:— ሌሎች የኦሮሞ ተወላጆች በሀገር ቤት መብት በመጠየቃቸው ብቻ በአደባባይ እየተገደሉ ብዙ የኦሮሞ ወጣቶች በስደት እንኳ መኖር እንዳይችሉ ኬንያ ድረስ በመሄድ ታፍነው እየተወሰዱና እየተገደሉ ።
:— እንጅነር ተስፋሁን ጨመዳ ከኬንያ ተጠልፎ በዝዋይ እስር ቤት እንደሞተ ይታወቃል
:— አቶ በቀለ ገርባ ገዥውን ሥርዓት በአደባባይ ስለነቀፉ ከአራት ዓመት በላይ በአሰቃቂው እስር ሲማቅቁ መቆየታቸው እየታወቀ የአቶ ሌንጮ ለታ ከሕውሓት ምን ለመቀበል ነው ከኋላ በር ዘው በማለት የገቡት ።
:— በርግጥ አቶ ሌንጮ ብዞ የኦሮሞን ወጣቶች አጋፍጠው መሄዳቸው ይታወቃል አሁንም በበረሃ ውላቸውን እንደተለመደው የፀረ— አማራ ሴራ ለማስጠበቅ ይሆን? በርግጥ ፀረ አማራነት ለሕውሓት ታማኝ ለመሆን ያስችላል ግን አቶ ሌንጮ መቸም ሕውሓቶች ጫና ሲበዛባቸው የኔን ድጋፍ ያሻቸዋል በሚል ከሆነ ተሳስተዋል ያ ቀድሞ ቀረ አሁን ሕውሓቶች ብዙ ታማኝ ቅልብ አገልጋይ አላጡም እንደነ ኃይለማርያም ደሳለኝ ፣እንደነ አባ ዱላ ገመዳ ፣እንደነ አለምነው መኮነን ወዘተ
:——የቀድሞው የኦነግ መሥራች የነበሩት አቶ ሌንጮ ለታ በቅርቡ ወደሀገር ቤት ገብተው እንደወጡ ሰማን ።
ከሀገር ገብተው የወጡበትን ምክንያትም ለመገናኛ ብዙኃን የገለፁትን አዳመጥኩ ።
አቶ ሌንጮ በሕውሓት ላይ የሆነ ተስፋ አላቸው እሱም ቀደም ሕውሓት በረሃ በነበረበት ወቅት የጋራ ስትራቴጂ ነበራቸው ያንም ይፈፅሙት ነበር ከደርግ ውድቀት በኋላም በጋራ ሽግግር መንግሥት በሚል ተደራጅተው በብዙ ወገኖች ላይ ድብቅ ጄኖሳይድ ፈፅመዋል ።
አቶ ሌንጮ ይመሩት በነበረበት ወቅት ኦነግ በአማራዎች ላይ የጅምላ ጭፍጨፋ ማድረጉን አናስታውሳለን በ1981 በአሶሳ ትምሕርት ቤት ውስጥ በመዝጋት የአማረኛ ተናጋሪ ሕፃናትን ከነነፍሳቸው አቃጥሏል በበደኖ በአርባ ጉጉ በአርሲ በጅማ በዘራቸው ተለይተው ታርደዋል ። ፈፃሚው በኦነግ ሥም ይሁን እንጅ የሕውኃት ሰዎች አብረው እንደፈፀሙትና የመለስ አመራርም ፈቃድ ነበረበት ።
እናም አሁንም አቶ ሌንጮ ሕውሓትን ደጅ መጥናታቸው የጀመሩት ያልጨረሱት የዘር ማጥፋት ተግባር የሕውሓትን ትብብር እንደሚያገኙ ተስፋቸው አልሞተም ።
ስለ ኦሮም ሕዝብ ቢያስቡ ኖሮ ከመቸውም በላይ የኦሮሞ ሕዝብ በደልና ግፍ በ21ኛው ክ/ ዘመን በሕውሓት እየተፈፀመበት ይገኛል ።
ታዲያ እንዴት ነው ከሕውሓት ጋር ሊሰሩ የሚያስቡት ምንድን ነው አንድ ሊያደርጋቸው የሚችለው ?

Shagiz Shagi's photo.
Shagiz Shagi's photo.