—— መአድ ( የመላው አማራ ድርጅት )——
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
:— ፕሮፊሰር አሥራት ወልደጌስ እውነተኛ ነበሩ ።
ገና ከመባቻው ይሆናል ብለው የሽግግር መንግሥት ምሥረታ ሊቋም በአዲስ አበባ በ1983 ዓ / ም በወርኃ ሰኔ በተደረገው ጉባኤ የኤርተራው ነፃነት ግንባር መሪ ና የሕውሓቱ መሪ መለስ ዜናዊ በተገኙበት ለሁለቱም ማሳሰቢያ ብለው ለሁለቱ ሕዝቦች ጠቃሚ ያሉት ሀሳብ አቅርበው ነበር ነበር በመለስ ዜናዊ የጉባኤ መሪነት ውድቅ ተደረገ ።
ፕሮፊሰሩ ወክለው የቀረቡት የዩኒቨርስቲውን ማሕበረ ሰብ ነበር ግን ሀሳባቸው ተቀባይነት ባለማግኘቱ ከጉባኤው ራሳቸውን አገለሉ ።
ይህ በዚሁ አላበቃም ራሳቸውን ካገለሉ በኋላ ሀገሪቱን የተቆጣጠረው ቡድን ጥርስ መግባት ጀመሩ ።
ሁኔታው እየከፋ መጣና አማረኛ ተናጋሪዎች ላይ ከፍተኛ የሆነ የዘር ጭፍጨፋና የጅምላ ማፈናቀል ይካሄድም ነበር ።
ፕሮፊሰር አሥራት ያን ወገን ጭፍጨፋ ለማስቆም ባንፈልግም በዘር መደራጀት የግድ መደራጀቱ በዘር አማራጭ የለውም በሚል ።
:— መአድ የሚል ድርጅት መሥርተው መንቀሳቀስ ጀመሩ ።
ይህ የመሰረቱት ድርጅት ከጅምሩም መሀል ሰፋሪ አማረኛ ተናጋሪ ምሁራንም አልተዋጠላቸውም ነበር ።
ሁኖም ግን አብዛኛው ተከታዮቻቸው መስዋዕት ቢሆኑም በምዕራብ ሐረርጌ ነበደኖ በጋራሙለታ በቀብሪ ደሀር በሀረር በድሬዳዋ በጅጅጋ በአርባጉጉ የሚካሄዱትን የዘር ማፅዳት ለጊዜው ጋብ እንዲል አድርገዋል ።
ታላቁ ለወገን ተቆርቋሪው ምሁር በሕውሓት ካድሪ የሀሰት ደብዳቤ ተረቆ የፕሮፊሰሩ ፊርማ ፎርጅድ ተሰርቶ ራሳቸው ከሳሽ ራሳቸው ፈራጅ ሁነው በእድሜ ባለፀጋ ምሁሩ ወደእስር እንዲጣሉ ተደረገ ህክምናም እንዳያገኙ ተደረገ ።
የተወሰኑ ዓመታትን መጥፎ በሆነ እስር ቤት በመጥፎ አያያዝ እንዲቆዩ ተደረገ ሕይወታቸው ልታልፍ አንድ ወርህ ሲቀር ለእርዳታ መለመኛ በእንግሊዝ ሀገር በሚገኙ ባዕዳን አማካኝነት ቢፈቱ በእስር ቤት ቆይታው ከፍተኛ ጉዳት ስለደረሰባቸው ሕይወታቸውን መታደግ አልተቻለም ።
አስታውሳለሁ በአንድ ወቅት ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ለህክምና ተብሎ ተኝተው ነበር ።
በዛን ጊዜ ዶክተሮች ሰውየውን ከአንድ ክፍል ወደሌላ ክፍል ለማዘዋወር እንኳ መለስ ዜናዊ ወይም ሥውሩ መንግሥት መፍቀድ ነበረበት ።
ባያድለን ነው እንጅ እንደፕሮፊሰር አስራት አገሩን ያገለገለ አንድ ምሁር የለም ።
አስራት አውሮፕላን አብራሪ ፓይሌት ፣ዶክተር ፣ ስፔሻል ሰርጀር ፣ ከሀገር መሪ እስከተራው ባላገር በሙያቸው ያገለገሉ ። የጥቁር አንበሳን ሆስፒታልን የመሠረቱ ። በግንባታው ወቅት በኮሚቴ በሀላፊነት የሰሩ ።
በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የሕክምና ፋክልቲ ያቋቋሙ ነበሩ።
ልክ እንደ ቴዎድሮስ ያለዕረፍት ለሀገራቸው የሠሩ ነበሩ ።
እንዲህ ነው ለኢትዮጵያ መሥራት መጨረሻው ይህ ነው ።
“ ሀገሬ ኢትይጵያ ሞኝ ነሽ ተላላ
የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ ፣ ”
አሁን ላይ ሁነን ስናየው ትክል ነበሩ አሁንም አማራ መደራጀት የግድ ነው
አማራ ተደራጀ ማለት ኢትዮጵያዊነቱን ረሳ ማለት አይደለም ።
አንድ ነገር ራሱን ካላጠነከረ ማንም አይጠጋውም ።
አሁን አሁን አማራ ነኝ ማለት አስፈሪና አሳፋሪም እየሆነ ነው ።
እስኪ ራሳችሁ እንደምሳሌ ውሰዱ
በምሥረቅ የሀገሪቱ ክልል ወይም በተለያዩት ክልል ሂዱና አንድ ችግር ቢገጥማችሁ አቤት ብትሉ የሚሰማ አካል አለ?
ስለዚህ አማራ የሚለውን ጎሳ የግድ መቀየር አዋጭነቱ በግልፅ እየታየ ነው ።
እኔ የማውቃቸው አንዳንድ ግለሰቦች አማራ አይደለሁም እያሉን ነው ።
አልተሳሳቱም ካላዋጣ ራሱ በአንድ ሁኖ መብቱን ካ ላስከበረ ለምን ራሴን ለአዳጋ አጋልጣለሁ ።

Shagiz Shagi's photo.