ፓይሌት ፣ዶክተር፣ ስፔሻል ሰርጀር፣ፕሮፊሰር
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ፕሮፊሰር አሥራት ወልደጌስ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
:— በወገኑ ላይ የተደቀነውን አዳጋ ቀድሞ የተረዳ ሕውሓት ገና ከጅምሩ አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ ከደርግ አስከፊ ሥርዓት መውደቅ ጋር በተዘበራረቀ ብዥታ በነበረበት ወቅት ነበር በበደኖ ፣በአርባ ጉጉ ፣ በአርሲ ፣በኡጋዴን ፣በጋራ ሙለታ ፣በሀረር ፣በድሬዳዋ በነበሩ የአማረኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያን ሕፃን ፣ሴት ወንድ ፣ሽማግሌና አዛውንት ፣በሆድ ውስጥ የነበረን ፅንስ ሳይቀር እናት ከነህይወቷ እያለች ሆዷን ቀደው ፅንሷን አይታ እንድትሞት ሲደረግ ይህን ለማስቆም ብለው የማይፈልጉትን በዘር መደራጀት ግዴታና አማራጭ የማይገኝለት የወቅቱ አንገብጋቢ ጥያቄ ነበር ። አሁን ላይ ሁነን ስናየው ፕሮፊሰር አስራት ትክክል ነበሩ ።
መአድ ( የመላው አማራ ድርጅትን) መሠረቱ ብዙ ተከታዮችን አገኙ በተለይ የወገን ሰቆቃ በተፈፀመበት አካባቢ ብዙ ለወገን ተቆርቋሪን አፈሩ ዳሩ ምን ይሆናል ከመሀል ሰፋሪ ምሁራን ነን ባዮች አድርባይ ብዙ የአፍራሽ ተግባር ቢገጥምም ለጊዜው ያን የጅምላ የዘር ማጥፋት ጨርሶ ባይቆምም በመጠኑ እንዲቀንስ አድርገዋል ።
በዚሕ ሥራቸው ከባድ የሕይወት ዋጋ እራሳቸውንጨምሮ ብዙ ባለብሩህ አዕምሮና ለወገን ተቆርቋሪ የገዥው አካል ሰለባ ሁነው ቀርተዋል በመአድ በድርጅቱ አባል ሁነው ይሰሩ የነበሩ ይህን ድርጅት ይደግፋሉ የተባሉ ከምሁር እስከ ተራ ገበሬ ከገጠር እስከ ከተማ አያሌ የአማራ ልጆች በመአድ ተፈርጀው ተገለዋል ፣ከቤት ታፍነው የደረሱበት ሳይታወቅ የቀሩ ከሥራ ገበታቸው የተፈናቀሉ ፣ ከቤታቸው ከድርጅታቸው የተፈናቀሉ ሰበብ እየተፈለገ የተጉላሉ አያሌ ወገኖች ነበሩ ።

Shagiz Shagi's photo.