እየሩሳለም ተስፋው ችግር ውስጥ ነች
ማእከላዊ እስር ቤት የምትገኘው እየሩሳለም
ተስፋው ችግር ውስጥ ነች፡፡ ከእየሩስ ተስፋው ጋር
የታሰሩ ብርሃኑ ተክለያሬድና ፍቅረ ማሪያም
አስማማው በቅርቡ በቤተሰብ እንዲጠየቁ
ቢደረግም እየሩሳሌም ተስፋውን ቤተሰቦቿ
እንዳይጠይቋት ተደርጓል፡፡ ከዚህ ባሻገር ስለ
እየሩስ ተስፋው መረጃ ማግኘት ያልተቻለ ሲሆን
ይህም ችግር ላይ እንዳለች የሚጠቁም ነው፡፡
ማዕከላዊ ውስጥ የታሰሩ ዜጎች እንዳይጠየቁና
እንዳይታዩ የሚደረገው ድብደባና ሌሎች ኢ-
ሰብአዊ ድርጊቶች ሲፈጸሙባቸው እንደሆነ ግልጽ
ነው፡፡ በተለይ ሌሎች ማዕከላዊ የሚገኙ
እስረኞችም ስለ እየሩሳሌም ተስፋው ምንም
አይነት መረጃ የሌላቸው መሆኑ ጉዳዩን አሳሳቢ
ያደርገዋል፡፡
እየሩሌም ተስፋው ባለፈው ችሎት በቀረበችበት
ወቅት ጥቁር መሃረብ ለብሳ የተገኘች ሲሆን
ይህም በማዕከላዊ እየደረሰባት የሚገኘውን በደል
ለመግለጽ እንደሆነ መገመት ይቻላል፡፡ ማዕከላዊ
እስር ቤት የሚገኙ ታሳሪዎችን በሌሎች ታሳዎችና
ሌሎች ሰዎች በማጠያየቅ መረጃ ማግኘት
የሚቻልባቸው አጋጣሚዎች ቢኖሩም ስለ እየሩስ
ተስፋው በእነዚህ ሁሉ አካላት በኩል መረጃ
አለመገኘቱ ከፍተኛ ችግርና አደጋ ውስጥ
እንደሆነች ትልቅ አመላካች ነው፡፡

A user's photo.