊ ወገ    :::::::::::::::::::
በነገው ዕለት 16 /2007 በኢትዮጵያ የሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ምርጫ ( ልግጫ) የተባለው ምንም ማለት አደለም በአፈሙዝ ነው ወደስልጣን የወጣው እንዴት ነው በወረቀት ሥልጣን ለሕዝብ የሚለቀው ?
ሞኝ ፣ተላላው ፣የዋሁ የሀገሬ ሕዝብ ሆይ ለሩብ ምዕተ ዓመት እንዴት ነው ስትታለል የምትኖረው ?
በቃ ሊባል የሚገባው የስቃዩ ፍፃሜ ሊኖረው ይገባል እንዴት ነው ሰው በሀገሩ ባይተዋር እና በቀቢፀ ተስፋ የሚኖረው ።
በሀገሬ እኩል መብት ሳይኖረኝ እኛ ና እነሱ እየተባለ በነፃነት ዕጦት የመንፈስ ድኃ መሆን ያለው ትውልድ ብቻም ሳይሆን ለተተኪው ትውልድ የሚተላለፍ የሕሊና ደዌ ነው ።
ነፃነት በነፃ አይመጣም ከቁርጠኛ ትግል ነው የጀግኖች አባቶች ቆራጥ ተጋድሎ ምንም ድኃ ብንሆን ኮረተን ኑረናል ።
ባሁኑ ሰዓት የጀግኖች ውለታ አፈር ድሜ በልቷል ለሀገሩ እንደዜጋ ብሔራዊ ስሜቱ የተነካ ትውልድ በማፍራት ላይ እንገኛለን እንብኝ ለሀገሬ እንብኝ ለክብሬ የሚል ወጣት ትውልድ ፈልጎ ማግኘት ከእንግዲህ አስቸጋሪ ነው የሚሆነው ።
ከእንግዲህ ወጣቱ ትውልድ ከኛ የሚወርሰው እንደጥንት አባቶቹ ዘር ሃይማኖ ሳይለየው ለአንዲት ሉዓላዊት ሀገር ከውጭ የሚመጣን ጠላት ለመከላከል ልዩነት አያግደውም ነበር ።
ይህ አሁን በወጣቱ አዕምሮ የአያቶቹን አኩሪ ገድል ተረት ተረት ነው ተብሏል የጋራ ሰንደቅ ዓላማ ጨርቅ ነው ተብሏል የአክሱም ሀውልት ለወላይታው ምኑ ነው ተብሏል ።
አዲሱ ትውልድ ስለጠቅላላው የኢትዮጵያ መልክዓ ምድር ስለ አየር ንብረት የቆዳ ስፋት የተፈጥሮ ሐብት የማወቅ እድሉ የለም ለአዲሱ ትውልድ ሀገሩ ክልሉ ብቻ እነደሆነ ተነግሮታ የኦሮምያ ወጣቶች ስለትግራይ እንዲያውቁ ሥርዓቱ አይፈቅድም የአማራው ስለሱማሌው የአፋሩ ስለ ጋንቤላው አያውቁም ።የትምሕርት ሥርዓ ከክልል ወደክል የተለያየሙ ይመስለኛል።
የክልል አንድ የመማሪያ መፅሓፍ ላይ ታላቁ የሰሜን ተራራ በትግራይ ክልል እንደሆነም ያሳያል ይባላል ።
በተቃራኒው የክልል ሶስት ተማሪ በዩኒበርስቲ ደረጃ የተማረ በቅርብ የማውቀው በወገራ አውራጃ ተወልዶና አድጎ የአጎራባች ወረዳዎችን ስለ ጃናሞራ ወረዳ ስጠይቀው መልሱ አላውቅም የሚል ነበር ።
ሁሉም ቀልድ ነው ምርጫ የለም መራጩም ተመራጩም አስመራጩም እራሱ ስለሆነ በተበላ ዕቁብ ለውጥ የለም ብዙ አትስጉ ግርግር ይፈጣራል ለሚለው ሀሳብ አልጋራም ።
የሕዝ መነሳሳት ቢኖርም ከዚህ ምራጫ ጋር አይሆንም ።ይህን ስል የሕዝ አመፅ አይነሳም ማለቴ አይደለም የሰ የሚሆነው ግን እንዲህ በሰራዊት ተከቦ በታንክ ታጥሮ በሚገኝበት ቀን አይሆንም ሌሎች አጋጣሚዎች ሳይጠበቅ ያበጠው ሊፈነዳ ይችላል የሚል ግምት አለኝ ።
ለሁሉም እንዲህ በነፃነት እጦት ሲሰቃይ ለኖረ ሕዝብ እንደተራበ አሳ መቃጥ እንዲጎርሱ አለመኝም
መልካሙን ሁሉ ለሀገራችን እንዲሆን እመኛለሁ

Shagiz Shagi's photo.