ስለ አክሱም ታሪክ ምን ተባለ???
===================

ፕሮፌሰር መስፍን በሸገር ሬዲዮ ላይ ከተናገሩት:- ¨እንደሚታወቀው ከነገደ ዩቁጣን የሚመዘዘው ሀበሻ የሚባለው ህዝብ የሰለሞኒክ ስረው መንግሰትን አክሱም ላይ ለብዙ ግዜ መስርቶ መኖሩ ግልጽ ነው:: እክሱምም ለብዙ ግዜ ገናና ህዝብ ሆኖ ቆይቶል:: በዚህ ግዜ ሚስጥራዊ የቤተመንግስት መግባቢያ አማረኛን ፈጥረው እራሳቸውን ከጠላት ሲከላከሉ ነበር:: ነገር ግን በግዜ ሄደት የአክሱም ነገስታቶች በተለያየ ምክንያት እየተዳከሙ ሲመጡ በአካባቢው ይኖሩ የነበሩትን የአገው እና አጋሜ ትግረ ህዝብ ባርነት መረረን በሚል ተባብረው የአክሱምን ነገስታቶች ወጉ:: ከጦርነቱ የተረፉት በቁጥር 150 የሚሆኑ ንጉሳዊ ቤተሰቦች ወደ ደቡባዊ አክሱም ወደ ወሎ እና ጎንደር እፈገፈጉ:: በዛን ግዜ በበጌምድር ጎጃምና ወሎ የሚኖረው ህዝብ የተለያየ አይነት ቆንቆ የሚናገር ማሀበረሰብ ነበር:: ሆኖም ግን እነዚህ ንጉሳዊ ቤተሰቦች ካለቸው የአስተዳደር እና ወታደራዊ ብቃት በአጭር ግዜ ውስጥ ጎንደርን ጎጃመን ወሎን ሸዋን ተቆጣጠሩ:: በዚህ መልኩ እረሳቸውን ካጠነከሩ በሆላ የድሮ ጠላታቸው የነበረውን የአገው ስረው መንግስትን ተበቀሉት:: ካሸነፉም በሆላ የአያቶቻቸውን እርስት አክሱምን ከብዙ ግዜ በሆላ ተቆጣጠሩ:: በዚህ ስአት ንጉሳዊ ቤተሰቦች በሁለት አወዛጋቢ ሁናቴዎች ተውጠው ነበር:: ተመለሶ ወደ አክሱም መሄድና አክሱምን መናገሻ ከተማ ማደረግ ወይም ደግሞ ቅባአተ ንግስናቸውን አክሱም በማደረግ የግዛታቸውን ከተማ ጎንደር እንዲሆን መወሰን:: ብዙ ካሰቡ በሆላ የመረጡት ሁለተኛውን አማራጭ ነው ምክንያቱም አሁን ከያዙት ቦታ አክሱም በጣም ስለሚርቅ አማካኝ ቦታ መሆን አልቻለም ነበር:: በዚህ መሰረት ለብዙ ዘመናት የሰለሞን ነገስታቶች የሚቀቡት አክሱም በመሄድ ነበር ምክንያቱም የአያቶቻቸውን እርስት መተው አለፈለጉምና :: እንግዲህ አማራ የተባለውን ህዝብ የፈጠሩት እነዛ 150 የሚሆኑ ንጉሳዊ ቤተሰቦች ናቸው:: በነገራችን ላይ መለስ ዜናዊ አክሱም የትግሬዎች እንደሆነ ሲናገር ሰምቻለሁ:: እውነታው ግን ከዚህ በተቃራኒ ነው አክሱምን የሰሩት ሰለሞናዊ ነግስታቶች ሲሆኑ ከትግሬዎች በብዙ መልኩ ይለያሉ:: ለዚህ ማስረጃ ደግሞ በአክሱም ሀውልቶች ላይ ካሉ ጽሁፎች እንድም የትግረኛ ቃል አታገኙም :: ይልቁንስ አማረኛ ነፍ ቃላቶች አሉ :: በመሆኑም አክሱምንና የትግሬን ወይንም የአጋመን ህዝብ የሚያገናቸው አንድም ታሪካዊ ክስተት የለም አሁን ከቦታው ከመገኘታቸው ውጭ:: ሌላው ነገር በዘመናዊት ኢትዮፒያ ግንባታ አሁን አማራ ተብሎ የሚጠራው ብሄር ጉልህ ሚና ተጫወቶል:: ስለዚህ ኢትዮፒያ ተብላ የምትጠራው አገር አብዛኛው ብሃሪዋ ከዚሁ ብሄር የተቀዳ በመሆኑ ይህ ብሄር አማራ ነኝ ከሚል ኢትዮፒያዊነቱን ቢያስቀድም አይፈረድበትም::¨ September 18, 2014