የዘር ማጥፋት ወንጀሎች በአማራ ሕዝብ ላይ በታሪክ ሂደት ውስጥ ከጥንት እስከ ዛሬ!

  • Share
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
amsalugkidan@gmail.com

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

ይሄንን ጽሑፍ ታች አምና ከጉራፈርዳና አካባቢው አማራ በመሆናቸው ምክንያት ብቻ ሕጋዊነታቸውን የሚያረጋግጡ ሰነዶችን ይዘው እያለ ሕጋዊ ሆነው የየክልሉ መንግሥት አውቋቸው በሥርዓቱ ግብር እየከፈሉ እየኖሩ የነበሩ ምስኪን ገበሬዎችን “ሕገ ወጥ ሰፋሪዎች”  በሚል ሕገ ወጥነታቸው አግባብነት ባለው የሕግ አካል (ፍርድቤት) ክስ ተመስርቶባቸው ሳይረጋገጥባቸው በጅምላ በግፍና በሕገ ወጥ መንገድ ንብረታቸውን ሁሉ ተወርሰው እንዲወጡ በተደረገ ጊዜ ጽፌው ለጥቂት መደበኛና ኢመደበኛ (Conventional and Social Media) ልኬው ነበር እስከማውቀው ድረስ ለሕዝብ ይፋ አድርገውት ያስነበቡት ወይም ያስደመጡት አልነበሩምና ሕዝብ ሊያውቃቸው የሚገባ በርካታ ቁምነገሮች ስላሉት እንዳያመልጣቹህ በማሰብ ወደ እናንተ አድርሸዋለሁ መልካም ንባብ፡፡
የዐፄ ዮሐንስ 4ኛ መንግሥታዊ (official) ቋንቋ ማለትም ከውጭ መንግሥታትም ይሁን ከሀገር ውስጥ ነገሥታት መልዕክት ይጻጻፉ የነበረው የቤተ መንግሥት ሥራቸውን ይሠሩ የነበሩት በአማርኛ ነበር፡፡ ዐፄ ዮሐንስ 4ኛ ትግሬ ሆነው ሳለ ይሄንን ማድረጋቸው ቅር ያሰኛቸው የትግሬ ሹማምንት በራስዎ በትግርኛ ቋንቋ የማይጠቀሙት ለምንድን ነው? ብለው ጠየቋቸው ዐፄ ዮሐንስ 4ኛም አማርኛ የአክሱማዊያን ነገሥታት ቋንቋ መሆኑን ለእነሱ በማስታወስ ይህንን መለወጥ እንደማይኖርባቸውና እንደማይገባም በመግለጽ ለሹማምንቶቻቸው ምላሽ ሰጡ፡፡ ይህ አክሱማዊያን አማሮች ነበሩ ወይም አማርኛ የእክሱማዊያን ቋንቋ ነው የሚለውን ታሪክ አክሱም አካባቢ ሄዳችሁ ብትጠይቁ የአክሱም ሰዎች በትውፊት ይዘውት እንደመጡ ማለትም አባቶቻቸው አማርኛ የአክሱም ነገሥታት ቋንቋ መሆኑን ይነግሯቸው እንደነበር ይገልጹላቹሀል፡፡ በላይ ግደይ የተባሉ ጸሐፊም “አክሱም” በተባለው መጽሐፋቸው ይሄንን ገልጸውታል፡፡
ታዲያ ጉዳዩ እንዲህ ከሆነ አማራን ወይም አማርኛን ከአክሱምና አከባቢዋ ማንና እንዴትስ አጠፋው ለሚለው ተገቢ ጥያቄ ታሪክ አጥኝዎችና ተመራማሪዎች እስከአሁን አልደረሱበት ሆኖ ይሁን? ወይም አውቀውት ነገር ግን በአንድም በሌላም ምክንያት መግለጽ ስላልፈለጉ? ለዚህ ጥያቄ አጥጋቢ ምላሽ ሊሰጡ አልቻሉም፡፡ ከዚህ አኳያ ይህ ጽሑፍ እስከ አሁን ያልተገለጸ ከታሪክ ኩነት መዞ ወይም ገልጦ መረጃ ይሰጣል፡፡
ጥንት ቋንቋቸው አማርኛ ኖሮ ዛሬ ላይ ቋንቋቸው ትግርኛ የሆነ አክሱሞች ብቻ አይደሉም፡፡ ከዚያው ከአጠገባቸው የወልቃይትና ከፊል ጠገዴን ሕዝብ ታገኛላቹህ፡፡ የእነኚህን አካባቢ ሰዎችን ማንነታቸውን ብትጠይቋቸው አማራ ጎንደሬ እንደሆኑ ይነግሯችኋል፡፡ የሚናገሩት ቋንቋ ግን ትግርኛ ነው፡፡ አሁን ሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት ሀገራቸውን ከጎንደር ቆርጦ ወደ ትግራይ ሲቀላቅልባቸውም ከመጀመሪያ ጀምሮ እንደተቃወሙ ነው፡፡ በተለያዬ ጊዜ በውጭም በሀገር ውስጥም ያሉ ወልቃይቶች የዚህ መንግሥት አመራርና ነባር ታጋይ የሆኑትም ሳይቀሩ ለመንግሥት ሥራ እውጭ ባሉበት “እኛ ትግርኛ ስለተናገርን ብቻ እንደ ትግሬ ልንቆጠር አይገባም ማንነታችን ይጠና እኛ ትግሬ አይደለንም” በማለት እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በተደጋጋሚ በተቃውሞ ሰልፉ ተቃውሟቸውን አሰምተዋል፡፡
