·

ጎንደር ምዕራባዊ ክፍል ሰቲት᎗ሁመራ !
***************************
የቀድሞዋ የጎንደሬዎች ከተማ ሁመራ አሁን ደግሞ የጎንደሬዎች መቀበሪያዋ የጅምላ መጨፍጨፊያዋ ሁመራ በየቀኑ የወገን የድረሱልን የሰቆቃ ድምፅ ይሰማል ሁኖም ግን ሰሚ ጀሮን አላገኘም ።
ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ በሰሜን ጎንደር ምዕራባዊ ክፍል ከአማረኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያዊ የፀዳ ክልል ለመፍጠር ከ40 ዓመታት በላይ የሰራበት ቢሆን እንዳሁኑ ለይቶለት አያውቅም ቀደም ሲል በወልቃይት በጠገዴ በትግል በበረሃ እያሉ ጀምረው ነዋሪዎችን ሌሊት ሌሊት ከቤታቸው እያፈኑ የደረሱበት ሳይታወቅ የቀሩ አያሌ ወገኖች ነበሩ ።
ኢትዮጵያን ከተቆጣጠሩም በኋል ትልቅ ትኩረት ሰጥተው የዘር ማጥፋቱ ሥራ ቀጥለውበታል የተከዜ ወንዝ የኢትዮጵያውያን መቃብር ብንለው ይመረጣል በተከዜ ወንዝ የሚርመሰመሰው አዞ ቀለቡ የአማረኛ ቋንቋ ተናጋሪ የፀለምት ፣የወልቃይት ፣የሰቲት ሁመራ ፣የጠገዴ ነዋሪወች ናቸው ።
በማንኛው ሰዓት በማንኛውም ጌዜ ከቤቱ ታፍኖ ተገሎ የሚጣል ተቆርቋሪ ያጣ ሕዝብ ሁኗል ።
በምዕራብ ጎንደር ነዋሪዎች የሕይወት ዋስትና የላቸውም የንብረት ባለቤትነትም እንዲሁ ።ነተፈለገ ጊዜ ሀብታቸው የሚነጠቅ ቤታቸው የሚፈርስ ።
በሰሜን ጎንደር ነጋዴው በንግዱ ገበሬም በመሬቱ ላይ ከሚደርስበት በደል የተነሳ ምን ተሰርቶ ዘላቂ ሕይወትን እንዴት መምራት እንደሚቻል አይታወቅም ።
የሰሜን ጎንደር ምዕራባዊ ክልል በስፋት ከሱዳን ከሱዳን ጋር ይዋሰን ነበር አሁን ግን እጅግ ጠቦ በሰሜን ምዕራብ በኩል ወደታላቋ ትግራይ ሲከለል ፣የተቀረው ደግሞ ከቋራ በኩል የአፄ ቴዎድሮስ የትውልድ ቦታ ወደሱዳን የተከለለው እንዳለ ሁኖ ከወለጋና ከጎጃም ተቆርጦ እጅግ ለምና ውሃ ገብ ድንግል መሬት የአባይ ወንዝ መሠረቱ ያደረገ አዲስ ሀገር በሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ የምትመራ አዲስ ግዛት ቤሻንጉል ተብሎ ወደሚጠራው ተከልሏል ።
አሁን ለጎንደሬዎች የቀረች በኘተማ በኩል ሲሆን ይችንም ለመንሳት የሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ በሚቆጣጠረው በአንድ ቋንቋ ተናጋሪ ሁኖ በተዋቀረው ሠራዊት ተከቦ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴው ተስተጓጉሎ በዓይነ ቁራኛ እየተጠበቀ ሌሊት ሌሊት ለመግደል የሚፈልጓቸው ሰዎች ከመኖሪያ ቤታቸው እየታፈኑ ወደሁመራ ተወስደው እንደሚረሸኑ የየጊዜው ዋይታና ጩኸት ይሰማል ።
ይድረስ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በኢትዮጵያዊነት ለምታምኑ የሰሜን ጎንደር ምዕራባዊ ዳርቻ የሚኖር ወገንህ ደየሰቆቃ ድምፁን ያሰማል አለነልህ ልትሉት ይሻል ዳሩ ካልተከበረ መሀሉ ዳር ይሆናል ይለሀል ።
ሌላ ማድረጉ ቢሳንህ ድምፅ ልትሆነው ይገባል ።
የጎነደር ሕዝብ የራሱን ቀብር እንዲቆፍር ይገደዳል ።
አቶ ፈለቀ የዳንሻ ነዋሪ በ4/05/2015 በሁመራ በአንድ የጦር ካምፕ ርሸና ተፈፀመባቸው መረጃወረን የሰጠው አብሮ የነበረ ወጣት ሕይወቱ በተዓምር የተረፈ የአይን ምስክር ነው ።

Shagiz Shagi's photo.