አንተ ቻይ አንተ ታጋሽ
አንተ የቆሎ ተማሪ
አንተ የቅኔ ቀማሪ
አንተ የእግዚአብሔር አገልጋይ
አንተ የኑሮ ተበዳይ
አንተ የቃል ኪዳን ቀለበት
ያረፈብህ የእግዚአብሔር ጣት
ስለ እመብርሃን ብለህ
ለእፍኝ ቆሎ አንገት ደፍተህ
ዓይንህን ወደ ሰማይ
ልብህን ወደ አዶናይ
ልከህ መዝሙረ ዳዊትን ስታዜም
ከሀጢአት ሰውረኝ ኤሎኪም
ኤሎኪም ሰውረኝ
ለልቤ ቅንነት ሙላልኝ
ከይቅርታህ መርቅልኝ
ጥበብንም አስተምረኝ
እያልክ ፀሎትህ የሰመረ
ሰምና ወርቅህ የዳበረ
የፍቅር እስከ መቃብር ቤተኛ
የኢትዮጵያ ታሪክ መገኛ
አንተ የቆሎ ተማሪ
አንተ የእመብርሃን ስም ጠሪ
ሁሉ እየመጣ ሲሄድ
አንተ ብቻ ኗሪ ፣ አንተ ብቻ ቀሪ ።

የቆሎ ተማሪ1014069_391260577652073_1022322647_n