የአክሱም ነገሥታት አማርኛ የቤተመንግሥት የሚስጥር ቋንቋ አድርገው ከመፍጠራቸው በፊት ቋንቋቸው ሙሉ ለሙሉ ግእዝ ነበር፡፡ አማርኛ ሊቀድም እንደሚችልም የሚያመላክቱ አንዳንድ ጠቋሚ ነገሮችም አሉ፡፡ የአክሱም ነገሥታት ስሞቻቸውን ያዬን እንደሆነም በተለያዩ ምክንያቶች በባዕዳን ማለትም በዕብራይስጥ፣ በጽርእ፣ በሮማይስጥ ስሞች ከተጠሩት ውጪ ስሞቹ ግእዝ ካልሆኑ አማርኛ ናቸው፡፡ ምንም እንኳ ብዙዎቹ የጠፉ ወይም የተረሱ የአማርኛ ቅላት ሆነው ለመረዳት የሚያስቸግሩ አማርኛዎች ቢበዙም አሁንም ድረስ በአማርኛ ቋንቋ ውስጥ ባሉ ቃላት የሚጠሩ የአክሱም ነገሥታት ስሞች አሉ፡፡ ለምሳሌ ያህል ጥቂቶቹን ብናነሣ ምኒልክ (ምንይልክ) ቅ.ል.ክ 982-957፣ ዙዋሬንብረት 1ኛ ቅ.ል.ክ. 599-558፣ ዙዋሬንብረት 2ኛ ቅ.ል.ክ. 276-260፣ ግርማአስፈር 77-86 ዓ.ም፣ አርፍድ (ገ/መስቀል) ከ357-361 ዓ.ም፣ ወሰንሰገድ 557-572 ዓ.ም፣ ጉም 693-717 ዓ.ም፣ አስጎምጉም ከ717-722 ዓ.ም፣ ለትም ከ722-738 ዓ.ም፣ ተላተም ከ738-759 ዓ.ም፣ አይዞር ለ6 ሰዓታት፣ ውድማአስፈር ከ787-817 ዓ.ም፣ አንበሳውድም (አንበሳአውድም) ከ882-902 ዓ.ም ድልነአድ 902-912 ዓ.ም፣ የመሳሰሉት ናቸው፡፡
ከላይ እንደገለጽኩት ሕዝቡ በዘር አማራ ሆኖ እንዴት ባለ ሁኔታ ይገዛ ቋንቋቸውን አጥፍተው ወይም ትተው ቋንቋቸው ያልነበረውን ትግርኛን ቋንቋቸው ሊያደርጉ እንደቻሉ እንይ፡፡ ይህ ድርጊት ከመጀመሪያውና ለ40 ዓመታት በተከታታይ ያለ ሟቀረጥ ከተፈጸመው እጅግ ከባዱና አሰቃቂው በአማራ ሕዝብ ላይ ከተፈጸመው የዘር ማጥፋት ወንጀል ጋር በቀጥታ የተገናኘ ነው፡፡ ዘመኑ 842 ዓ.ም 882 ዓ.ም ድረስ በጨካኟና በክፏዋ “እሳቶ ወይም ጉዲት” በመባል በምትታወቀዋ ዮዲት የተፈጸመ ነው፡፡ የዓረብና የምዕራቡ ዓለም ታሪክ ጸሐፍት “ክርስትና የሀገሪቱ ብሔራዊ ሃይማኖት ሆኖ በ አራተኛው መቶ ክ/ዘመን በአብርሃና አጽብሐ ወይም በኢዛናና ሳይዛና ከመታወጁ ጋራ በተያያዘ በመጨረሻ በአማራ አሸናፊነት እስኪጠናቀቅና ተሸናፊዎቹ ፈላሾች በሀገሪቱ አርሶ የመጠቀም መብት ተነፍገው በእጅ ሞያና በጉልበት ሥራዎች የአማሮች አገልጋዮች እንዲሆኑ እስኪፈረድባቸው ጊዜ ድረስ በአማሮችና በፈላሾች (ኢትዮጵያ ውስጥ በነበሩ ቤተ እስራኤሎች) ማለትም አይሁዶች መሀከል እስከ ዮዲት ጊዜ ድረስ ለአምስት መቶ ዓመታት የዘለቀ ጦርነት ተደርጓል” ሲሉ ጽፈዋል፡፡ ልብ አድርጉ “በአማሮችና በፈላሾች” መካከል፡፡
የዮዲት ጉዲት ዘመን ግን ፈላሾች ጦርነቱን አሸንፈው ያሻቸውን ማድረግ የቻሉበት በኢትዮጵያ ታሪክ ሊገለጽ ከሚችለው በላይ ሀገሪቱ ከዚያ ዘመን በፊት የነበራትን ሥልጣኔ የሚያሳዩ ቅርሶችን ከጥቂት ምልክቶች በስተቀር ወድሞ የጠፋበት ዘመን ነበር፡፡ በዚያ ዘመን የክርስትና መታወጅ መጀመሪያ ግጭት ፈጠረ እያደር ግን በሀገሪቱ የአይሁድና የክርስቲያን ቀጠና ለይቶ ሀገሪቱን ለከባድ ኪሣራ ለዳረገና እጅግ ለተራዘመ ጦርነት ምክንያት ሆነ፡፡ ከ500 ዓመታት በኋላም አይሁዶች ወይም ፈላሾች በለስ ቀንቷቸው ጦርነቱን አሸንፈው በገነኑበት በ40 ዓመታት በዮዲት ጉዲት ዘመን ነበር አማሮችን በአክሱምና አካባቢዋ በተቻላትም መጠን በተቀረው የሀገሪቱ ክፍል እንዲጠፉ ያደረገችው፡፡ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ለነገሩ ወደ ታችም ወረድ ይላል አንድ ትውፊታዊ አባባል አለ እሱ ምንድን ነው? በሰሜን ኢትዮጵያ ክፍል “አማራ” ማለት የዘር ስም ብቻ አይደለም የሃይማኖትም ስም ጭምር እንጂ፡፡ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ሰዎች በዘር ትግሬ ወይም ሌላ ቢሆኑም ሃይማኖታቸውን ሲገልጹ ክርስቲያን ነኝ ለማለት “አማራ” ነኝ ይላሉ፡፡ ይህ አንድ ዐቢይ ነገርን ግልጽ አድርጎ ያሳያል፡፡ በዚያ ዘመን ይደረግ የነበረው ጦርነት በማንና በማን መሀከል ይደረግ እንደነበረ፡፡
በመሆኑም ዮዲት ጉዲት ጠላቶቿ አድርጋ የተነሣችባቸውን በዘርና በሃይማኖት “አማሮች” የሆኑትን አክሱማዊያንን ከመላ ሀገሪቱ ያለ ርህራሔ በጨከነና በማይታጠፉ ውሣኔ ጨርሶ የማጥፋት ዘመቻዋን በመላ ዘመኗ (ለ40 ዓመታት) ስትፈጽም በነበረበት ዘመን አማሮች ከዚያ መቅሰፍት ለመዳን ለመትረፍ ወይም ለማምለጥ ከመሰደድ በመለስ የነበራቸው ብቸኛ አማራጭ አማራነታቸውን ማስተባበል ወይም አማራ እንዳልሆኑና ትግሬ እንደሆኑ ለአጥፊዎቻቸው ለዮዲት ጉዲት ሠራዊት መግለጽ ነበር፡፡ ይህ የመከራ ዘመን የአንድ ትውልድን ዘመን (33 ዓመታት) ጨርሶ የቀጣዩን ትውልድ ዘመንም አጋምሶ ስለነበርና ዮዲት ጉዲት ድል ከተመታችም በኋላ ያ መራራ መከራ ደግሞ ተመልሶ ላለመምጣቱ እርግጠኛ ያለመሆን ሥጋት ችግር እንዲህ ነበርን ከሚለው ትውፊታዊ ውርስ በቀር የአክሱምና የአካባቢዋን ሕዝብ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከማንነቱ ማለትም ከአማራነቱና ከቋንቋው አለያይቶት ሊቀር ቻለ፡፡
ከዚያም በኋላ የቤተክርስቲያንና የሀገራችን ታሪክ ጸሐፍት በሰዓቱ ግልጽ ሆኖ የሚታየውና የሚታወቀው ነገር ልክ በእነሱ ዘመን በግልጽ እንደሚታወቀው ሁሉ በኋላ ዘመንም እንደዚያው በግልጽ ታውቆ የሚቀጥልና ዛሬ ያለው ያ ችግር የፈጠራቸው የታሪክ ባለቤት ማንነት ያለመታወቅና ለተሳሳተ ግንዛቤ የሚዳርጉ ክፍተቶች በኋለኛው ዘመን ላይ የታሪክ መሳከር ወይም መጣረስ ሊያስከትል እንደሚችል ባለመገመታቸው ጦርነቱ ሃይማኖታዊ እንደነበረ ዮዲት ጉዲት በቤተክርስቲያን በሕዝቡና በሀገሪቱ ላይ ያወረደችውን መዓትና ጥፋት እንጂ በአማራና በፈላሻ መሀከልም እንደነበረ አጉልተው ወይም ግልጽ ባለ ቋንቋ ሳይገልጹት ቀርተዋል፡፡
እንግዲህ ይህ ታሪክ ማለትም የዮዲት 40 ዓመታት ዘመን፤ አይደለም በሀገራችን በውጭ ጸሐፍት ሳይቀር በሚገባ የሚታወቅ አሳዛኙ የታሪካችን ገጽታ ነው፡፡ በሚገርም ሁኔታ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከያኔያን (አርቲስቶች) ሳይቀሩ ንቁ ተሳታፊ ሆነው እየተንቀሳቀሱበት ያሉበት በመጽሐፍ ቅዱስ እንዳልሞተና በእሳት ሰረገላ እንደተነጠቀ የተገለፀው ነብየ እግዚአብሔር ኤልያስ ሰው እንደመሆኑ በዳግም ምጽአት ዋዜማ ሞትን ለመቅመስ ወደ ኢየሩሳሌም እንደሚመጣ በትርጓሜ መጻሕፍት በግልጽ ተጽፎ እያለ ነብዩ ኤልያስ ኢትዮጵያን ሊታደግ በሁለት አፉ የተሳለ ሰይፍ ይዞ መጥቷል የሚሉ የሐሳዊያን ቡድን ያሰራጨው መረጃ ላይ በኢትዮጵያ ታሪክ የሚታወቁ እውነቶችን በተቃራኒው በመገልበጥ በፈጠራ ታሪክ መጥፎውን መልካም አጥፊውን ገንቢ ኃጥኡን ቅዱስ እንደነበሩ በማበል ፈጽሞ ኃላፊነት በጎደለው መልኩ ታሪክን የማጠፋፋት ዘመቻ ላይ ናቸው፡፡
ለምሳሌ በዚህች ሀገር ላይ ያንን ሁሉ ጥፋት በማድረሷ ታሪክ የሚያውቃትን ዮዲት ጉዲትን ቅድስት እና ሠማዕት ናት እንጂ አጥፊ አይደለችም ይላሉ፡፡ እሷን ብቻም ሳይሆን በዐፄ ዘርዓያዕቆብ ዘመነ መንግሥት በኑፋቄአቸው ወይም በክህደታቸው ምክንያት ንጉሡ የቀጧቸውን ቤተክርስቲያን ያወገዘቻቸውን መናፍቃንን ማለትም ደቂቀ እስጢፋዎችን ከሀዲያን መናፍቃን ሳይሆኑ ቅዱሳን ሠማዕታት ናቸው በማለት በጠራራ ፀሐይ በሀገሪቱና በቤተክርስቲያን ታሪክ ላይ አስገራሚና አስደንጋጭ እጅግ ኃላፊነት የጎደለው የጥፋትና የክህደት ደባውን በመተብተብ ላይ ይገኛሉ፡፡ አንድ የዚህ ቡድን ሌላ ክንፍ ሊሆን እንደሚችል የሚገመት በመንግሥትም ድጋፍ የሚደረግለትና የብዙኃን መገናኛ ሽፋን እየተሰጠው ያለ ሌላ ቡድን የዐፄ ዘርዓያዕቆብንና የደቂቀ እስጢፋን የጥል ጉዳይ ምክንያት ዛሬም ባለው የቤተክርስቲያን ዶግማና ቀኖና ማረጋገጥ የሚቻል ሆኖ እያለ ጎዳዩ ሃይማኖታዊ እንዳልነበረና ፖለቲካዊ እንደነበር ጸቡ የአማራና የትግሬ እንደነበር አድርጐ በሰፊው በመለፈፍ ላይ ይገኛል፡፡ የእነዚህ ሁለት የሐሳዊያን ቡድኖች በአንድ ወቅት አንድ ዓይነት መልዕክትና አቋም ይዘው ብቅ ማለት እንዲሁም በስውር ጥቅሙን ሊያስጠብቁለት የፈለጉት አካል ማንነትና ሌሎች ነገሮች ሲታይ ከእኒህ እንቅስቃሴዎች ጀርባ ይህ የአገዛዝ ሥርዓት መኖሩን ይጠቁማል፡፡
እዚህ ላይ አንድ ገጠመኝን ብናገር ነገሩን የበለጠ ግልጽ ያደርገዋል፡፡ አንድ ድንግላዊ ነኝ የሚል ግን መነኩሴ ያልሆነ በቅቻለሁ በደመና ተጭኘ ኢየሩሳሌምን ጨምሮ የፈለኩበት ሀገር እመላለሳለሁ ከተሠወሩ ቅዱሳን ጋርም እገናኛለሁ ከሚል ሰው ጋር ጓደኞቼ አስተዋወቁኝ ለጊዜው በጓደኞቼ ወሬ ተሞልቼ ስለነበር እውነትም የበቃ ከቅዱሳን አንዱ መስሎኝ ነበር፡፡ ይህ ሰው እንደላይኞቹ ቡድኖች ሁሉ ዮዲት ጉዲትንና ደቂቀ እስጢፋን የሚያወድስ ከመሆኑም በላይ ትንቢት ነው እያለ የሚያወራው የዚህን ሥርዓት ጥቅም ሊያስጠብቅ በሚችል መልኩ ቀምሮና አበጃጅቶ ነው፡፡ እግዚአብሔር ግን እየተሠራ ያለውን ደባ ለመግለጽ ስለወደደ ይህ ሰው ማን እንደሆነ የማውቅበትን ጥሩ አጋጣሚ ፈጠሮ እንዳውቅ አደረገ፡፡ እናም ይህ ሰው ድንግላዊ ሳይሆን የቤተሰብ ኃላፊ መሆኑንና ሥራውም እራሱን እየለዋወጠ በየገዳሙና በየጸበሉ እየዞረ የሚሰልል “የመንግሥት” መረጃ ወይም ሰላይ መሆኑን ደረስኩበት፡፡ እንግዲህ እነኝህ ሰዎች ለምን ዓላማ የቱን ያህል ርቀት እንደሚጓዙ ቁልጭ አድርጎ አሳይቶኛል፡፡
yodit-300x184ወደ ቀደመው ነገራችን ስንመለስ እናም የዮዲት መጨረሻ ሲቃረብ ማለትም ሸዋ መራቤቴ ላይ በተደረገው ጦርነት ዮዲት ጉዲት ከተገደለችና ሠራዊቷም ከተደመሰሰ በኋላ አማሮች ወይም አክሱማዊያን የነበረውን የአክሱም ሥርዎ መንግሥት ለማስቀጠል ሞክረው ነበር ነገር ግን ለ40 ዓመታት ያህል የነበረው መከራ የሥርዎ መንግሥቱን መሠረት እጅግ አናግቶት ስለነበር ለ30 ዓመታት ከቆዩት ሁለት ነገሥታት በኋላ ማስቀጠል ሳይችሉ በዛጉዌ ወይም በአገው ሥርዎ መንግሥት ተገልብጦ የዛጉዌ ሥርዎ መንግሥትም ከ912-1245 ዓ.ም ድረስ ለ333 ዓመታት 11 ነገሥታትን አንግሦ ኢትዮጵያን ሲገዛ ቆይቶ አቡነ ተክለሃይማኖት ሥልጣኑ ለነበረው ለሰሎሞናዊው ሥርዎ መንግሥት መመለስ አለበት በማለታቸው አቡነ ተክለሃይማኖትና የመጨረሻው የዛጉዌ ሥርዎ መንግሥት የመጨረሻው የነበረውን ንጉሥ ይትባረክ ባደረጉት ሰላማዊ ስምምነት ሥልጣኑ ወደ ሰሎሞናዊው ሥርዎ መንግሥት ተመልሶ መቀመጫውን ግን አክሱም ሳይሆን ሸዋ አደረገ፡፡ በእርግጥ የአክሱም ሥርዎ መንግሥት መቀመጫውን ሸዋ ሲያደርግ ይህ የመጀመሪያው አልነበረም ከአብርሃ ወአጽብሐ ከ298 ዓም – አምሲ 461 ዓ.ም ድረስ 28 የአክሱም ነገሥታት ከአክሱም ባሻገር መቀመጫቸውን ሸዋ የረር ላይ ማለትም አዲስ አበባ ምሥራቃዊ ጫፍ ላይ ከሚታየው የረር በመባል በሚታወቀው ከፍታ ቦታ ላይ አድርጎ ቆይቷል፡፡ አሁንም ድረስ የዚያ ታሪክ አሻራዎች በቦታው ይገኛሉ፡፡
ከዚያም ይህ ሥርዎ መንግሥት እስከ ግራኝ መሐመድ በወረራውና በጦርነቱ ከነሕዝቡ ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ ገፍቶ እስከ ሰደዳቸውና ሁለተኛው የዘር ማጥፋት ወንጀል በአማራ ሕዝብ ላይ ለ15 ዓመታት ያህል እስከተከሰተበት ጊዜ ዐፄ ልብነ ድንግል ድረስ ቆየ፡፡ ዐፄ ልብነ ድንግል በጦርነቱ ከመናገሻቸው ሸዋ ከተረፈው ሕዝባቸው ጋር ተፈናቅለውና ተሰደው ሰሜን ኢትዮጵያ ጫፍ ድረስ ተሰደው አንዳሉ በሞት ተለዩ ግራኝ መሐመድ ለ15 ዓመታት ያህል ክርስቲያኑን (አማራውን) ሕዝብ እያሳደደ ፈጀው በሀገሪቱም ላይ ከዮዲት ጉዲት በከፋና ተወዳዳሪ በማይገኝለት ጨርሶ ኢትዮጵያዊ ወገናዊነት ባልተንጸባረቀበት በፍጹም ባዕዳዊ ስሜት ሀገሪቱን ከሥር ነቀላት አደቀቃት የቤተመንግሥትና የቤተክህነትን ሀብቶችና ቅርሶችን ሁሉ ጥርግ አድርጎ ለእርዳታ ላመጣቸው አረቦችና ለቱርኮች ጦር ሰጠ፡፡
ተንቀሳቀሽ ያልሆኑትንም አፈራረሰ ደመሰሰ ሌላው ቀርቶ በሀገሪቱ አንዲት ዛፍ እንኳን ቆሞ እንዳይቀር እስከ ማድረግ የደረሰ በገሪቱን ከሥር የመንቀል የጥፋት ዓላማ አንግቦ አወደመ፡፡ ሕዝቡንም አልሰልምም ያለውን እየሰየፈ ሞትን ፈርተው እሽ ያሉትን እያሰለመ ሲዋጋ የቀረው ሕዝብ ከንጉሡ ጋር ተሰዶ በሰሜን ኢትዮጵያ እየተቅበዘበዘ እንዳለ በጦርነቱ ምክንያት ሕዝቡ ቀየውን ጥሎ በመሰደዱ ባዶና ነጻ ሆኖ ያገኙትን መሬት በ15 ዓመታቱ ውስጥ የኦሮሞ ተወላጆች ድንበር ተሻግረው በቦረና በኩል በመግባት ሰፊ መሬት ለመቆጣጠር ዕድል አገኙ፡፡ ዐፄ ልብነ ድንግል ከሞቱ በኋላ ልጃቸው ዐፄ ገላውዴዎስ በስደት እንዳሉ በ1530 ዓ.ም ነግሠው ከፖርቹጋሎች ባገኙት እርዳታ ታግዘው ግራኝን ጎንደር ፎገራ ላይ ገድለው ድል አደረጉት ግራኝን ከገደሉና ሠራዊቱንም የማረኩትን ማርከው የሸሸውም ከሸሸ በኋላ ወደ አባቶቻቸው መናገሻ ሲመለሱ ከሀገሩ የሚበዛው በእንግዶች ማለትም በኦሮሞ ተወላጆች ተይዞ አገኙት፡፡ ንጉሡም የሕዝባቸውን ማለቅ ተመልክተው በጣም የሳሳውን የሕዝባቸውን ቁጥር ለማካካስ እንደሚረዳቸው በማሰብና ፈቃደ እግዚአብሔር እንደሆነ በመገመት ለእንግዳው ሕዝብ የጎሳ አለቆች ሕዝቡ ሀገሬውን መስሎ ለመንግሥት እየገበረ የሚኖር ከሆነ ሕዝቡ ካለበት ስፍራ መኖሩን እንደሚፈቅዱ አስታወቁ፡፡ የኦሮሞ ሕዝብ አለቆችም ይህንን ችሮታ በደስታ በመቀበል ሀገሬውን መስለው እንደሀገሬው ሕዝብ እየገበሩ ለመኖር ቃል በመግባት የኢትዮጵያዊነት ዜግነታቸውን አገኙ፡፡ ሌላ አዲስ ፈላሲ እንዳይገባ ግን የቦረናን በር ዘጉ፡፡ እንግዲህ ይህ ከሆነ ረጅም ወይም በጣም ሩቅ የማይባል ማለትም አምስት መቶ ዓመታት መሆኑ ነው፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳል በፋሽስት ጣሊያን የ5 ዓመታት የወረራ ጊዜ የፋሽስትን የጥፋት ምክር በመስማት እንዲሁም የ1983ቱን የመንግሥት ለውጥ ተከትሎ የጥፋት መልዕክተኛ በሆኑት ምክርና ግፊት በሚያሳዝን ሁኔታ የኦሮሞ ተወላጆች ከዐፄ ገላውዴዎስ ጋር አድርገውት የነበረውን ስምምነት አደጋ ላይ በሚጥል ሁኔታ በሀገሪቱ የተለያዩ ስፍራዎች እውነቱን እያወቁ ሳያውቁም ሊሆን ይችላል እራሳቸውን እንደባለቤት በመቁጠር ጭራሽ አማራውን ሀገራችንን ለቃቹህ ውጡልን በማለት ከዚያም አልፈው የብዙ ንጹሐን ዜጎችን ደም በጭካኔ አፈሰሱ መጠኑ ከፍተኛ ነው ባይባልም ይህ በአማራ ሕዝብ ላይ የተደረገው አራተኛው የዘር ማጥፋት ወንጀል ነበር፡፡ ሦስተኛው የዘር ማጥፋት ሊባል የሚችለው ኦሮሞዎቹ ሸዋ ላይ የነበረውን ሰሎሞናዊ ሥርዎ መንግሥት መቀመጫውን ጎንደር እንዲያደርግ እስከ መገደድ ድረስ የደረሰ አብያተ ክርስቲያናትንና ገዳማትን ማውደምን የጨመረ ጥቃት በተለያየ ጊዜ በፈጸሙ ጊዜ ያደረሱት ጥፋት ነው፡፡
ዛሬ ደግሞ ነገሩ ከዚያም አልፎ የኦሮሞን ሕዝብ ስም ያለ ፍላጎቱ መጠቀሚያ ያደረጉ  እንገነጥላለን የሚሉ የጥፋት ኃይሎች ተፈጥረው ቁጭ አሉ፡፡ ኧረ ተዉ ሕሊና ይኑረን እንጂ ምነው? የማንን ሀገር ነው የምትገነጥሉት? ለነገሩ በአሁኑ ሰዓት ሁሉም ብሔረሰቦች አንዱ ከሌላው ጋር ተቀላቅሉ ተዋልደው ተዋሕደው ወቶላቸዋልና አማራ፣ ኦሮሞ፣ ትግሬ፣ ጉራጌ ወዘተ. የሚባል ሕዝብ ባይኖርም ቅሉ አሁን ትላንትና በእንግድነት ተገብቶ ዝም ተብሎ የሰው ሀገር መገንጠል አለ እንዴ? ለዚያ ውለታ ልትከፍሉት የሚገባው ብድራትስ ይሄ መሆን ነበረበት እንዴ? ሁላችንም ዘራችንን ወደ ኋላ ብንቆጥር አንድና ከአንድ በላይ የሌላ ዘር ደም ተቀላቅሎበት እናገኛለን መረጃውን ለማግኘት ውስንነት ወይም የአቅም ችግር ካላጋጠመን በስተቀር፡፡ በመሆኑም የዘር ፖለቲካ ኢትዮጵያ ውስጥ ጨርሶ ሊሠራ አይችልም ለመሥራት ከተሞከረም በእውነት ላይ ያልተመሠረተና ድንቁርና የተሞላ አስተሳሰብ ነው፡፡ ስላለውና ስለምናየው ሳይሆን ስለሌለውና ስለማናየው እናወራለን እንደክማለንና ጅሎችም ነን፡፡ ይሄንን ማለት ግን የአማራ የትግሬ የጉራጌ የኦሮሞ የመሳሳሉት ባሕል ቋንቋና ሌሎችም መገለጫዎች የሉም ማለት አይደለም፡፡ እነሱም ቢሆኑ ግን አንደኛው ከሌላኛው ጋር አልተወራረሰም አልተቀላቀለም ማለት ፈጽሞ አይቻልም፡፡
ወደ ቀደመው ነገራችን እንመለስና አፄ ገላውዴዎስ ሸዋ ሆነው ከገዙ በኋላ ከሳቸው በኋላ ከነገሡት ከዐፄ ሚናስ በኋላ ያሉት የዚህ ሥርዎ መንግሥት ነገሥታት መቀመጫቸውን ወደ ጎንደር በማዞር በመጨረሻ በዳግማዊ ምኒልክ ወደ ሸዋ ከመመለሱ በፊት በላስቴው ዐፄ ተክለጊዮርጊስ 1860 ዓ.ም-1863 ለሦስት ዓመታት መቀመጫቸውን ጎንደርና ላስታ በማድረግ ቀጥለውም የትግሬው ዐፄ ዮሐንስ 4ኛ ከ1863 ዓ.ም-1881 ዓ.ም መቀመጫቸውን መቀሌና ጎንደር በማድረግ ጣልቃ ከመግባታቸው ውጭ ሰሎሞናዊው ሥርዎ መንግሥት እስከ 19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ድረስ መቀመጫውን ጎንደር አድርጎ ቆይቶ ነበር፡፡
እንግዲህ ይሄንን ታሪክ ማለትም በአክሱማዊያን (አማሮች) ዙሪያ ያለውን እውነት የሕወሀት ባለሥልጣናት በሚገባ የሚያውቁት ጉዳይ ነው፡፡ በሁለት መንገዶች 1ኛ እንደማንኛውም የትግራይ ሕዝብ ተወላጅ በትውፊታዊ መረጃ 2ኛ ትግል ላይ በነበሩበት ወቅት በአንድ 100 ዓመታትን በራቁ የትግራይ ተወላጅ ሽማግሌ አባት ይሰጣቸው በነበረ ምክርና ትምህርት፡፡ እኒህ አረጋዊ ሰው የኢሕአዴግን ምልክት ንብ እንዲሆን ያስቻሉም ሰው ናቸው፡፡ እኒህ ሰው ሕወሀቶችን እናንተ የዐፄ ዮሐንስ 4ኛ የካሳ ምርጫ ልጆች ናቹህ እያሉ ይነግሯቸው እንደነበር የሕወሐት አመራሮች ይናገራሉ፡፡ ነገር ግን ምንም እንኳ ይህንን እውነት የሚያውቁ ቢሆንም በዮዲት ጊዜ በተፈጠረው ችግር ምክንያት አሁን ባለው የሕዝብ አሰፋፈር አማሮች ወይም አማርኛ ተናጋሪ አክሱም አካባቢ አለመኖራቸውና አካባቢው በትግርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች መያዙ ቢያንስ ምንም የታሪክ ዕውቀት በሌላቸው ዜጎች ዘንድ አክሱም የትግሬ ተወላጆች እንደነበረ ተደርጎ እንዲታሰብ በፈጠረላቸው ምቹ ሁኔታ በሰው ወርቅ ለመድመቅ ሲሞክሩና ሲቋምጡ ይታያሉ፡፡
ይሁንና ሥነ ልቡናቸውና ሰብእናቸው ማለትም ሕወሐቶች ለታሪክ ለድንበር ለቅርስ ለመሳሰሉት ሀብቶቻችንና እሴቶቻችን ያላቸው አመለካከት ሲታይ ግን ከአክሱም ሥርዎ መንግሥት ጋር ግንኙነት እንዳልነበራቸው ሲያሳብቅባቸው ወይም ሲያሳጣቸው ይታያል ምክንያቱም ሕወሀቶች ለእነዚህ እሴቶቻችን ባጠቃላይ ለሀገሪቱ ታሪክና እሴቶች ያላቸው ግልጽ የሆነ ጥላቻና ዴንታቢስነት ወይም ለእነዚህ እሴቶቻችን ያላቸው ፍቅርና አቅርቦት ደካማ ወይም የምናውቀውን ያህል ነውና፡፡ ይህ ማለት ግን የትግራይ ሕዝብ በሙሉ ለታሪካችን ለነጻነታችን ለሉዓላዊነታችን ለድንበራችን ለቅርሶቻችን ወዘተ. ዴንታ ቢስና ግድየለሽ ነው ማለት አይደለም፡፡ በአንፃሩ ደግሞ የአማራን የባለአደራነት ስሜት ማለትም ለታሪክ ለቅርስ ለድንበር በአጠቃላይ ለሀገር ያለውን ተቆርቋሪነት ያየን እንደሆነ የሚመሰገንና አርዓያነትም ያለው ነው፡፡ እንግዲህ ይሄ ከየትም የሚመጣ ሳይሆን እንደ ንብረት ሁሉ ከቀደሙት ትውልዶች የሚወረስ የባለ አደራነት የባለቤትነት ስሜት መንፈሳዊ ውርስ ሀብት ወይም እርሾ በመኖሩ ነው፡፡ ይሄንንም ስል የተቀረው የኢትዮጵያ ሕዝብ የሀገር ፍቅር ስሜት የለውም እያልኩ አለመሆኔ ይታወቅ፡፡ ትንታኔዬ ያተኮረው ከላይ በተገለጸው አካባቢና ርዕሰ ጉዳይ ብቻ በመሆኑ ነው፡፡
የ1983 ዓ.ም የመንግሥት ለውጥ ተከትሎ በአማራ ሕዝብ ላይ በግልጽና በስውር በእቅድና በተጠና መልኩ የዘር ማጥፋት ወንጀሎች በመፈጸም ላይ ይገኛል፡፡ ዛሬም እንደ ዮዲት ዘመን ለመኖርና ለመብላት በሚል ማንነቱን ማለትም አማራነቱን የካደውና የደበቀው ለአማራነቱ ግድ የለሽ የሆነው ጭራሽም እንዴት እንደሆነ ባልታወቀ ሁኔታ ቅንጣት ቁጭትና ጸጸት ሳይታይባቸው ከግፈኞች ጋር ተባባሪ በመሆን በገዛ ማንነታቸው ላይ የዘመቱ ሰዎች ቁጥር የትየሌሌ ነው፡፡ የዚህ የዘር ማጥፋት ወንጀል መገለጫ ዘርፈ ብዙና የተወሳሰበም ነው፡፡ በገሀድ ከተፈጸሙት የዘር ማጥፋት ወንጀሎች በቅርብ ትውስ የሚሉትን ስናነሣ በእነ ታምራት ላይኔ ዓይነቱ በሕወሃት መራሹ “መንግሥት” ባለሥልጣናት ገፋሪነት ሥልጣን በያዙ ማግሥት በአቦምሳ ወይም በአርባጉጉ በሌሎችም ሥፍራዎች በአማራነታቸው ብቻ ከሕፃን እስከ አረጋዊያን በጭካኔ የተገደሉና በተለያዬ ጊዜም ከበደኖ ከጉራፈርዳ አሁን በቅርቡ ደግሞ ከቤንሻንጉል ጉምዝ ንብረታቸውን ወርሰው ማባረራቸው የገዛ ሕገመንግሥታቸው ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በየትኛውም የሀገሪቱ ስፍራ ሠርቶ የማደር ኑሮውን የመመሥረት ሕገመንግሥታዊ መብት አለው እያለ በአንድ ሕዝብ ላይ ያነጣጠረ ጅምላ ማፈናቀል በተለያየ ጊዜ በተለያዩ ቦታዎች ተፈጸመ፡፡ አቶ መለስ ዜናዊ ሲጠየቁ ምን ብለው መለሱ ይህ የክልሉ መንግሥት ጉዳይ ነው ሕገወጥ ሰፋሪዎች ናቸው ካለና አልፈልጋቸውም ካለ መብቱ ነው ይችላል በማለት የገዛ ሕገመንግሥታቸውን የሚፃረር ምላሽ ሰጡ፡፡ ይህ መልሳቸውም ይህ ጉዳይ የተፈፀመው በእሳቸው ትዕዛዝ መሆኑን ጠቆመ ለነገሩ በ21 ዓመታቱ የወያኔ መንግሥት አስተዳደር ተሞክሮ እንደምንረዳው እንዲህ ዓይነቱ ከባድና አሳሳቢ ውሣኔ በክልል አስተዳደሮች ደረጃ ሊወሰን እንደማይችል መረዳት አያዳግትም፡፡ አቶ መለስ እንዲህ ብለው ሲሉ እናንተም በጊዜአቹህ እኛ እንዳደረግነው ሁሉ ትግሬን ባዶ እጁን አራግፋቹህ አፈናቅላቹህ ማባረር ትችላላቹህ ማለታቸውና ይህንን አዲስ አዙሪት ባርከው መጀመራቸው እንደሆነ አቶ መለስ ጨርሶ አልገባቸውም፡፡
“አየ ጭንቅላት አየ የኛ አርቆ አሳቢ” የብልህነትንና የአርቆ አሳቢነትን ትርጉም ለማያውቁ ሰዎች አርቆ አሳቢ መሪ ማለት ውሎ አድሮ ምን ሊያስከትል እንደሚችል መገመት ተስኖት በሰላምና በፍቅር የሚኖርን ሕዝብ እንዲናቆር ማሴር እንዲፋጅ እንዲባላ መሸረብና መጣር ቀን እንዲጠባበቅ ማድረግ ሳይሆን እንኳን ያላጣውን ሰላም ፍቅር አንድነት ሕብረት ያጣ ሕዝብ እንኳን ቢሆን ኖሮ እንዲህ የሆነውን ሕዝብ ማስማማት ማግባባት ማፋቀር ማዋደድ መቻል ነው ብልህና ባለአእምሮ መሪ ማለት እንጅ የሚያናቁረውና ለማፋጀት የሚጥረው አይደለም ያ ደደብ ደንቆሮ እንጂ ብልህና አሳቢ ሊባል ከቶ እንዴት ይቻላል? የኢትዮጵያ ሕዝብ አላውቃቸው ብሎና ተስፋ አልቆርጥ ብሎ ነው እንጂ ከእነዚህ መንግሥታዊ ዳሲኘሊን (ሥነ ሥርዓት) ከማያውቁ፣ ኃላፊነትና ተጠያቂነት የሚባል ነገር ጨርሶ ከማይገባቸው፣ የጫካ አውሬዎች የመንደር ወጠጤዎች የስርቻ ወሮበሎች የቆሻሻ ሥነ ምግባር መፍለቂያዎች ከሆኑ ከእነዚህ ጉዶች ከዚህ የተለየ ምን ይጠበቅ ኖሯል፡፡ እድሜ ዘመናቸውን ሳይለወጡና ሳይሰለጥኑ ጭራሽ እየባሰባቸውና እየደነቆሩ ሄደው ቁጭ አሉ፡፡ ይለወጣሉ ብላቹህም ከቶም ተስፋ አታድርጉ፡፡
ወደ ሌሎቹ አማራን የማጥፋት ወንጀሎች ዓይነቶች ስናልፍ በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል የአማራ ተወላጅ በስውር ደባ ሠርቶ የመኖር ዕድል መነፈጉ፣ በአንድ ወቅት ላይ በተለይ ጎጃም የወባ ወረርሽኝ ገብቶ ሕዝቡን ሲጨርስ የአገዛዙ አካላት ተነግሯቸውና እያወቁ ፓርላማ ውስጥ መነጋገሪያ እስከመሆን ሲደርስ መንግስታዊ ያልሆኑ የውጭ ደርጅቶች እስኪታዘቡ ድረስ አገዛዙ አይቶ እንዳላየ ሰምቶ እንዳልሰማ ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎ ምንም ዓይነት የህክምና አቅርቦት እንዳይሰጥ በማድረግ ሕዝቡ እንዲያልቅ መደረጉ፣ ከዓመታት በፊት የጎንደር ፖሊስ በወገናዊነት ቁጭት በመነሣሣት ጫትን በቸልተኝነት ዝም ብለን በመመልከታችን ትውልዱ እንዳለ የጫት ሱሰኛ እስከመሆን ደረሰ አሁን ደግሞ ይሄ ሺሻ የሚባለውን ዝም ብንል ነገ እንደጫቱ ልንቀለብሰው ከማንችልበት ደረጃ መድረሳችንም አይደለ? በማለት ተነሣስተው ከየጫት ቤቱ ሲሰበስቡ ወዲያውኑ ከክልል ተደውሎ ማን አዛዛቹህ አሁኑኑ በአስቸኳይ መልሱ ተብለው እንዲመልሱና ትውልዱ ሱሰኛና እንኩቶ ብላሽ እንዲሆን ጥረት መደረጉ፣ በሀገሪቱ ሁለት ዓይነት የትምህርት ሥርዓት በመቅረጽ በትግራይና በተቀረው የሀገሪቱ ክፍል ያለውን በመለያየት በተለይ ደግሞ የአማራውን ክልል የትምህርት ጥራት ደረጃ አሳዛኝ በሆነ መልኩ እንዲወድቅ መደረጉ የመሳሰሉት ሲሆኑ በስውር ከሚፈጸመው የዘር ማጥፋት ወንጀሎች ደግሞ ሁለቱን ብቻ ልጥቀስ፡-
አንደኛው በአማራ ክፍላተ ሀገራት ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ምክንያታቸው ያልታወቁና ያልተገለፁ በየጊዜው የሚከናወኑ የጅምላ ክትባቶች አሉ፡፡ እነኝህ ክትባቶች የተከተቡትን ሰዎች መውለድ እንዳይችሉ የሚያደርጉ ክትባቶች ናቸው፡፡ ይህ ክትባት በተደጋጋሚ ሲፈጸም የተለያዩ ምክንያቶችን እየፈጠሩ በክትባቱ ወቅት በመቅረት ሳይከተቡ የሚቀሩ ወገኖች እንዳሉ ታወቀ፡፡ የስውር ደባ ሰለባ እየሆኑ እንደሆነ የገባቸው ተማሪዎች የተለያዩ ምክንያቶችን እየፈጠሩ ላለመከተብ የሚያደርጉት ጥረት የአሳዛኙ ቲያትር አስቂኝ ገጽታ ሆኖ ታይቷል፡፡ ወደ ኋላም ሕዝቡ ይሄንን ጉዳይ ጭራሽ የወጉ ማጣፈጫና ማምረራያ አድረጎት አረፈ፡፡ ሽለ ሙቅ የሆነች ሴት ስትታይ “አሀ ይች ከክትባት ያመለጠች ናት” ያባላል ስሜተ ቀዝቃዛዋን ደግሞ፣ “ይች ተከታቢ ናት” እያለ እስኪቀልድበት ድረስ ይህ ጉዳይ የሕልውናውን ጉልህ ሥፍራ እንደያዘና ማወቁን ወይም መንቃቱን ጠቆመ፡፡ ከዚህ የተለየ ግን ምንም ያደረገው ነገር የለም፡፡ በሌሎች ሀገሮች ቢሆን ግን ከዚህ የበለጠ የሕዝብ አመጽ ሊቀሰቅስ የሚችል ምክንያት ባልነበረ፡፡
ሁለተኛው ደግሞ በተለይ 1996/97 ዓ.ም. ፀረ ትራኮማ ክትባት በሚል ሽፋን በበርካታ አካባቢዎች በተለያዬ ጊዜ የተደረጉ ክትባቶች ብዙ ሕፃናትንና ነፈሰጡር እናቶችን ለሞት አብቅተዋል፡፡ በነዚህ የአማራ አካባቢዎች የቀብር ስፍራዎች ብትዘዋወሩ ከቀድሞው በተለየና ባልተለመደ መልኩ በርካታ የሕፃናትና የነፍሰጡር እናቶች መቃብሮችን ታያላችሁ፡፡ እንግዲህ እነኝህና ሌሎች እነኝህን የመሳሰሉ ስውርና ድብቅ የዘር ማጥፋት ወንጀሎች በአማራ ሕዝብ ላይ ሲፈጸም ቆይቷል፡፡ በግልጽ በአደባባይ በዓለም አቀፉ በሕብረተሰብ እይታ ስር በዘራቸው ምክንያት ብቻ የዜጐችን ንብረት ዘርፎ የሚያፈናቅል የሚያባርር የእርዳታ እህል የሚከለክልና በረሃብ የሚያሰቃይ ሌላም በግልጽ የሚታዩ ግፎችን የሚፈጽም ግፈኛ አገዛዝ በስውር ወይም በድብቅ እነኚህን የጠቀስኳቸውንና ሌሎችንም አያደርግም ብሎ የሚጠራጠር ሰው ወይም ዜጋ ካለ እጅግ የዋህና ያልበሰለ መሆኑን ዛሬ ይወቅ፡፡
ወያኔ ቢወድቅ ወይም ከሥልጣን ቢወገድ የሚከተለውን አጸፋ ጠንቅቆ ስለሚያውቅ በተቻለው መጠን በሥልጣን እያለ ይህንን የበቀል እርምጃ ይወስድብኛል ብሎ የሚፈራውን ሕዝብ (አማራን) በግልጽም ይሁን በስውር በሚያደርጋቸው የማጥፊያ ዘዴዎች ለቅሞ ማጥፋት ዋነኛውና ሌት ተቀን የሚሠራበት ዓላማው ነው የሚል ከባድ ሥጋት አለብኝ፡፡ እስከ 1999 ዓ.ም በተሠራው ደባ ያገኙት ድምር ውጤት ከ6 ዓመታት በፊት በ1999 ዓ.ም በተደረገው የሕዝብ ቆጠራ በሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ባልታየና እንግዳ በሆነ መልኩ የሌላው ሕዝብ በቅድሚያ ትንበያው መሠረት እና ከዚያም በላይ ሆኖ ሲገኝ የአማራ ሕዝብ ግን ይደርሳል ተብሎ ከተጠበቀው የትንበያ ቁጥር ወይም መድረስ ከነበረበት ቁጥር አለመድረሱ ብቻ ሳይሆን ጭራሽም በሚሊዮኖች (አእላፋት) አሽቆልቁሎ እንደተገኘ ማስታወስ ይቻላል፡፡ ገና ከ4 ዓመታት በኋላ በሚደረገው ቆጠራም ከ1999 ዓ.ም በኋላ በሠሩት ደባ ከዚህም በከፋ ሊያሽቆለቁል እንደሚችል ይገመታል፡፡
በየሙያ መስኩ ሰዎች ስንት ጉድ ያውቃሉ መሰላችሁ ለመናገርና ለመመስከር ጊዜን የሚጠብቁ፡፡ የሚገርመኝና ግራ የሚገባኝ ነገር ቢኖር በዚህ ሕዝብ ላይ እንዲህ ጥርስ የተነከሰውና የተጨከነው ለምንድን ነው? ከሌሎች ብሔረሰቦች ጋር በመሆን የዚህችን ሀገር ነጻነት አስጠብቆ ባቆዬ? ከቀደምት ሥልጡንና ኃያላን ሀገራት ጎራ ባሰለፈ? ለእነኝህና ለሌሎች ኩራቶቻችን ሲል ስንትና ስንት መከራ ባሳለፈ? ለምን? ይህ ያስመሰግነዋል እንጂ በምን ተአምር ነው ለጥፋት ድግስ ሊዳርገው የሚገባው? በኢትዮጵያዊነቱና በሀገሩ ኩራትና ክብር የሚሰማው ባለውለታና የሚያስብ ሕሊና ያለው ኢትዮጵያዊ ዜጋ ሁሉ ይህንን የዘር ማጥፋት ወንጀል በዝምታና በይሁንታ የሚመለከትበት አቅል ይኖራል ብሎ ማሰብ ይቻል ይሆን? አረማዊያን ሆይ በምሳሩ ላይ ቆማቹሀል ለራሳችሁም ይብስባቹሀል፡፡ አየ የኛ ልማታዊ መንግሥት ለማያውቅሽ ታጠኝ አያ፡፡ አንባቢያን ሆይ ደኅና ሁኑ ከዚህ በኋላ እንኳን የምንገናኝ አይመስለኝም፡፡ (በመግቢያው ላይ ያለው ፎቶ ለማሳያነት የቀረበ)
ኢትዮጵያ ከውድ ልጆቿ ጋ